የእናቶች ቀን፡ ያለ እናት የመጀመሪያው የእናቶች ቀን

ሻረንና እናቷ ሎሬን Image copyright Shareen
አጭር የምስል መግለጫ ሻረን እናቷን ያጣችው በቅርቡ ነው

ስለ እናት ፍቅር ለመግለፅ ቃላት ያጥረናል የሚሉት በርካቶች ናቸው። የእናትን ፍቅር ግዝፈቱንና በቃላት የማይገለፅ መሆኑን ለማሳየት። ስለ እናት ብዙ ተዚሟል፤ ተገጥሟል፤ ተነግሯል። ወደፊትም ይቀጥላል ... ዛሬ የእናቶች ቀን ነው። ይህ ቀን እናታቸው ከጎናቸው ላሉት ደስታ፤ በሕይወት ለተለየቻቸው ደግሞ ሃዘን ፈጥሮ ያልፋል።

የልጃቸውን ደፋሪ የገደሉት እናት ነጻ ወጡ

ለመሆኑ እናታቸው በሞት ከተለየቻቸው በኋላ የእናቶችን ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ እንዴት ያከብሩታል? ምንስ ይሰማቸዋል?

"የእናቶች ቀን ባይመጣ ደስ ይለኛል" የምትለው የለንደኗ ነዋሪ ሻረን ዱሳርድ ናት። ሻረን እናቷን ሎሬንን በሞት ካጣች ገና አስር ሳምንታት ብቻ ናቸው የተቆጠሩት። በመሆኑም የእናቶች ቀን ደንታም አይሰጣት። እናቱን ላጣ ሰው የእናቶች ቀን የተለየ ትርጉም አለውም ትላለች።

"ሃዘናችሁን ለመቋቋም ስትታገሉ፤ ቀኑን አስመልክቶ በየማሕበራዊ ሚዲያው ላይ የሚለጠፉ ፎቶግራፎችና የሚተላለፉ መልዕክቶች ይጎርፋሉ፤ ይህንን ምንም ማስወገድ አይቻልም።" ትላለች።

እርሷ እንደምትለው ይህ ብቻም ሳይሆን በየሱቆቹ የሚሸጡ የስጦታ ካርዶች፣ አበቦች እና ስጦታዎች አብራችሁ ስለሌለች እናት እንድታስቡና እንደታከብሩ ይገፋፋል።

ሀና እና ጓደኞቿ የሰሩት የእናቶች ምጥ መቆጣጠሪያ

"ይህ ቀን መምጣቱን ሳስብ በጣም ይጨንቀኛል፤ ምን እንደማደርግ ይጠፋኛል ፤ ማሕበራዊ ገፄን ለመዝጋትም አስባለሁ" ትላለች ሻረን።

የ28 ዓመቷ ሻረን እንደምትለው በርካታ ሰዎች ስሜቷን ለመጠበቅ ሲሉ ከእርሷ ጋር ስለ እናቶች ቀን ማውራታቸውን ትተዋል። ነገር ግን ለአንድ የራዲዮ ጣቢያ በሰጠችው ቃለ-መጠይቅ ሰዎች ቀኑን በማሰብ ብቻ መልዕክት ቢልኩላት እንደማይከፋት ተናግራለች።

"ዋናው ነገር ሰዎች መጠየቀቻውና ደህንነቴን ማረጋገጣቸው ነው፤ እርሱን ደግሞ እፈልገዋለሁ" ስትልም አክላለች። "እናቴ የተጠበሰ ሥጋ ትወዳለች፤ እርሱን እንሠራለን፤ እርሷን የምናስብበትና ፍቅራችንን የምንገልፅበት ቀን ነው ፤ ላለማልቀስ እሞክራለሁ" ስትል ቀኑን እንዴት ልታሳልፈው እንዳሰበች ገልፃለች።

Image copyright Chrstie Ford
አጭር የምስል መግለጫ ክሪስቲ እና እናቷ ማንዲ

ሌላኛዋ ቢቢሲ ያነጋገራት ክሪስቲ ናት። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የክሪስቲ እናት ከዚህ ዓለም የተለየችው በድንገት ነበር። እርሷ እንደምትለው በዚህ ቀን በስጦታዎችና በስጦታ ካርዶች መከበብ ለእርሷ በጣም ከባድ ነው።" በየዓመቱ የስጦታ ካርድ እሰጣታለሁ፤ ካርዶቹ የሚያስቁ ነበሩ፤ ሌላ ስጦታ ገዝቼላት አላውቅም" ስትል ታስታውሳለች።

ክሪስቲ የማህበራዊ ሚዲያው እንደረዳት ትናገራለች ምክንያቱም እናታቸውን በቅርቡ ያጡ ሰዎች እዚያ ላይ አሉ፤ እነርሱን ስታይም ብቻዋን እንዳልሆነች ይሰማታል።

እርሷ እንደምትለው አንዳንድ ሰዎች በእርሷ ሃዘን ምክንያት ደስታቸውን ለመደበቅ ይሞክራሉ። እርሷ ግን ይህንን አትፈልገውም።

ካለሁበት 16 ፡ 'ጭራሹኑ መጥፎ ነገሮች እንዳይከሰቱ ማድረግ ብችል ደስታዬ ወደር የለውም'

"ርዕሱን አትለውጡት ምክንያቱም እናንተ የእራሳችሁ እናት አለች ፤ እራሳችሁን ደስተኛ አድርጉ" ስትል በእርሷ ምክንያት ሌሎች ሰዎች በስሜት ሲመሰቃቀሉ ማየት እንደማትወድ ገልፃልናለች።

ሳራ ቤኔት በሃዘን ላይ ያሉ ሕፃናት፣ ወጣቶችንና ቤተሰቦቻቸውን የሚረዳ ግብረሰናይ ድርጅት ውስጥ ትሠራለች። እርሷ እንደምትለው "እናታችሁን ካጣችሁ የመጀመሪያው የእናቶች ቀን ከሆነ ሁሉም ነገር ይቀየራል፤ እናት ስትሞት ቀሪው ቤተሰብ በዚህ ቀን ምን ማድረግ እንዳለባቸው አያውቁም፤ ምንስ ሊያደርጉስ ይችላሉ?" ጥያቄዋ ነው።

እርሷ እንደምትለው አንዳንዶች በሕይወት የሌለች እናታቸውን በማስታወስ ያከብሩታል፤ ሌሎች ግን ጭራሽኑ ስለ ቀኑ ማሰብ አይፈልጉም።

በመሆኑም ትላለች ሳራ "በጣም ከባድ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል፤ ለቤተሰብና ለወዳጅ ዘመድም ስለ እሷ ማሰብ ምን ያህል ፈታኝ እንደሚሆን መገንዘብ ይጠይቃል" ቁጭ ብላችሁ እራሳችሁን አዳምጡ። እናትን ማጣት ምን ያህል አንገብጋቢ እንደሚሆን ማሰብ ቀላል ነው ስትል ስሜቷን አጋርታለች።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ