የሥራ ቃለመጠይቅ ማድረግ ያስፈራዎታል? መፍትሄዎቹን እነሆ

ቃለመጠይቅ ላይ ፈገግ ያለች ሴት Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ቃለመጠይቅ አሁንም ሠራተኞችን ለመመልመል ወሳኝ ዘዴ ነው

ዓመታትን ተምረው ሲመረቁ፣ በሰለጠኑበት ሙያ ሥራ ማግኘት ፈታኝ ሲሆን፣ በዛ ላይ ደግሞ አሠሪዎች ምን እንደሚፈልጉ ሳያውቁ ሲቀር በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆናል። ሠራተኞችን የመቅጠሪያ ዘዴ በየጊዜው የሚለዋወጥ ቢሆንም አካላዊ ቃለ-መጠይቅ ግን እስካሁን ያልተቀየረ የምልመላ ወሳኝ አካል ነው።

"ቃለ-መጠይቅ እስካሁን ለማንኛውም የሥራ ምልመላ በጣም አስፈላጊው ሠራተኞችን የመለያ መንገድ ነው" የምትለው ጄን ቲፕን በሎይድ ባንኪንግ ግሩፕ የሰው ኃይል ባለሙያ ናት።

ከሰው ፊት ሃሳብን መግለፅና ጥያቄዎችን መመለስ መቻል የሰዎችን ሥራ የማግኘት እድል ይወስናል ትላለች።

"ሊወልዱ እያማጡም የእናታቸውን ስም ነው የሚጠሩት" ሚዲዋይፍ

በቃለመጠይቅ ጊዜ የሚረዱ ጥቂት ነጥቦች እነሆ፡

1.ስለመሥሪያ ቤቱ ጥናት ያድርጉ

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ቃለመጠይቁ ምን ዓይነት ሊመስል እንደሚችል ጥናት ያድርጉ

በመጨረሻ የሚፈልጉትን ስራ አግኝተው ለቃለመጠይቅ ከደረሱ ከቃለመጠይቁ በፊት ስለ ድርጅቱ በቂ ጥናት ማድረግዎን እንዳይዘነጉ።

ጥናትዎ ድርጅቱ ምን አይነት ሥራ ላይ ነው የተሰማራው? አመታዊ ገቢው ምን ያህል ነው? አለቃው ማን ነው? የሚሉትን ጥያቄዎችና የድርጅቱን ቀንደኛ ተፎካካሪዎች ለማወቅ ይሞክሩ።

ስለድርጅቱ ለማጥናት ሲፈልጉም ከድረ-ገፅ መጀመር ስራን ያቀላል።

ድርጅቱ ላይ ካደረጉት ጥናት ባለፈ ቃለ መጠይቅ የሚያደርግልዎትን ኃላፊ ለማወቅ ይሞክሩ።

ቃለመጠይቁም ካለቀ በኋላ የሚጠይቁት ጥያቄ ማዘጋጀት ስለድርጅቱ ያለዎትን እውቀትና ፍላጎት ስለሚያሳይ የተመራጭነት እድልዎትን ያሰፋል።

2.ሊጠየቁ የሚችሏቸውን ጥያቄዎች ይለማመዱ

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ጓደኞችዎን ደርድረው ቃለመጠይቅ ማድረግ ይለማመዱ

ቃለመጠይቅ ከመግባትዎ በፊት ሊጠየቁ ይችላሉ ብለው የሚያስቧቸውን ጥያቄዎች መርጠው በመመለስ ይለማመዱ።

ጥያቄዎቹ ከከበድዎት የተለያዩ ጥያቄዎችን እንዴት ባለ መልኩ መመለስ እንዳለብን የሚያስረዱ ድረ-ገፆችን መመልከት ይችላሉ።

ያለ እናት የመጀመሪያው የእናቶች ቀን

መልስዎትን ሲያዘጋጁ ብዙ ጊዜ ካሳለፏቸው የሥራ ልምዶች ምሳሌዎችን እየወሰዱ ቢሆን ይመረጣል። ምሳሌዎትንም መቼ፣ የትና እንዴት እንዳደረጉት በመግለፅ ጥልቀት ይስጡት።

የሚሰጧቸው መልሶች ከባለፈው የሥራ ልምድዎ ተነስተው በአዲሱ የሥራ ዘርፍ ላይ የሚፈጥሩትን መልካም እሴት ቢያስረዱ መልካም ነው።

3.ቀልብን የሚገዛ አለባበስ ይልበሱ

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ራስዎን ከተጠራጠሩ በደንብ በመልበስ የራስ መተማመንዎን ይጨምሩ

የመጀመሪያ እይታ አሁንም ወሳኝ ነው።

አንዳንድ ቀጣሪዎች ውሳኔያቸውን የሚያደርጉት በ30 ሰከንድ ውስጥ ነው። አንዴ የአሰሪዎን ቀልብ ካልገዙ አስገራሚ መልሶችን ቢመልሱም ስራውን የማግኘት እድሎ ይጠባል።

ድርጅቱ የአለባበስ ምርጫ ባይኖረውም በቃለመጠይቅዎ ጊዜ ግን በጅንስ እንዲመጡ አይጠብቁም። ሥራ ቀጣሪዎች ሠራተኞች ለቃለመጠይቅ ሲመጡ ለሥራው የሚመጥነውን "ፕሮፌሽናል" ልብስ እንዲለብሱ ይጠበቃሉ። ለወንዶች ሱፍ በከረባት የተመረጠ እንደሆነ የቀጣሪዎች ሃሳብ ነው።

በብሔር ግጭት የተነሳ የሚፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ

ቀለል ያለ ቃለመጠይቅ ከሆነ ደግሞ ንፁህና የተተኮሰ ልብስ ቢለብሱ መልካም ይሆናል።

4.አጨባበጥዎን ያስተካክሉ

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ከቃለመጠይቅዎ በፊት የሚያደርጉት አጨባበጥ ሚና አለው

ብዙ ጊዜ ችላ የምንለው ነገር ቢሆንም ሥራ ቀጣሪዎ በእጅ አጨባበጥዎ ሊገምትዎት ይችላል።

ትክክለኛ ጠንከር ያለ ሰላምታ ደፋር፣ የሥራ ሰውና ስለራስዎ ያለዎትን በጎ ግንዛቤ ይናገራል። ነገር ግን ከመጠን ያለፈ ጠንካራ ሰላምታ የሚሰጡ ከሆነ የበላይነት ባህሪ እንዳለዎት ሊናገር ይችላል። በሌላ መልኩ እጅዎ ላላ ያለ ከሆነ የማፈርና የመፍራት ባህሪ እንዳለዎት ያሳብቃል።

ይሄንንም ለማሻሻል ጓደኞችዎን ሰላም በማለት ተለማምደው እጆትን ማላላት ወይም ማጥበቅ እንዳለብዎት ይለዩ።

ስጋን የተካው "ስጋ"

የቃለመጠይቁ ቀን ሰላምታ ሲሰጡ ዓይን ለዓይን መተያየትን አይዘንጉ። ከሰላምታ በፊትም የእጆትን ላብ መጥረጊያ መሃረብ መያዝ እንዳይረሱ ማንም ሰው በላብ የተጠመቀ መዳፍ መጨበጥ አይፈልግም።

5.ፈገግታ

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ እዚህ በመገኘቴ በጣም ደስተኛ ነኝ!

ተጨንቀውና በሃሳብ ተውጠው ባሉበት ጊዜ ሌላው ቀርቶ ስሞትንም ሊረሱት ይችላሉ።

ፈገግታ በቀላሉ ሰላምታ ማስተላለፍ ሲችል "እዚ ስለተገኘው ደስ ብሎኛል፤ ደስተኛ ሰው ነኝ" ይላል። ስለዚህ በሩን ከፍተው ከገቡበት ቅፅበት ጀምሮ ፊቶን ፈገግታ ባይለየው እድሎትን ያሰፋሎታል።

አካላዊ አቀማመጥን በተመለከተ ደግሞ ቀጥ ብሎ መቀመጥ ከፈገግታ ጋር ተጨምሮ መልካም አካላዊ ገፅታ ይሰጥዎታል።

6.ጭንቀት እድልዎን እንዲያሳጣዎ አይፍቀዱለት

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ከቃለመጠይቅ በፊት ራሶትን ያረጋጉ፤ ትንፋሽ መውሰድ አንዱ መንገድ ነው

አድሬናሊን በጣም አስገራሚ ነገሮችን እንድናካሂድ ወይም ደግሞ በጣም የወረደ ስራ እንድንሰራ ሊያደርገን ይችላል።

ቃለመጠይቁን ስንደርስ ያጠናናቸውና ለመመለስ የተዘጋጀናቸው መልሶች በሙሉ በነው ሊጠፉ ይችላሉ። ከዚህም አልፈው በአካላዊ ገፅታችን እጃችን ሲንቀጠቀጥ፣ ሲያልበን ወይም ስንደናበር ለሰዎች ሊታይ ይችላል።

ቴምር በረመዳን ለምን ይዘወተራል?

እርስዎ እንደዚህ ያለ ጭንቀት የሚያስቸግርዎት ከሆነ ከቃለመጠይቁ በፊት ራስዎን ለማረጋጋት የሚረዱ እንደ ትንፋሽ መውሰድ የመሳሰሉ ልምዶችን ሊያዳብሩ ይችላሉ።

መልካሙ ነገር አድሬናሊን የተለየና በጣም አሪፍ ቃለመጠይቅ እንድናደርግ ሊረዳን ስለሚችል ነው።

7.እርስዎን ምን ልዩ እንደሚያደርጎት ይናገሩ

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ በቃለመጠይቅ ላይ እርስዎን ልዩ የሚያደርጎትን ነገሮች ይግለፁ

የኮንስትራክሽን ድርጅት ባለቤት የሆኑት ዴርሞት ሮኒ "ፊት ለፊት የሚደረግ ቃለመጠይቅ ሰዎች ስለራሳቸው ልዩ ተሰጥኦ፣ ፍላጎትና ባህሪ እንዲናገሩ እድል ይሰጣቸዋል" ይላሉ። በቃለመጠየቁ ጊዜ ራስዎን በጥልቀት ማስተዋወቅ መቻል አለብዎት።

ከዚህም በተጨማሪ ምን ያህል ሥራውን ለማግኘት ጉጉት እንዳለዎት፣ ድርጅቱን ምን ያህል እንደሚወዱትና መሥራት እንደሚፈልጉ መግለፅ መልካም ነው።

8.ተስፋ አይቁረጡ

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው የሚችሉትን ጥረት ማድረግ ይቀጥሉ!

ቃለመጠይቁ በጠበቁት መንገድ እየተሳካልዎት ባይሆንም እርስዎ ግን እንደማያገኙት ወስነው ከመሞከር መሸሽ የለብዎትም። ቃለመጠይቅ አድራጊዎቹም እንዳልወደድዎት ሊሰማዎት ይችላል፤ ነገር ግን ውሳኔያቸውን ሳይሰሙ አይወስኑ።

ሥራ ቀጣሪና አባራሪ እየሆነ የመጣው ሮቦት

የሥራ ቀጣሪው የሚፈልገው የእርስዎን ቀጣይ መልስ ሊሆን ስለሚችል ለሁሉም ጥያቄዎች የሚችሉትንና አሪፍ የሚሉትን ይመልሱ።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ