"በሀገራችን ከሶስት ሴቶች አንዷ ላይ ጾታዊ ጥቃት ይደርሳል"

ወ/ሮ ዘሃራ ለገሰ የሥነ ልቦና አማካሪና ማኅበራዊ ሠራተኛ

በሲቪል ምህንድስና ዘርፍ አዲስ ተመራቂ የሆነችው ወጣት ወጥታ የምትገባበት ሥራ በማግኘቷ ደስተኛ ነበረች። ኑሮዋን ያደረገችው ሥራ ባገኘችበት አዲስ አበባ ነው።

በአንድ አጋጣሚ ወደጉዳይዋ ለመሄድ በተሳፈረችው ታክሲ ውስጥ አንድ ወጣት ተዋወቀች። ወጣቱ ጨዋታ ጀመረ፤ ጨዋታው ወደስልክ ልውውጥ አደገ። ይህ የስልክ ልውውጥ ወደ ፍቅር ግንኙነት ከፍ ለማለት ወር አልፈጀበትም።

ፍቅሩ ፍሬ ሳያፈራ ግን ባለፈው ዓመት መስከረም ወር ላይ ፍቅረኛዬ ያላትን ወጣት ገደላት።

ፍቅረኛውን በገደለበት ሌሊት ተከራይታ ትኖርበት ከነበረው ቤት ወደ እሱ መኖሪያ የወሰዳት "ጠዋት ጠበል እንጠመቃለን" በሚል ነበር።

ነገሩ ያላማራት አፍቃሪ ግን፤ አብረው ተኝተው እያሉ አለቀሰች፤ እሱ እንደሚለው "ከማልቀስም በተጨማሪ እኩለ ሌሊት ላይ ተናደደች"።

ለሰሚም ለነጋሪም በሚከብድና ሰቀጣጭ ሁኔታ የገደላት ወጣት ለፖሊስ በሰጠው ቃል፤ ሊገድላት አቅዶ እንዳላደረገው በማስረዳት ተከራክሯል።

ፖሊስ ወጣቱን በቁጥጥር ሥር ሲያውለው ከሌላ ሴት ጋር በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ዓለሙን እየቀጨ ነበር።

ይህ ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም የማያውቅ ቢመስልም፤ እንደአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሪፖርት ከሆነ ካለፈው ሐምሌ እስከ ዘንድሮ መጋቢት ድረስ ባሉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 13 ሴቶች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

ምንም እንኳን ብዙዎች ጥቃትን አካላዊ ወይም ፆታዊ ብቻ ነው የሚል እሳቤ ቢኖርም እንደ የሥነ ልቦና አማካሪና ማኅበራዊ ሠራተኛዋ ዘሃራ ለገሰ ግን ሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት አምስት አይነት ነው። እነዚህም የሥነ የልቦና፣ አካላዊ ፣ የአእምሮ ፣ ፆታዊና የኢኮኖሚ ጥቃት ናቸው።

በዝምታ ማንባት

ወ/ሮ ዘሃራ እንደሚሉት በሴቶች ላይ የሚደርሰው የመጀመሪያው ጥቃት የሥነ ልቦና ነው።

"ራሷን እንዳታምን፣ እንድትጠራጥር፣ እንድትፈራ ያደርጋል። ከተጋቡ ወይንም የፍቅር ጓደኝነት ከጀመሩ በኋላ ቶሎ ብሎ ከጓደኞቿ ወይም ከቤተሰቦቿ ጋር ይነጣጥላታል። ብቸኛ እንድትሆንም ያደርጋል" ሲሉ ጥቃትን የሚያደርሱ ወንዶች ሴቶችን በምን መንገድ ብቸኛ እንዲሆኑ እንደሚያደርጉ ያስረዳሉ።

የተነጠቀ ልጅነት

አንዲትን ሴት 'እኔ ነኝ ያለሁልሽ'፣ 'አብሬሽ ነኝ' በማለት ከአካባቢውና ከማኅበረሰቡ እንድትገለል ካደረገ በኋላ እምሮዋና ልቦናዋ ላይ ጥቃት ያደርሳል በማለት ሴቶች ጥቃት ሲደርስባቸው ደፍረው ለመናገር እንደሚቸገሩ ይገልጻሉ።

ባለሙያዋ እንደሚሉት፤ ከሥነ ልቦናዊ ጫናው ባሻገር የኢኮኖሚ ጥገኛ ማድረግ አንድ የጥቃት መንገድ እንደሆነ ይገልፃሉ። አክለውም "ልጆች ካሏት ደግሞ ጥቃትን የምትሸከምበት ጫንቃ ይደነድናል" ይላሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ ሴት ልጅ ምንም አይነት በደል ቢደርስባት ሴት ልጅ 'ባሏን እንዳመሉ ችላ መኖር አለባት' የሚለው የተዛባ አመለካከት ከፍተኛ ተፅእኖ ከማድረሱ በተጨማሪ ይህንን እንኳን ጥሳ 'ከፋኝ'፤ 'ተበደልኩ'፤ ብላ ወደቤተሰቦቿ ዘንድ ብትሔድም 'ተመለሺ' ትባላለች። ።

ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያ ውስጥ ሐይማኖት በማህበራዊ ህይወት ውስጥ ያለው ሚና የጎላ በመሆኑ ምንም አይነት ጥቃት ቢደርስባቸው በተለያዩ እምነቶች ዘንድ ፍች ሃጥያት ነው ስለሚባል እንደ አማራጭም አይታይም።

መአዛን በስለት ወግቶ ከፖሊስ ያመለጠው አሁንም አልተያዘም

ከንብረት ክርክር፣ የልጆች ትምህርት ቤት ክፍያ፣ የባህልና እምነት ጉዳይ ከጥቃቱ በአንዴ እንዳትወጣ ስለሚያግዷትም ጥቃት የሚደርስባት ባለትዳር ሴት ከግንኙነቱ ለመውጣት 10 ዓመት እንደሚፈጅባት ወ/ሮ ዘሃራ ይናገራሉ።

ብዙ ጊዜ በፍርድ ቤት ክርክር ወቅት ባሎች 'ልጅ አልሰጥም' ስለሚሉ፣ በተለያዩ ነገሮች ስለሚያስፈራሩና አብዛኞቹ ሴቶች በራሷቸው የሚያዙበት ገቢ ስለሌላቸውም ለመውጣት እንደሚቸገሩ ይገልጻሉ።

"የሚያስፈራ ነገር ውስጥ ካለች ወደጥቃቱ ተመልሳ ልትገባም ትችላለች" ይላሉ።

የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።
"በሀገራችን ከሶስት ሴቶች አንዷ ላይ ጾታዊ ጥቃት ይደርሳል"

አንዲት ሴት ሥራ ቢኖራትም የምታገኘውን ገንዘብ በአጠቃላይ ለቤት ወጪና ለልጆች ማሳደጊያ እንድታውለው ስለሚያደርጋት ከዕለት ጉርስ፣ ከልጆች ትምህርት ቤት ክፍያና ቀለብ የሚተርፍ ገንዘብ አይኖራትም የሚሉት ባለሙያዋ፤ የትዳር አጋሯ ግን የሚያገኘውን ገቢ ለቤትና ለተያያዥ ወጪዎች ስለማያውል ገንዘብ እንደሚያጠራቅም ያስረዳሉ።

"እሷ ገንዘብ ስለማይኖራት የጥቃት ሰለባ ሆና አብራው ትኖራለች" ይላሉ።

ሌላው በአፍላ ፍቅር ላይ ያሉ ወጣቶች ጉዳይ ነው። "ወጣቶች ፍቅረኛ ሲይዙ የምንመለከተው የመነጠል ባህሪ ሌላው ችግር ነው" ይላሉ ባለሙያዋ።

ወጣቶች የጦፈ ፍቅር ውስጥ እንደሆኑ ሲሰማቸው ከፍቅረኛቸው ጋር የሚለዋወጡት ተደጋጋሚ የጽሑፍ መልዕክት ሳይቀር ለጥቃት በር ይከፍትላቸዋል ሲሉ ያስረዳሉ።

በተለይም ቁጥጥር በሚመስል ሁኔታ እያንዳንዷ እንቅስቃሴዋን ማሳወቅ የሚኖርባትን ሁኔታ ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት እንደሆነ ይናገራሉ፥

"ክፍል ስትገባ 'ገባሁ' ብላ መልእክት እንድትልክ፣ ቤት ስትገባ መግባቷን እንድትናገር፣ ከጓደኞቿ ጋር ስትሆን ከነማን ጋር እንደሆነች እንድትገልፅ የምትገደደው በፍቅር ስም ነው። ይህ በፍቅር ስም የሚደረግ ክትትል እሷን ከማኅበራዊ መስተጋብሯ በመነጠል ከሱ ጋር ብቻ እንድትሆን ያደርጋል። በኋ ላይ ጥቃት ሲደርስባት መሸሺያ እንድታጣም ያደርጋታል" ይላሉ።

"በወንድሜ ለአምስት ዓመታት ተደፍሬአለሁ"

አሲድን እንደ መሳሪያ

ወጣቶች ስለፍቅረኛቸው ባህሪ ሲጠየቁና ፍቅሩን ስለሚገልፅበት መንገድ ሲናገሩ በቀን ምን ያህል ጊዜ የጽሑፍ መልእክት እንደሚላላኩ እንደማስረጃ ያቀርባሉ። ይህ ግን የፍቅር መግለጫ ሳይሆን መከታተል ነው።

አንዲት ሴት ታክሲ ድረስ ለሸኘ አፍቃሪ፣ ቤት ስትደርስ ማሳወቅ እንዳለባት ከተሰማት፣ ካላሳወቀች ዘለፋና ማስፈራሪያ ካደረሰባት ጉዳዩ የጥቃት ምልክት ስለሆነ እድትጠነቀቅ ይመክራሉ።

"የመከታተል ጠባይ ያለበት አፍቃሪ በራሱ የማይተማመን፣ እሷንም ቶሎ መቆጣጠር የሚፈልግ ሰው ነው" በማለት ባለሙያዋ ያብራራሉ።

ጥቃት የሚያደርሱ ወንዶች በደሉን ከፈፀሙ በኋላ ይቅርታ በመጠየቅ ይታወቃሉ የሚሉት ወ/ሮ ዘሃራ፤ 'እንዲህ ያደረኩት ስለምወድሽ ነው'፣ 'ሥራ በዝቶብኝ ተጨናንቄ ነው'፣ 'ያለሽኝ አንቺ ብቻ ነሽ'፣ 'ያለአንቺ መኖር አልችልም' ሲል ይቅርታ እንደሚደረግለት ገልጸው፤ ይህ ግን የማያልቅ የጥቃት ኡደት ነው" ይላሉ።

ጥቃቱ ከአካል ማጉደል ነፍስ እስከማጥፋት እንደሚደርስም ያስረግጣሉ።

'አስጸያፊ' ከመባል ኦስካር ወደማሸነፍ

ጥቃት በከተማና በገጠር በተማሩባልተማሩ

አንዲት የ26 አመት ወጣት ናት። ትውልዷ አምቦ ሲሆን፤ ያደገችው ቢሾፍቱ ነው። እናቷ የአእምሮ ታማሚ ስለነበረች እሷና ሦስት ወንድሞቿን ጥላ የሄደችው ገና ጨቅላ ሳሉ ነበር። ስለዚህም በየሰዉ ቤት እየተንከራተቱ የእለት ጉርሳቸውን ለማግኘት መሞከር ግድ ሆነባቸው።

ወጣቷ ቢሾፍቱ አንድ ገበሬ ቤት በሠራተኝነት ተቀጠረች። የተቀጠረችበት ቤት ጎረቤት ግን ለክፉ ተመኛት። አሳቻ ቦታ ጠብቆ፣ አስፈራርቶ ደፈራት። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ብዙም ሳይቆይ ነፍሰ ጡር መሆኗን አወቀች።

ሚስጥሯንና ልጇን በሆዷ ይዛ ወደከተማ ሄደች። ከተማ የቀን ሥራ እየሠራች ሲከፋም ጠላ እየቸረቸረች ልጇን በሰላም ተገላገለች። አንድ ዕለት ልጇን እያሳደገች ጠላ የምትቸረችርበት ሰፈር ዘወትር አተላ እየመጣ ለሚወስድ አንድ ሰው ልጇን አደራ ብላ ውሃ ለመቅዳት ሄደች። ስትመለስ ግን ልጇ በደም ተለውሳ አገኘቻት። ወጣቷ የእሷም የልጇም እጣ መመሳሰሉ አቅሏን አሳታት።

ባደጉ አገሮች ከአራት ሴቶች አንዷ ጥቃት እንደሚደርስባት ጥናቶች የሚያሳዩ ሲሆን በኢትዮጵያ ግን ከሁለት ሴቶች አንደኛዋ ጥቃት ይደርስባታል የሚል ጥናት ሲሆን ሌላው ጥናት ደግሞ ከሦስት ሴቶች አንዷ የጥቃት ሰለባ ነች የሚል እንደሆነ ወ/ሮ ዘሃራ ይናገራሉ።

"የየትኛውም ሐይማኖት ተከታይ፣ የየትኛውም ጎሳ አባል ብትሆን ጥቃት ያጋጥማታል ማለት ነው።" ይላሉ።

የሥነ ልቦና ባለሙያዋ እንደሚሉት፤ በአንጻራዊነት ፊደል የቆጠረች ሴት የሚደርስባትን ጥቃት በይፋ ለመናገርና በደሏን ወደፍትሕ አደባባይ ለማድረስ ድፍረት አላት።

"የጥቃት መጀመሪያው ማስፈራራት ነው" የሚሉት ወ/ሮ ዘሃራ፤ 'ይህንን ካደረግሽ እገልሻለሁ?'፣ 'ልጅሽን አልሰጥሽም' ወዘተ. . . የሚሉ ማስፈራሪያዎች አእምሮና ልቦና ላይ የሚሰነዘሩ ከባድ ጥቃቶች እንደሆኑ ይገልጻሉ።

ይህ ለአካላዊና ለጾታዊ ጥቃት መንገድ ይከፍታል የሚሉት ባለሙያዋ፤ ትዳር ውስጥ ያለች ሴት የሚደርስባት የልቦናና የአእምሮ ጥቃት ራሷን ዝቅ አድርጋ እንድትመለከትና ራሷን እንዳታምን እንደሚያደርግ ይገልጻሉ።

"አይኗን ሰብራ የምትኖር፣ ድምጿን ዝቅ አድርጋ የምትናገር ትሆናለች፤ ራሷን መጠበቅ ትተዋለች" በማለት ስለሚታዩት ባህሪዎች ያስረዳሉ።

'ወንዶች ለም' መዘዝ ያለ...አይመዘዝ

"አብዛኞቹ ጥቃት አድራሾች የሚያድጉት በአጥቂ አባወራ እጅ ነው" የሚሉት ወ/ሮ ዘሃራ፤ እነዚህ ልጆች በሐይማኖት አባቶች፣ በቅርብ ዘመዶች ወይም በሌላ አካል ጥቃት ማድረስ ተገቢ እንዳልሆነ እየተነገራቸው ካላደጉ ጥቃት አድራሽ ሆነው ይቀራሉ ይላሉ።

ወንድ ልጅ ሲያድግ መብቱ እንዲጠበቅ፣ ራሱን እንዲያከብር፣ በጨዋታ ወቅትም ጉልበት የሚፈትኑ ውድድሮች ላይ እንዲሳተፍ ይደረጋል።

በተቃራኒው ሴቶችን ተንከባካቢ በማድረግ ራሳቸውን ችለው ከመቆም ይልቅ ደጋፊ እንደሚያስፈልጋቸው እንዲያስቡ ይደረጋሉ።

ኢንተርፖል 50 ህጻናትን ከጾታዊ ጥቃት መታደጉን አሳወቀ

በጉርምስና ወቅት በሚኖሩ ጓደኞች መካከል ለከፋና ጥቃትን እንደጀብድ መታየታቸው ሌላው ለአጥቂነት የሚገፉ ምክንያቶች ናቸው።

'የደበደብኳት ስለጠጣሁ ነው' የሚሉ ሰዎችን የምንሰማው፤ ጥቃት ያደረሱት ስለጠጡ ሳይሆን ቀድሞውንም የአጥቂነት ባህርይ ውስጣቸው ኖሮ በኋላ በሱስ ገፊ ምክንያትነት ወጥቶ እንጂ፤ መጠጥ በራሱ አጥቂ አድርጓቸው አይደለም" ይላሉ።

በትዳር ውስጥ ጥቃት ከመድረሱ በፊት የሚታየውን ባህሪ ሲያስረዱ የወንዱን ቁጠኛነትና ተናዳጅነትን ይጠቅሳሉ።

"ወንዱ በር ጓ አድርጎ ሲወረውር፣ እቃ ሲሰብር፣ ሲጮህ እሷ ልጆቿን ይዛ ወደ ጓዳ ትገባለች። ጉዳዩ ወደጥቃት ከተሸጋገረ በኋላ ሽማግሌ ይመጣል። በሽምግልና ወቅትም እግሯ ስር ወድቆ ይቅርታ መጠየቅ፣ ካሳ መስጠት ይከተላል። ይህ ጥቃት ከደረሰ በኋላ የሚመጣ መፍትሄ በመሆኑ ዘላቂነት የለውም" ይላሉ ባለሙያዋ።

ሽምግልና መጀመር ያለበት በቤት ውስጥ ውጥረቱ ሲጀምር እንጂ ነገሮች ሲባባሱ አለመሆኑንም ያክላሉ።

ፖፑ የካቶሊክ ቄሶች ሴት መነኮሳትን የወሲብ ባሪያ ማድረጋቸውን አመኑ

በሽምግልና ወቅት በእድሜ ከፍ ያሉ፣ ሱሰኛ ያልሆኑ፣ አርአያ የሚሆኑ ሰዎች ግጭት የተፈጠረበት ቤተሰብን ጉዳይ በአንድ ቀን ሳይሆን ለወራት መከታተልና ማረቅ ያስፈልጋቸዋል ሲሉም ይመክራሉ።

ይህ ባለመሆኑ ግን የታረቁ ሰዎች ከጥቂት ወራት በኋላ በድጋሚ የሚጋጩ ሲሆን፤ጥቃቱም ከፍ ብሎ እስከሞት ድረስ ይሄዳል በማለት በትዳር ውስጥ የሚፈጠር ግጭት የሚፈታበትን መንገድ ማጤን እንደሚያስፈልግ ያስገነዝባሉ።

የቤተሰብ ድጋፍ

ጥቃት የሚደርስባቸው ሴቶች ማስፈራሪያም ስለሚደርስባቸው ፍትህ እንዳያገኙ ያግዳል። ስለዚህም አንዲት ሴት በሕግ ጉዳይዋን ስትከታተል ደህንነቷ ተጠብቆ የምትቆይበት ማእከል እንደሚያስፈልግ ያነሳሉ። በአገራችን ያሉት ማቆያዎች በቂ አለመሆናቸውንም ያስረዳሉ።

ጥቃት የደረሰባት ሴት ጠንካራ የቤተሰብ ድጋፍ ያስፈልጋታል የሚሉት ባለሙያዋ፤ የቅርብ ቤተሰቦች ጥቃት ወዳደረሰባት ሰው እንድትመለስ ከመገፋፋት ይልቅ ሊደግፏት እንደሚገባ ያስገነዝባሉ።

በአብዛኛው ጥቃት የሚያደርሱ ወንዶች 'ለቤት ቀጋ ለውጭ አልጋ' እንደሚባለው፤ ቤት ውስጥ ክፉ ቢሆኑም ለውጪ ሰው ግን ደግ ስለሆኑ፣ 'ባሌ በደል አደረሰብኝ' ስትል የሚያምናት አታገኝም።

ሀርቪ ዋንስታይን 44 ሚሊየን ዶላር ካሳ ሊከፍል ነው

ብዙ ጊዜ ጥቃት የሚያደርሱ ወንዶች የባለቤታቸውን ቤተሰቦች ጥሩ አድርገው ስለሚንከባከቡ፤ የገዛ ቤተሰቦቿም ለሷ ጠበቃ መሆን ይከብዳቸዋል ይላሉ። ስለዚህ ወደባለቤቷ ቤተሰቦችም ሆነ ወደእሷ ቤተሰቦች መሄድ አለመቻሏ ብቻዋን እንድትሆን ያደርጋታል።

አንድ ሰው መጀመሪያ ላይ ባህሪውን ሲያሳይ ማመን እንደሚያስፈልግ የሚናገሩት ወ/ሮ ዘሃራ፤ አንዲት ሴት የፍቅር ወይም የትዳር ጓደኛዋ አንዴ ጥቃት ሲያደርስ ወዲያው ማስቆም እንዳለባት ይመክራሉ።

'ይቀየራል'፣ 'ይሻሻል' እያሉ መቆየት የአካል መጉደልና የሕህይወት ዋጋ ሊያስከፍል እንደሚችልም ያክላሉ።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ