በሶማሊያ ሀገር አቀፍ ፈተና በመሰርቁ ለሌላ ጊዜ ተዘዋወረ

ተማሪ ፈተና ሲፈተን Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በፈተናው መሰረዝ 31 000 ተማሪዎች ይስተጓጎላሉ ተብሏል።

ባለፉት ዓመታት የማህበራዊ ሚዲያዎች በፍጥነት መስፋፋት ለምስራቅ አፍሪካ ሃገራት የትምህርት ምዘና አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል። ሶማሊያም ኢትዮጵያ ከዓመታት በፊት ያጋጠማትን ክስተት ተጋፍጣለች።

የትምህርት ሚንስትሩ አብዱላሂ ጎዳህ ባሬ እንደተናገሩት እስካሁን የተወሰዱት ፈተናዎች ተሰርዘዋል። ይህ ውሳኔም በመዲናዋ ሞቃዲሾ የተማሪዎች አመፅን አስነስቷል።

ፈተናው ወደግንቦት መጨረሻ የተዘዋወረ ሲሆን ዳግመኛ ስርቆትን ለመከላከል የማህበራዊ ሚዲያዎች እንደሚዘጉ አስታውቀዋል።

ሚንስትሩ በንግግራቸው የትኞቹ የማህበራዊ ሚዲያዎች እንደሚዘጉና በየትኞቹ የሃገሪቱ ክፍሎች እንደሚዘጉ በግልፅ አላስቀመጡም።

ዳልሳን የተባለ የሃገሪቱ ሬዲዮ እንደዘገበው ፈተናዎች ተሸጠው በማህበራዊ ድህረገፅ የተሰራጩት በወንጀለኞች ቡድን ነው።

አስገራሚው የደቡብ ኮሪያ ፈተና

ተማሪዎች ሞባይሎቻቸውን ሊነጠቁ ነው

ውሻውን "መንግሥት" ብሎ የጠራው ዘብጥያ ወረደ

ተማሪዎች ቅዳሜ የጀመሩት ፈተና በሳምንት ጊዜ ውስጥ የሚያልቅ የነበረ ቢሆንም ሚኒስትሩ ፈተናውን ማራዘም አስፈላጊ ነው ብለዋል።

በቴልቪዥን ላይ ቀርበው እንደተናገሩት "ያጭበረበረ ተማሪ በርትቶ ካጠና ተማሪ ጋር ሲቀመጥ ያሳፍራል። ስለዚህ የትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎች የወሰዷቸውም ሆነ የቀሯቸው ፈተናዎች ተሰርዘዋል።"

በፈተናው መሰረዝ ምክንየዓት 31 ሺህ ተማሪዎች ይስተጓጎላሉ ተብሏል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ