በኮ/ል መንግሥቱ ላይ በተሞከረው በመፈንቅለ መንግሥት ዙርያ ያልተመለሱት 5ቱ ጥያቄዎች

ካፒቴን እዮብ አባተ Image copyright እዮብ አባተ
አጭር የምስል መግለጫ ካፒቴን እዮብ አባተ

የ81ዱ መፈንቅለ መንግሥትን በተመለከተ ፊልሞች ተደርሠዋል፣ መጻሕፍት ተጽፈዋል፣ የጥናት ወረቀቶች ቀርበዋል...፡፡ አንዳቸውም ግን ለአንኳር ጥያቄዎች ከመላምት ያለፈ ምላሽ አልሰጡም፡፡

ምናልባትም በጉዳዩ ዙርያ እንደ አቶ ደረጀ ደምሴ የተጋ ተመራማሪ የለ ይሆናል፡፡ አቶ ደረጀ ከሌሎች አጥኚዎች የተለየ ቦታ የሚያሰጣቸው ሁለት አበይት ምክንያቶች አሉ፡፡ አንደኛ ጄ/ል ቁምላቸው በሕይወት ሳሉ አግኝተው ገጽ ለገጽ ማውጋታቸው ነው፡፡ በዚያ ላይ የሟቹ የጄ/ል ደምሴ ቡልቶ 4ኛ ልጅ ናቸው፡፡

የዛሬ 30 ዓመት... የኮ/ል መንግሥቱ አውሮፕላን ለምን አልጋየም?

‹‹የተሟላ መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ ያደረገው ዋናዎቹ ተዋናዮች በሙሉ በመሞታቸው ነው፤ ከዚህ በኋላ በአውዳዊ መረጃ (circumstantial evidence) ነው መናገር የምንችለው›› ይላሉ የሕግ አዋቂው አቶ ደረጀ ደምሴ ቡልቶ፡፡

‹‹ሴራው ሲሸረብ በነበረበት የመከላከያ አዳራሽ ቀኑን ሙሉ ምን ሲደረግ እንደነበር መናገር የሚችል ሰው በሕይወት የቀረ የለም" ይላሉ ሌላኛው የጉዳዩ አጥኚ ሻምበል እዮብ አባተ፡፡

ሻምበል እዮብ ቀድሞ የመከላከያ ደኅንነት መኮንን ነበሩ፡፡ በመፈንቅለ መንግሥቱ ዙርያ የሚያጠነጥን ‹‹ጄኔራሎቹ›› የሚል በርከታ ላለ ጊዜ የታተመ መጽሐፍ ደራሲ ናቸው፡፡

ቢቢሲ የመፈንቅለ መንግሥቱን አምስት ያልተመለሱ ጥያቄዎች ለነዚህ ሁለት ሰዎች አንስቶላቸዋል፡፡

1. የኮ/ል መንግሥቱን አውሮፕላን እንዳይመታ ያዘዘው ማን ነው?

መፈንቅለ መንግሥት አድራጊዎቹ የርዕሰ ብሔሩ አውሮፕላን በሚሳይል እንዲመታ አልያም አሥመራ ተገዶ እንዲያርፍ ስምምነት ደርሰው ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ግን በመጨረሻ ሰዓት ይህ ውጥን ተቀለበሰ፡፡ ለምን? በማን?

አቶ ደረጄ ደምሴ ቡልቶ፡-

"ለማወቅ ፈልጌ ማወቅ ያልቻልኩት ነገር ምንድነው መሰለህ? ይሄ አሁን አንተ የጠየቅከኝን ጥያቄ ነው፡፡ የአውሮፕላኑን ሁኔታ ፕላኑ እንዲቀየር ያደረገው ማን ነው? በምን ሁኔታ ሊቀየር ቻለ? ደግሞስ የመንግቱ አውሮፕላን ወድቋል፤ እሱም ተገድሏል የሚለው መልክት እንዴት ወደ አሥመራ ተላለፈ?...

ጓድ መንግሥቱ እንባ የተናነቃቸው 'ለት

ግምትህን ንገረኝ ካልከኝ…ጄ/ል አመሃ ይመስሉኛል አይመታ ያሉት፡፡ ምክንያቱም እርሳቸው ገና ያን ቀን ነው ስለ መፈንቅለ መንግቱ የተነገራቸው፡፡ወደ ደብረዘይት እየሄዱ ነው ከመንገድ ተጠርተው ወደ መከላከያ ሚኒስር የገቡት፡፡..."

ሻምበል እዮብ አባተ

የመጀመርያው ዕቅድ ሰውየው እንዲመቱ ነው። ይሄን የሚደግፉት እነ ጄ/ል አበራ ናቸው። ፕሬዝዳንቱ ካልተገደሉ ነገሩ አይሳካም ብለው ያምናሉ። በአመጽ ውስጥ ያሉት 'ኤርፎርሶች' ደግሞ ይሄን አልደገፉም። በሄደበት ካስቀረነው በቂ ነው ብለው የሚያምኑ ናቸው።

አሁን ምንድነው የሆነው... መጨረሻ አካባቢ ውዝግብ ሲሆን ዝርዝር መመሪያ ይወጣልምን ማድረግ እንዳለባቸው የሚገልጽመንግሥቱ ሊወጣ ሲል ይመታል ከዚያ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ይታወጃል፣ መከላከያ ዘመቻ መምሪያ አገሪቱን ይመራል። መግለጫው በዚህ ይነበባል የሚል ዝርዝር ነገር አዘጋጅተው ጠበቁ። አመቺ ጊዜ ነበር የሚጠበቀው። ድንገት ግንቦት 8 ፕሬዝዳንቱ ከአገር እንደሚወጡ ተሰማ። ይሄ የተሰማው ግን ግንቦት 7 ነው። በዚህ ምክንያት በቂ ጊዜ አልነበረም። ጥድፊያ ሆነ።

መንግሥቱ እና የኮሎኔል አጥናፉ ኑዛዜ

ጊዜ አጠረ። አመቺ ጊዜ ሲጠብቅ ተኝቶ ተኝቶ ድንገት ሆነ። ከዚያ በኋላ ነው እንቅስቃሴው ሁሉ የተጀመረው። አሁን ከጊዜ በኋላ አውሮፕላኑ ከተመታ በውጭ ኃይሎች ዘንድ ተቀባይነት ያሳጣል፣ እንኳን አውሮፕላን ተመትቶ ኩዴታ ራሱ ተቀባይነት ያሳጣል፣ ብዙ ንጹሐን ይጎዳሉ፣ ከዚህ ሁሉ ለምን በስደት አናስቀረውም ብለው በተለይ 'ኤርፎርሶች' ናቸው የተቃወሙት።

በኋላ ስብሰባ ላይ አይመታ ሲባል ጄ/ል አበራ ተበሳጭተዋል። ሰውየው ካልተገደለ መፈንቅለ መንግት የለም ብለው ነበር። ሌላው አማራጭ አመራ ማሳረፍ ነበር"ለጄ/ል ደምሴ እንስጠውና እዚያው ትጥቅ ያስፈታው" የሚል ነበር። እዛ ደሞ ችግሩ 2ኛው አብዮተዊ ራዊት የመንግቱ ወዳጅ ነው። በደጋፊዎቻቸው መሀል ይህን ማድረግ ከባድ አደጋ አለው ተባለ።

ስብሰባ ላይ ሲወዛገቡ ቆይተው ኋላ ላይ ጄ/ል ፋንታ "አበራ! አሁን ልንመታው አንችልም፥ ከኢትዮጵያ አየር ክልል ወጥቷል። ቀይ ባርን እያቋረጠነው" ብለው ነገሩን ደመደሙት።

2. ጄ/ል ቁምላቸው ደጀኔ በምን ተአምር ከአገር ሊወጡ ቻሉ?

በጄ/ል ደምሴ ቡልቶ ትእዛዝ ከአሥመራ የአየር ወለድ ጦር በአንቶኖቭ ወደ አዲስ አበባ ጭነው የመጡት ጄ/ል ቁምላቸው ነበሩ፡፡ እስከ ምሽት አምስት ሰዓት ድረስ ጦራቸውን ይዘው አርሚ አቪየሽን ግቢ ቆዩ፡፡ እነ ጄ/ር መርዕድ ራሳቸውን አጥፍተው ኩዴታው መክሸፉ በሬዲዮ ተነግሮ እንኳን እሳቸው በመከላከያ ቅርብ ርቀት ጎማ ቁጠባና ጤና ጥበቃ አካባቢ ቅኝት ሲያደርጉ ነበር፡፡

ድንገት ግን ሌሊት ላይ ተሰወሩ፡፡ በኋላ አሜሪካ ተገኙ፤ ጄ/ል ቁምላቸው እንዴት ከአገር ወጡ? እንደሚባለው የሲአይኤ እጅ አለበት?

አቶ ደረጄ ደምሴ ቡልቶ፡-

እዚህ አሜሪካን አገር አግኝቻቸው ነበር፡፡ ካንሰር ታመው ነበር፡፡እኔ ያለሁበት ቦስተንም መጥተው መጨረሻ ሰዓአስተምሚያቸዋለሁ፡፡ ብዙ ነገሮችን አጫውተውኛል፡፡ ስለአወጣጣቸው ግን ብዙም ለመናገር ስለማይሹ አልተጫንኳቸውም፡፡ ከሞቱ በኋላ ግን አንድ የአሜሪካ ዜጋ የፌዴራል መረጃ ቋት ላይ የሚገኝን ሰነድ እንዲሰጠው ከጠየቀ እንዲሰጠው በሚያስገድደው ሕግ ተጠቅሜ (*Freedom of Information Act) ይባላል፤ አዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አንድ መረጃ አገኘሁ፡፡ ሰነዱ አንድ ሰው በዚያ ወቀት ሳቸው ስም ኤምባሲውን ጥገኝነት እንደጠየቀ ይገልጻል፡፡ እሳቸው ግን ያንን አልገለጹልኝም፡፡ ‹‹የአገሬው ሰው እያቀባበለ ሸኘኝ›› ነው ያሉኝ፡፡

ሻምበል እዮብ አባተ

ጄ/ል ቁምላቸውን ያገዛቸው የመንግት ባለሥልጣን የሆነ አካል ነው። ያን ሌሊት አንድ ዘመዳቸው የሆነ ፖሊስ ቤት ነው የሄዱት። ሁኔታውን አመቻቸና ወደ ጉራጌ አገር እንድብር እንዲሄዱ አደረገ። በአጋጣሚ ያን ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ የኮንግረስማን ሚኪሊላንድ አውሮፕላን የተከሰከሰበት ጊዜ ነበር። የሚኪሊላንድን አስክሬን ለመፈለግ ከአሜሪካ ብዙ መሪያዎች መጥተዋል ያኔ ይሄን ሽፋን አድርገው የአሜሪካ አየር ኃይል ሰዎች ናቸው በዚያው የወሰዷቸው።

እንዴት? ያልክ እንደሆነ አንድ ቀን ፍለጋ ላይ የተሰማሩ ሁለት የአሜሪካ ተሮች እንድብር ያርፋሉ። ምንድነው ሲባል ነሐሴ ወር ስለነበር ዝናብ ነው፤ አየር ጠባዩ አስቸገረን አሉ እዚያ አረፉ። ሄሊኮፕተሮቹ እዛው ቆሙ፥ አደሩ

የከሸፈው መፈንቅለ መንግሥት ሥዕላዊ መግለጫ

በድብቅ ጄ/ል ቁምላቸውን ወደ ሄሊኮፕተርሳያስገቧቸው አልቀሩም። በማግሥቱ አዲስ አበባ አመጧቸው። ቡድኑ ሥራው ጨርሶ ወደ አሜሪካ ሲመለስ ጄ/ል ቁምላቸውን አሾለኳቸው።

ዋሺንግተን ፖስት ጋዜጣ ኦገስት 15 ፥ 1889 ሄሊኮተሮቹ እንድብር ማረፋቸውን ይገልጻል። እነሱ የሚሉት የአየር ጠባዩ አስቸገረን ነው። በኋላ የኢትዮጵያ ደኅንነት የደረሰበት ግን ቁምላቸውን ለማሾለክ ነበር እዚያ ያረፉት

3. ጄ/ል ፋንታ በላይን ማን 'አስገደላቸው'?

መፈንቅለ መንግሥቱ ሲከሽፍ እንደ ኮንቴይነር በተቀለሰች አንዲት የቆርቆሮ ዛኒጋባ ውስጥ እዚያው መከላከያ ሚኒስቴር ተደብቀው ሦስት ቀን ከሌሊት ጋር ያሳለፉት ጄኔራሉ በመጨረሻ እጅ ሰጡ፡፡ ከዚያም ማዕከላዊ ተወሰዱ፡፡ ከተወሰኑ ወራት በኋላ ድንገት ሊያመልጡ ሲሉ ተገደሉ ተባለ፡፡ እውነት ሊያመልጡ ሲሉ ነው የተገደሉት?

አቶ ደረጀ ደምሴ ቡልቶ፦

ስለርሳቸው ይሄ ነው የሚባል መረጃ የለም፡፡ ከታሰሩ በኋላ ስለ መፈንቅለ መንግሥቱ ዓላማ አንድ ቃለ ምልልስ ሰጥተው ነበር፤ ከኢቴቪ ጋር፡፡ ‹‹መፈንቅለ መንግሥቱን የሞከርነው ማብቂያ የሌለውን ጦርነት ለማቆም ነው›› ነበር ያሉት፡፡ ያኔ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሊያስተላልፈው ባይፈቅድም በኋላ የመንግሥት ለውጥን ተከትሎ ቪዲዮው ወጥቷል፡፡ ምናልባት ያኔ ለጋዜጠች ‹‹ይሄን በል፣ ያንን በል›› ተብለው ይሆናል ለቃለ መጠይቅ የቀረቡት፡፡ እርሳቸው ግን ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርተው እውነቱን ስለተናገሩ ይሆናል ያን ጊዜ ያልተላለፈው፡፡

ስላሟሟታቸው ግን ምንም መረጃ የለም፡፡ አንድ ሰው እንደዚህ ሆነው እንደዚያ ተደርገው ተገደሉ ሲል መረጃውን ከየት እንዳመጣው መናገር አለበት፡፡ ጠባቂያቸውን መትተው ሽጉጥ ነጥቀው ሊያመልጡ ሲሉ ተገደሉ የሚሉ አሉ፡፡ መረጃ አለኝ የሚል ግን የለም፡፡በጣም ብዙ ዓይነት ነገር ነው የሚጻፈው፤ ያለበቂ መረጃ፡፡

ሻምበል እዮብ አባተ

ግልጽ አይደለም። መላምቶቹ ሁለት ናቸው። አንደኛው መላምት የደኅንነት ሚኒስትሩ አስገድለዋቸዋል ነው የሚባለው። ብዙ ምሥጢሮችን ከማውጣታቸው በፊት። ጄ/ል ፋንታ እዛ ከኮንቴይነሩ ውስጥ በተያዙበት ጊዜ ኮ/ል ተስፋዬ ወ/ሥላሴን ፊትለፊት ሲያይዋቿው «ተስፋዬ አከሸፍከው አደል? ተሳካልህ አይደል?» ብለዋቸዋል። ይሄ በቀጥታ ለኮ/ል መንግሥቱ ተነግሯቸዋል።

ሌላው ደግሞ አብዛኛዎቹ የተያዙት ጄኔራሎች የታሰሩት ቤተመንግት ነው። እሳቸው ግን ከመከላከያ እንደተያዙ ወደ ማዕከላዊ ነው የተወሰዱት። ለምን ወደዚያ እንዲሄዱ ተፈለገ? ይሄን የሚነግረኝ አላገኘሁም።

4. የደኅንነቱ ሹም ተስፋዬ ወ/ሥላሴ ሴራው ላይ ነበሩበት?

አቶ ደረጄ ደምሴ ቡልቶ፡-

ኔ አመለካከት ያውቁ ነበር ባይ ነኝ፡፡ ይህንን የምልህ ብልህ ከሆነ ግምት (Educated guess) በመነሳት ነው፡፡ ነገር ግን ልክ አውሮፕላኑ በሰላም ከኢትዮጵያ አየር ክልል መውጣቱን ሲያውቁ አሰላለፋቸውን የቀየሩ ይመስለኛል፡፡

በዚያን ወቅት ሦስት አሰላለፍ ነበር፡፡ መጀመርያው ረድፍ ወይ እሞታለሁ ወይ መፈንቅለ መንግሥቱን አሳካለሁ የሚሉ ናቸው፡፡ ሁለተኛው የኮ/ል መንግሥቱ ታማኝ ሆኜ እጸናለሁ የሚል ነው፡፡ ሦስተኛው የኮ/ል መንግሥቱ መውረድ መቶ በመቶ ከተረጋገጠ መፈንቅለ መንግሥቱእደግፋለሁ፤ እስከዚያው ግን ለማንም ሳልወግን እቆያለሁ የሚል ቡድን ነው፡፡ የደኅንነት ሹሙ በዚህ ጎራ የተሰለፉ ነበሩ ብዬ አምናለሁ፡፡

አባቴ ግን ሰውዬውን ድሮም አያምነውም ነበር፡፡ አንድ ጊዜ አባቴ ታሞ ደኅንነቱ ተስፋዬ ሊጠይቀው መጥቶ ኮ/ል መንግሥቱን ያማለታል፡፡

‹‹…ሰውዬው አብዷል፤ ምን ማድረግ እንደሚቻል ግራ ገብቶናል፡፡ የምንሰጠውን ምክር ሁሉ አይቀበልም…›› እያለ ስለ ኮ/ል መንግሥቱ አስቸጋሪነት ይተርክለታል፡፡

አባቴ ለምን እሱ ፊት እንደዛ እንደሚናገር ተደንቆ ሲያወራ ሰምቼዋለሁ፡፡ ‹‹ እንዴ! እሱ ሰላይ ነው፡፡ እንደዛ ሊቀመንበሩን ሲያማልኝ እኔ ምን እንድለው ፈልጎ ነው?›› እያለ ሲገረምበት ነበር፡፡ ይህ አጋጣሚ ከመፈንቅለ መንግሥቱ አንድ ዓመት በፊት የሆነ ነው፡፡

ሻምበል እዮብ አባተ

ኬጂቢ ስለ መፈቅለ መንግሥቱመረጃ ነበረው። ነገር ግን መረጃውን እንዴት እንዳገኘ ማንም አያውቅም። ለኬጂቢ የሚሠሩ ኢትዮጵያዊያን እንዳሉ ግምት ተሰጥቷል።

በወታደራዊ ደህንነት ውስጥ ዋናው ሥራ ጄኔራሎችን መከታተል ነው። ሴራው ሲጎነጎን ኮ/ል ተስፋዬ አያውቁም ማለት ይከብዳል። ጄኔራሎቹም ቢሆን አንዳንድ ጊዜ በመዝናኛ ቦታ ዘብረቅ ማድረጋቸው አልቀረም። የቢሮና የቤት ስልካቸውን ያዳምጣሉ። ፕሬዝዳንቱ ደግሞ ቁጡ ናቸው። ጄኔራሎቹን በሚቆጡበት መጠን ኮ/ል ተስፋዬንም ይቆጧቸዋል። ተስፋዬ ወ/ሥላሴ ከሚችሉት በላይ ጫና ነበረባቸው። ተሰላችተዋል።

ጄኔራሎቹም እያለሳለሱ ዕቅዳቸውን ጠቆም ሳያደርጓቸው አልቀረም። "ፕሬዝዳንቱ ሊያምነን አልቻለም ውደቀት ይመጣል። ብስለት የሌላቸውን የካድሬዎችሪፖርት እያዳመጠ እኛን ጠላን" እያሉ አሳማኝ ማስረጃ ይነግሯቸው ነበር። ደኅንነቱ ተስፋዬ ሐሳባቸውን አላጣጣሉም። እንደ ደኀንነት ሰው በአንድ ጊዜ አልተቃወሙም። "እስኪ ነገሩን እናጥናው፥ እናንተም እስኪ አስቡበት" እያሉ ቀርበዋቸዋል።

ደኅንነቱ ኮ/ል ተስፋዬ በበኩላቸው"ፕሬዝዳንቱ ከሥልጣን እንዲወገዱ ፍላጎት ነበረኝ። ነገር ግን በነዚህ ጄኔራሎች አገሪቱ እንድትመራ አልፈልግም ነበር ብለው ተናግረዋል" ከለውጥ በኋላ እስር ቤት ሳሉ።

እንደምገምተው ተስፋዬ ለጄኔራሎቹ ትንሽ 'ግሪን ላይት'(ይሁንታ) ሰጥተዋቸዋል። ያንን ይዘው ይመስለኛል ጄኔራሎቹ ሙከራ ያደረጉት። በኋላ ላይ ግን እየራቁ የመጡ ይመስለኛል።

5. ጄ/ል አበራ አበበ መከላከያ ሚኒስትሩን ለምን ገድለው ጠፉ?

የመፈንቅለ መንግሥቱን አቅጣጫ ከቀየሩት ኩነቶች አንዱና ዋንኛው ጄኔራል አበራ የመከላከያ ሚኒስትሩን ጄኔራል ኃይለጊዮርጊስን እዚያው መከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ ገድለው መሰወራቸው ነው፡፡

የ‹‹ነበር›› መጽሐፍ ደራሲ ዘነበ ፈለቀ "ጄ/ል አበራ ‹‹አብዮት›› እያካሄዱ መሆናቸውን ዘንግተው እንደ ተራ ነፍሰ ገዳይ እግሬ አውጪኝ ማለታቸው የሚያስገርም ነው" ይላል፡፡ ተገቢ ትዝብት ይመስላል።

መጀመሪያውንስ መከላከያ ሚኒስትሩን ለምን ገደሏቸው? ምን ለማትረፍ? ጄኔራል አበራ መፈንቅለ መንግሥቱን የማስተባበር በርካታ ኃላፊነቶች እያሉባቸው እንዴት ይህን ድርጊት ፈጽመው ሸሹ?

አቶ ደረጄ ደምሴ ቡልቶ፡-

ጄኔራል አበራ የኩዴታው ዘመቻ ኃላፊ ናቸው፡፡ ከፍተኛ የጦር መሪ ናቸው፡፡ ብዙ ጀብዱ የፈጸሙ ናቸው፡፡ ለምን ያን እንዳደረጉ ግልጽ አይደለም። ይሄን የሚመልስ ሰው የለም፡፡ አሁን ብዙ የደርግ ካድሬዎች ዝም ብለው ቁንጽል ነገር ይዘው በመሰለኝ መጽሐፍ ይጽፋሉ፡፡ ሀቁ ግን ይህን የሚነግረን አንድም ወሬ ነጋሪ አለመቅረቱ ነው፡፡

የግል ግምቴን ከሆነ የጠየቅከኝ ያን ልነገርህ እችላለሁ፡፡

እንደሚመስለኝ ጄኔራል አበራ ይመጣል የተባለው ጦር እንደማይመጣ ሲያውቁ፣ ሊከበቡ እንደሚችሉ ሲያውቁ የሚደግፋቸው ጦር እንደሌለ ሲያውቁ መሰለኝ የወጡት። የርሳቸው መውጣት ደግሞ ሁሉንም ነገር አመሰቃቀለ። ምክንያቱም ጄኔራል ቁምላቸው ያን ጦር ይዘው ተነጋገር የተባሉት ከጄኔራል አበራ ጋር ነበር። ጄ/ል አበራ ደግሞ ምናልባት ያ ጦር ካልመጣ ነገሩ ተበላሽል ብለው ያሰቡ ይመስላል፡፡

ሻምበል እዮብ አባተ

ጄ/ል አበራ መፈንቅለ መንግሥቱ ሂደት ላይ እያለ «ጊዜ ያስፈልገናል ጥናት እናድርግ» ይሉ ነበር። ቶሎ እናድርግ በሚለው ቡድን ተረቱ። መፈንቅለ መንግቱ ቶሎ እናድርግ የሚለው ቡድን ጦርነቱ ከተሸነፍን [ከሻቢያ ጋር]የመደራደር አቅማችን ይቀንሳል የሚል መከራከሪያን ይዟል።

ስብሰባው እየተካሄደም ቢሆን ገባ ወጣ ይሉ ነበር። በዚህ ጊዜ የመከላከያ ሚኒስሩ ጄ/ል ኃይለጊዮርጊስ ይመጣሉ። የሳቸው ል ረዳት በር ላይ ያገቸዋል። «ጌታዬ አይግቡርሶ ጥሩ አይደለም። ይመለሱ» ይላቸዋል ስለሚወዳቸው። በመደናገጥ ተመልሰው ይሄዳሉ።

ወጣ ገባ የሚሉት ጄ/ል አበራ ይለጊዮርጊስ መጥቶ ሄደ ሲባሉ አበዱራሳቸውን እስከመሳት ደረሱ። አሁን እሱ ሄዶ እዚህ የሚሆነውን ካወቀ ቀጥሎ በታንክ መከበባችን ነው አሉ። አሁን መደናገጥ መጣ። ጸረ መፈንቅለ መንግቱን የሚመሩት ደግሞ ሌላ ትልቅ ስህተት ሩ። በድጋሚ ሚኒስትሩን ወደ መከላከያ ግቢ ይልኳቸዋል።

ስብሰባውን ይበትኑ ተብለውበድጋሚ መጡ። ሲመጡ ከጄ/ል አበራ ጋር ይገጣጠማሉ። ልክ እሳቸው ደረጃውን ሲወጡ፣ አበራ ደረጃውን ሲወርድ ተገናኙ። በሁለት ጥይት መቷቸው። ጄ/ል አበራ የታንክ ድምጽ ሰምተዋል። በልዩ ጥበቃ ብርጌድ ከተከበቡ በኋላ ምንም ማድረግ እንደማይችሉ አውቀዋል። ስለዚህ ተስፋ መቁረጥ አለ። ያ ይመስለኛል ለዚህ ውሳኔ ያበቃቸው።

አየር ወለድ ስለነበሩ የመከላከያ አጥርን ዘለው ሲቪል ሰዎች የሚኖሩበት ግቢ ገብተው ካፖርት ቢጤ ለብሰ ነው ያመለጡት። ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ጉለሌ በተደበቁበት ተከበው ሊያመልጡ ሲሉ ግንባራቸውን ተመተው ተገደሉ።

ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ሁለት ነገር ቆጭቷቸዋልአንዱ የቁምላቸው ማምለጥ ሲሆን አንዱ ደግሞ የጄ/ል አበራ በሕይወት አለመያዝ ነው።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ