የሚያስወርዱ ሴቶች ቁጥር ከሚወልዱ ሴቶች የሚበልጥባት ሀገር

አሻንጉሊቶች Image copyright PAARISA

የ19 ዓመቷ ፒያ፤ ግሪንላንድ ውስጥ ከቤተሰቦቿ ጋር ነው የምትኖረው። ጽንስ ስለማስወረድ ከጓደኞቿና ከቤተሰቦቿ ጋር በነጻነት እንደምታወራ ትናገራለች። ለመጨረሻ ጊዜ ጽንስ ያስወረደች ጊዜም ለቤተሰቦቿ ነግራቸዋል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት አምስት ጊዜ ጽንስ አስወርዳለች።

''ብዙ ጊዜ እርግዝና መከላከያ እጠቀማለሁ፤ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ እዘነጋዋለሁ። በአሁኑ ሰአት ልጅ መውለድ አልፈልግም። የምገኘው በትምህርቴ የመጨረሻ ዓመት ላይ ነው።'' ትላለች ፒያ።

ከተለያየ አባት የተወለዱት መንትዮች

ብቻቸውን ወደ መዝናኛ ስፍራ የሚሄዱ ሴቶች ፈተና

ከአውሮፓውያኑ 2013 ጀምሮ ግሪንላንድ ውስጥ በየዓመቱ 700 ህጸናት የሚወለዱ ሲሆን፤ በሚያስገርም ሁኔታ በየዓመቱ 800 ጽንስ ማቋረጦች ይደረጋሉ። ግሪንላንድ ውስጥ የጽንስ ማቋረጥ ቁጥር ለምን ይህን ያህል ከፍ አለ?

ግሪንላንድ የዓለም ትልቋ ደሴት ስትሆን፤ በሀገሪቱ ስታትስቲክስ ቢሮ መረጃ መሰረት በደሴቷ የሚኖሩት 55 ሺ 992 ሰዎች ብቻ ናቸው።

በሃገሪቱ ከሚያረግዙ ሴቶች መካከል ግማሾቹ ጽንስ ያቋርጣሉ። ይህ ደግሞ ከ1000 ሴት 30 የሚሆኑት እርግዛናቸውን ያቋርጣሉ እንደማለት ነው።

በብዙ ሃገራት ጽንስ ማቋረጥ ነጻና በሕግ የሚፈቀድ ሆኖ እንኳን ጽንስ ማቋረጥ የሚፈልጉ ሴቶች ከባድ መገለል ስለሚደርስባቸው ብዙ ጊዜ ተደብቀው ነው የሚፈጽሙት። ግሪንላንድ ውስጥ ግን ሴቶች ጽንስ ስለማቋረጥ ብዙም ጭንቀት አይገባቸውም።

ሴቶች በሰሜን ኮሪያ ሠራዊት ውስጥ

የጽንስ ማቋርጥ ቀን

''ብዙዎቹ ጓደኞቼ ከዚህ በፊት ጽንስ አቋርጠው ያውቃሉ። እናቴ እንኳን እኔና ወንድሜን ከመውለዷ በፊት ሦስት ጊዜ ጽንስ አቋርጣ ነበር'' ትላለች የ19 ዓመቷ ፒያ።

በዋና ከተማዋ ኑክ የሚኖሩ ሴት ተማሪዎች ረቡዕ ዕለት ወደ ስነ ተዋልዶ ክሊኒኮች እየሄዱ ጽንስ የማስወረድ ልማድ አላቸው። ዕለቱንም ''ጽንስ የማቋረጥ ቀን'' ብለው ይጠሩታል።

ግሪንላንድ ውስጥ ክርክሩ ጽንስ ማቋረጥ መከልከል አለበት ወይስ የለበትም በሚለው ሳይሆን ከትዳር በፊት ግብረ ስጋ ግንኙነት ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነው።

Image copyright Media for Medical
አጭር የምስል መግለጫ ግሪንላንድ ውስጥ የወሊድ መከላከያዎች በነጻ ቢቀርቡም ሴቶች ብዙ ጊዜ አይጠቀሟቸውም

የዓለማችን ሃብታም ሴቶች

ስቲና ብሪኖይ ግሪንላንድ ውስጥ የወሊድ ነርስ ነች። ባለፉት ዓመታት ለምን በተደጋጋሚ የጽንስ ማቋረጥ እንደሚደጋገም ስታጠና ነበር።

እሷ እንደምትለው፤ ወዶችም ሆነ ሴቶች በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት መከላከያ አይጠቀሙም። ምክንያቱ ደግሞ አብዛኛዎቹ አልኮል ስለሚጠጡ ነው።

''ካነጋገርኳቸው ታካሚዎች መካከል 50 በመቶ የሚሆኑት ስለወሊድ መከላከያ እውቀቱ እንዳለቸው ነግረውኛል፤ ነገር ግን 85 በመቶ የሚሆኑት መጠቀም አይፈልጉም አልያም በትክክል አይጠቀሙትም'' በማለት ሁኔታውን ታስረዳለች።