አርኖልድ ሸዋዚንገር በደቡብ አፍሪካ ጥቃት ተሰነዘረበት

አሜሪካዊው ታዋቂ ተዋናይና የካሊፎርኒያ ግዛት አስተዳዳሪ አርኖልድ ሸዋዚንገር በክላሲክ አፍሪካ ዝግጅት ላይ Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ሸዋዚንገር አድናቂዎቹ በእሱ ላይ የደረሰውን ጥቃት ሳይሆን ስፖርታዊ ክንውኑ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ አሳስቧል

እውቁ አሜሪካዊ ተዋናይና የካሊፎርኒያ ግዛት የቀድሞ አገረ ገዢ አርኖልድ ሸዋዚንገር በደቡብ አፍሪካ አንድ ዝግጅት ላይ ጥቃት እንደተሰነዘረበት የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በስፋት እየተሰራጨ ነው።

ግብፃዊቷ ተዋናይት በአለባበሷ ተከሰሰች

የ71 ዓመቱ የካሊፎርኒያ የቀድሞ አገረ ገዢ አርኖልድ ሸዋዚንገር ጥቃቱ የተሰነዘረበት በደቡብ አፍሪካ 'አርኖልድ ክላሲክ' ስፖርታዊ ዝግጅት ላይ ከአድናቂዎቹ ጋር እየተዋወቀና እያወራ በነበረበት ወቅት ነው።

እውቁ ተዋናይ አድናቂዎቹ በትዊተር ገጻቸውና ስለ እርሱ መጨነቃቸውን በመግለፃቸው አመስግኖ "የሚያስጨንቃችሁ ምንም ነገር የለም" ብሏል።

ሸዋዚንገር በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ በተካሄደው ዝግጅት ላይ ከአድናቂዎቹ ጋር ፎቶ በመነሳት ላይ ሳለ ነበር ድንገት ከኋላው ጥቃት የተሰነዘረበት ይህንን የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስልም በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት ተሰራጭቷል።

የአሜሪካው ፅንስ ማቋረጥ ሕግ ሆሊውድን አስቆጣ

'ዘ ተርሚኔተር' የተሰኘው ፊልም ዋነኛ ተዋናይ ጥቃቱ ሲሰዘነዘርበት ተንገዳግዶ ወደኋላ ሲዞር፤ ጥቃት ፈፃሚው መሬት ላይ ሊወድቅ ችሏል። ከዚያም ወዲያውኑ በፀጥታ አስከባሪዎች መያዙንና በኋላም ለፖሊስ ተላልፎ እንደተሰጠ የዝግጅቱ አስተባባሪዎች ገልፀዋል።

ሸዋዚንገር ከአራት ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ባለው የትዊተር ገፁ ላይ "ብዙ ጊዜ እንደሚያጋጥመው በሰዎች መጨናነቅ የተገፋሁ ነበር የመሰለኝ፤ ጥቃት እንደደረሰብኝ ያወቅኩት እንደ እናንተ ተንቀሳቃሽ ምስሉን ስመለከት ነው" ሲል አስፍሯል።

በመጨረሻም አድናቂዎቹ በዝግጅቱ ላይ ስለሚኖረው ስፖርታዊ ክንውን እንጂ ጥቃቱ ላይ ትኩረት እንዳያደርጉ አሳስቧል።

"በደቡብ አፍሪካ ውስጥ በሚዘጋጀው 'አርኖልድ ስፖርት' 90 የሚሆኑ ስፖርታዊ ክንውኖች ይካሄዳሉ፤ የሚያስደንቅ ተሰጥኦ ያላቸውና በሁሉም የዕድሜ ክልል የሚገኙ 24 ሺህ ስፖርተኞችም ይሳተፉበታል፤ እንደግፋቸው" ሲልም በትዊተር ገፁ ላይ መልዕክት አስተላልፏል።

'አርኖልድ ክላሲክ አፍሪካ' ዝግጅት በየዓመቱ ግንቦት ወር ላይ የሚካሄድ ሲሆን የሰውነት ግንባታና ሌሎች ስፖርታዊ ውድድሮች ይካሄዱበታል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ