የሰሜን ኮሪያ ሴቶች ለወሲብ ንግድ ወደ ቻይና ይወሰዳሉ

በሻንጋይ በወሲብ ንግድ የሚተዳደሩ ሴቶች Image copyright Korea Future Initiative

በሺዎች የሚቆጠሩ ሰሜን ኮሪያውያን ሴቶችና ልጃገረዶች በቻይና የወሲብ ንግድ ላይ እንዲሰማሩ ጫና እየተደረገባቸው ነው ሲል ተቀማጭነቱን ለንደን ያደረገው የመብት ተሟጋች በጥናቱ አስታውቋል።

ለወሲብ ትክክለኛው ዕድሜ የቱ ነው?

በአብዛኛው ሰሜን ኮሪያውያን ሴቶች በወሲብ ንግድ እንዲተዳዳሩ ተጠልፈውና ተሸጠው፣ አሊያም ቻይናዊ ወንድ እንዲያገቡ ተደርገው ይወሰዳሉ ሲል ኮሪያ ፊዩቸር ኢንሸቲቭ የተባለ ድርጅት ገልጿል።

ሪፖርቱ እንደሚለው የወሲብ ንግዱ በወንጀል ሥራ ላይ ለተሰማሩት ድርጅቶች በዓመት 100 ሚሊየን ዶላር ገቢ ያስገኝላቸዋል።

እነዚህ ሴቶች በአብዛኛው ቻይና ሰሜን ኮሪያውያንን ለሥራ ስለምታስመጣ ወጥመድ ውስጥ ይገባሉ። ከዚያም የቤት ውስጥ ጥቃት ይደርስባቸዋል፤ ይሰቃያሉ።

ተጠቂዎቹ ሴቶች በጣም አነስተኛ የሆነ ገንዘብ የሚከፈላቸው ሲሆን በአማካይ 30 የቻይና የን ወይም 4.30 ዶላር (120 ብር ገደማ) ይከፈላቸዋል፤ ለሚስትነት የሚሸጡት ደግሞ ቢያንስ 1ሺህ እስከ 50 ሺህ የን ይከፈላቸዋል።

እነዚህ ሴቶች በአብዛኛው የሚሸጡት ወደ ገጠር አካባቢ ሲሆን በባሎቻቸው ይደፈራሉ፤ ጥቃትም ይፈፀምባቸዋል።

'የሴቶች ቫያግራ' በአፍሪካዊቷ ሃገር

ይህ ብቻም ሳይሆን በመረጃ መረብ ላይ ምስላቸውን በመጫን ለዓለም የበይነ መረብ ተጠቃሚዎች ተጋልጠው ይሰጣሉ ይላሉ የዚህ ሪፖርት ፀሐፊ ኦን ሂ ሱን።

ሴቶቹ በበይነ መረብ የወሲብ ኢንዱስትሪ ወሲብ እንዲፈፅሙ ይደረጋሉ፤ በካሜራ ፊትም የወሲብ ጥቃት ይፈፀምባቸዋል። ይህንን ምስል የሚያዩት አብዛኞቹ ሰሜን ኮሪያውያን እንደሆኑ ይገመታል።

አብዛኞቹ ልጃገረዶችና ሴቶች ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 29 የሚደርስ ሲሆን አንዳንዴ ከ9 ዓመት ዕድሜ ያነሱ ሴቶችም እንደሚላኩ ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል።

ሪፖርቱ አክሎም ሴቶቹ ከቻይና ተታልለው፣ ተሸጠው አሊያም ተጠልፈው ይወሰዳሉ። በቀጥታም ከሰሜን ኮሪያ ተጓጉዘው የሚሄዱም አሉ። አብዛኞቹ ከአንድ ጊዜ በላይ የተሸጡ ሲሆን ቤታቸውን ለቅቀው ከወጡ በዓመት ውስጥ ቢያንስ በአንድ የንግዱ ዘርፍ የወሲብ ባሪያ እንዲሆኑ ይገደዳሉ።

አብዛኛዎቹ የወሲብ ንግዱን እንዲሰሩ የሚደረጉት በርካታ ስደተኞች በሚኖሩባት ሰሜን ምስራቅ ቻይና በሚገኙ የወሲብ ንግድ የሚካሄድባቸው ቤቶች ነው።

ፌስ ቡክ በፓፓዋ ኒው ጊኒ ለአንድ ወር ሊታገድ ነው

የአጥኝዎቹ ቡድን ይህንን መረጃ የሰበሰበው ጥቃቱ ከደረሰባቸውና ተመልሰው ወደ ሰሜን ኮሪያ ካቀኑት ሴቶች ሲሆን በሰሜን ኮሪያ ቾንግጅን ከተማ ነዋሪ ሆነችው ዮን "እኔ የተሸጥኩት ከሌሎች ስድስት ሰሜን ኮሪያውያን ጋር ሲሆን በአንድ ሆቴል ውስጥ እንዲንቆይ ተደረግን፤ ምግብ አይሰጠንም ነበር፤ ስምንት ወራትን በአስቸጋሪ ሁኔታ ካለፍን በኋላ ግማሾቻችን በድጋሜ ተሸጥን" ትላለች።

በደላላውም በጣም አስከፊ ጥቃቶች ሲፈፀሙባት እንደነበር የምትናገረው ዮን "ደላላው ይደበድበን ስለነበር በሌላ ከተማ ስደርስም የቆዳዬ ቀለም እየተለወጠ መጣ ፤ ሌሎች የደላላ ቡድኖችም እግራችንን በስለት ይቆራርጡን ነበር" ስትል የደረሰባትን ተናግራለች።

ሌላኛዋ ሴት ኪም ደግሞ " በቻይና ዳሊያን በርካታ ሰሜን ኮሪያውያን አሉ፤ በሆቴል የበር ቀዳዳም የአድራሻ ካርድ እናስቀምጣለን፤ ካርዱ በኮሪያ ቋንቋ የተፃፈ ሲሆን የምንሰጠው አገልግሎት ይፃፍበታል። በአብዛኛው ወደ መጠጥ ቤቶች ነው የሚወስዱን" ብላለች።

"የደቡብ ኮሪያ ድርጅቶች ለሠራተኞቻቸው የሰሜን ኮሪያን የወሲብ ባሪያዎችን ይፈልጋሉ፤ የወሲብ ንግድን የተለማመድኩት አንድ ደቡብ ኮሪያዊ ሰው ጋር ነው" ስትል መራሩን ተሞክሮዋን አጋርታለች።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ