ኤምአርአይ ምንድነው?

Cancer scan Image copyright skynesher/Getty Images

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተወሳሰቡና ቀደም ሲል ለመለየት እጅግ አስቸጋሪ የነበሩ በሽታዎችንና የሰውነት እክሎችን ለመለየት 'ኤምአርአይ' የተባለ የህክምና መሳሪያ በጥቅም ላይ መዋል ጀምሯል።

ኤምአርአይ በራዲዮዌቭና በማግኔት የሚሰራ ለህክምና አገልግሎት የሚውል ማሽን ነው። ማሽኑም በሰውነታችን ውስጥ ያለውን በሽታ በቀላሉና በጠራ መልኩ የሚያሳይ የህክምና መሳሪያ ነው።

በርካቶች ከምጥ ይልቅ በቀዶ ህክምና መውለድን እየመረጡ ነው

ይህም ደግሞ የጎንዮሽ ጉዳት በሌለው መልኩና በቀላል መንገድ በሽታውን ለመለየት የሚያግዝ እንደሆነ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ራዲዮሎጂስት የሆኑት ዶክተር ሳምሶን አሽኔ ይናገራሉ።

በዚህ ምክንያት ከሌሎች ለህክምና አገልግሎት ከሚውሉ ማሽኖች የተሻለ ነው። በህክምና ዘርፉ ውስጥ በሽታዎችን በቀላሉ በመመርመርና በማወቅ ሂደት ውስጥ ያሉ ግድፈቶችን ለማቃለልም ከፍተኛ ሚና እንዳለው ባለሙያው ያብራራሉ።

የሚያስወርዱ ሴቶች ቁጥር ከሚወልዱ ሴቶች የሚበልጥባት ሀገር

ማሽኑ ትልልቅ በማግኔት የሚሰሩ ቱቦዎች ያሉት ሲሆን የህክምና ባለሙያዎች በአይናቸው ሊያዩዋቸው የማይችሏቸውን የሰውነታችንን ክፍሎችና በሽታዎችን በቀላሉ ለመለየት ያግዛል።

ኤምአርአይን ለምን አይነት ምርመራዎች እንጠቀምበታለን?

መሳሪያው ገና ለብዙ ዓመታት ጥቅም ላይ አለመዋሉን በዚሁ ዙሪያ ብዙ ምርምሮች እየተደረጉ ስለሆነ ለወደፊቱ አሁን እየሰጠው ካለው አገልግሎት በላቀ መልኩ ጥቅም ላይ እንደሚውል ዶክተር ሳምሶን ጠቅሰዋል።

አሁን ባለበት ደረጃ ግን ኤምአርአይ በአጠቃይ ለአንጎል ችግሮች፣ የአከርካሪ አጥንት፣ ሆድ፣ ካንሰር እንዲሁም ለመገጣጠሚያ በሽታዎችና ሌሎችም ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን የዘመኑ እጅግ ጠቃሚ መሳሪያ ነው።

ወንዶች የማያወሯቸው አምስት አሳሳቢ ነገሮች

በተለይ ደግሞ በአንጎል ውስጥ የሚገኙ ችግሮችንም ሆነ እጢዎች ለመለየት ለዘመናት ትልቅ ችግር ነበር የሚሉት ባለሙያው፤ ከዚህ በፊት ሲቲ ስካን የሚባል መሳሪያ በጥቅም ላይ ይውል ነበር።

ሲቲ ስካንን ተከትሎ ደግሞ ኤምአርአይ መጣ።

''ይህ መሳሪያ ለምሳሌ አንጎልን ብንወስድ በመጀመሪያ አንጎላችን ውስጥ እጢ አለ ወይስ የለም? የሚለውን ይነግረናል። ከዚህ ባለፈም እጢው ምን አይነት ባህሪዎች አሉት? ይዘቱ ምንድን ነው? እንዲሁም ህክምናው ምን መሆን አለበት የሚሉት ጥያቄዎች ለመመለስ በእጅጉ ይረዳል'' ይላሉ ዶክተር ሳምሶን።

''ተገቢው ህክምና ከተደረገ በኋላ እንኳን ህክምናው ውጤታማ ነበር ወይ? የሚለውን ለማወቅ ይህ መሳሪያ እጅግ ጠቃሚ ነው። ''

በኤምአርአይና በሲቲስካን መካከል ያለውን ልዩነት ሲያስረዱ ባለሙያው ሲቲስካን በሽታዎችንና የሰውነት ክፍሎቻችን ላይ የተፈጠሩ ችግሮችን ለመለየት ጨረር የሚጠቀም ስለሆነ ብዙ ጊዜ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል ብለዋል።

ከ27 ዓመታት በኋላ ከ'ኮማ' የነቃችው ሴት

የሲቲስካን ምርመራ በሚደረግበት ወቅት በተለይ ህጻነት ለከፍተኛ ጨረር እንዳይጋለጡ ጥንቃቄ መደረግ አለበት።

''ኤምአርአይ ግን ለምርመራው የማግኔት ኃይልን ስለሚጠቀም የጎንዮሽ ጉዳት የለውም። ምናልባት ታካሚዎች በሰውነታቸው ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች ብረት ነክ መሳሪያዎች ካሉ ግን በጣም ከባድ ነው። እኛም ብንሆን ምርመራው ከመደረጉ በፊት ተገቢውን ማጣራት አካሂደን ነው ወደ ኤምአርአይ የምንመራው።''

ከዚህ በተጨማሪ በሰውነታችን ውስጥ ያለውን ነገር ጥርት አግርጎ ከማሳየት አንጻር ኤምአርአይ የተሻለ ነው። እንደውም ባለሙያው የሲቲስካንና ኤምአርአይ ልዩነትን ለማስረዳት በድሮና ዘመን አመጣሽ ካሜራዎች መካከል ያለውን ይጠቅሳሉ።

ኤምአርአይ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ቦታዎችን ጥርት ባለና ለውሳኔ በሚቀል መልኩ የሚያቀርብ ሲሆን ሲቲስካን ግን የምስሎቹ ጥራት ከኤምአርአይ ጋር ሲወዳደር በጣም ዝቅተና ነው።

ጫት የአእምሮ ጤናን እንደሚጎዳ ጥናት አመለከተ

ነገር ግን ይላሉ ባለሙያው፤ ''ሁሉም ኤምአርአይ መሳሪያዎች እኩል የሆነ አገልግሎት የላቸውም። በውስጣቸው ባለው የማግኔት ቱቦ መጠንና የማጉላት አቅም መሰረት ሁሉም የየራሳቸው አይነት ጥቅምና አሰራር አላቸው።''

በሌሎች አጋጣሚዎች ግን ሲቲስካን የሚመረጥበት ጊዜ እንዳለ ዶክተር ሳምሶን ያስረዳሉ።

ለምሳሌ ድንገተኛ አደጋዎች ሲያጋጥሙና ታካሚዎች አስቸኳይ ምርመራ ሲያስፈልጋቸው ሲቲስካን ተመራጭ ነው። ምክንያቱም ሲቲስካን በፍጥነት ውጤቱን ያደርሳል። ኤምአርአይ ግን በትንሹ 30 ደቂቃ ሊፈጅ ይችላል።