በጉጂ አስር ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

ጎሮ ዶላ ወረዳ Image copyright Google Map

በደቡብ ኦሮሚያ ጉጂ ዞን ግንቦት 12/2011 ዓ. ም. አስር ሰዎች በአንድ ቦታ መገደላቸው ተገለጸ። ግድያው ጎሮ ዶላ ወረዳ ውስጥ እንደተፈጸመ የዞኑ ኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ ዮሃንስ ኦልኮዮ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

ታጣቂዎች ተደብቀው የሽምቅ ውጊያ ሲያደርጉ እንደነበረ የተገለጸ ሲሆን፤ አንድ የመከላከያ ኃይል አባል መግደላቸውንም አቶ ዮሃንስ አረጋግጠዋል። በዚህ ምክንያት የመከላከያ ኃይሉ ራሱን ለመከላከል በወሰደው እርምጃ 10 ታጣቂዎች ስለመገደላቸው ከአካባቢው መረጃ እንደደረሳቸው ኃላፊው አክለዋል።

የስኳር ፋብሪካዎችን ለግል ባለሃብቶች የመስጠት ፋይዳና ፈተናዎቹ

ጋዜጠኞች ስለ ለውጡ ማግስት ሚዲያ ምን ይላሉ?

የመስጠም አደጋ የተጋረጠባት ዋና ከተማ ልትቀየር ነው

የታጣቂዎቹን ማንንት በተመለከተ ቢቢሲ ላቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ዮሃንስ ሲመልሱ፤ '' ከሕዝቡ እንደሰማሁት ከሆነ የኦነግ ታጣቂዎች ናቸው'' ብለዋል።

እነዚህ የኦነግ ታጣቂዎች የሲቪል ልብስ በመልበስ በአካባቢው ሲንቀሳቀሱ የነበረ ሲሆን፤ በአካባቢው ሰላም ለማስጠበቅ የተመደበው የመከላከያ ኃይል ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈጽመዋል ብለዋል።

ኃላፊው እንዳሉት፤ ከሰሞኑ ሲወራ እንደነበረው የተገደሉት ሰላማዊ ዜጎች ሳይሆኑ እርምጃ የተወሰደባቸው ታጣቂዎቹ ናቸው። አክለውም መከላከያ በቂም በቀል ሕዝቡ ላይ ተኩስ ከፍቶ ሕይወት አጥፍቷል የሚባለው ከእውነት የራቀ ነው ብለዋል።

በተኩስ ልውውጡ መሃል ሕይወቱ ያለፈ ሰላማዊ ዜጋ ሊኖር እንደሚችችል ግን አልሸሸጉም። እሱም ማጣራት ያስፈልገዋል ብለዋል።

ተያያዥ ርዕሶች