"ማሰብን የሚፈራ ትውልድ ፈጥረናል"- ቢንያንቫንጋ ዋይናይና

ቢንያቫንጋ ዋይናይና Image copyright SIMON MAINA

"በህይወቴ መኖር የምፈልገው ነፃ በሆነ ምናብ(ሃሳብ) በመመላለስ ነው። በአህጉሪቷ ካሉ ሰዎች ጋር አዳዲስና፤ ሳይንሳዊ የሚያስደስቱ ስራዎችን መስራት እፈልጋለሁ፤ማሰብን የሚፈሩ ትውልድን ፈጥረናል፤ አዲሱ ትውልድ የራሱን ታሪክ የሚፅፍበት፤ አፍሪካውያን የራሳቸውን ሃሳብ የሚያሰርፁበት አህጉርን ማየት እፈልጋለሁ። በተለይም መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች ለደሃው የትኛውንም ፖሊሲን የሚቀርፁት እነሱ ናቸው፤ ሃሳብንም ሆነ ፈጠራን የሚገድሉት እነሱ ናቸው"

ይህ የተወሰደው በትናንትናው ዕለት ህይወቱ ያለፈው ኬንያዊው ፀሀፊ ቢንያቫንጋ ዋይናይና 'ነፃ እሳቤ' ከሚለው ንግግሩ ነው።

"ኢትዮጵያዊ ታሪኮችን ወደ ዓለም አቀፍ የፊልም መድረክ ማምጣት ፈታኝ ነው" ዘረሰናይ መሐሪ

"ገዳ የወደፊቱ የፖለቲካ ስርዓት መሆን ይችላል" ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ

በአፍሪካ ስነ-ፅሁፍ ዘርፍ ከፍተኛ ስፍራ የነበረው ቢንያቫንጋ በቋንቋው ውበት፣ በጠንካራ አቋሙ፣ በድፍረቱና አፍሪካንና ህዝቦቿን ማእከል ባደረገ ፅሁፎቹ ይታወቃል።

ከነዚህም ፅሁፎቹ መካከል 'ዋን ደይ አይ ዊል ራይት አባውት ዚስ ፕሌስ'፣ 'ሃው ቱ ራይት አባውት አፍሪካ' ይገኙበታል።

የምዕራቡ አለም ከአንድ ቢሊዮን በላይ ህዝቦች በላይ የሚኖሩባትን አህጉር በተለይም በፀሃፍያን ዘንድ የምትመሰልበትን መንገድ ሽሙጣዊ በሆነ መልኩ በፃፈበት "ሃው ቱ ራይት አባውት አፍሪካ (ስለ አፍሪካ እንዴት መፃፍ እንችላለን) በሚለው ፅሁፉ ቢንያቫንጋ ዋይናይና

"የመፅሃፋችሁን ሽፋን በየቀኑ የምናገኛቸውን አፍሪካውያንን ፎቶ ሳይሆን ኤኬ 47 ጠመንጃን የተሸከመ፤ የሽምቅ ውጊያ የተራቆቱ ጡቶች፤ የገጠጡ አጥንቶችን አድርጉ" በማለት ምዕራባውያን ስለ አፍሪካ ሲፅፉ በተደጋጋሚ የሚያወጧቸውን ፎቶዎች በማየት በነገር ሸንቆጥ አድርጓቸዋል።

ሙዚቃ ሳይሰሙ መወዛዋዝ ይችላሉ?

ከምዕራባውያን በተጨማሪ መካከለኛ ገቢ ያላቸውን አፍሪካውያን በመተቸት የሚታወቀው ቢንያቫንጋ "አፍሪካን ወደ አውሮፓ መቀየር ይፈልጋሉ፤ የልማት ሞዴላቸው አውሮፓን ሙሉ በሙሉ መኮረጅ ነው፤ ለራሳችን ችግሮች ሀሳብ፣ ፈጠራን ማስተማር አቅቶናል። እንዴት የአፍሪካን ልማት እናመጣለን'

" ሀሳብን ነፃ በማድረግ፤ አህጉሪቷን እንዴት እንድትቀየር እንፈልጋለን፤ ህይወታችንስ? በራሳችን መንገድ ልናስብ ይገባል። እስካሁን የተማርናቸው ነገሮች ለአፍሪካ ምን አመጡላት? እንደገና ልናየው አይገባም?"

በማለት ይጠይቃል። በዚህ ሀሳቡም ከታዋቂው ምሁር ፍራንዝ ፋኖን ጋር ይመሳሰላል፤ ፍራንዝ ፋኖን እንደሚለው የአውሮፓ የስልጣኔ እሴቶች መሰረታቸው ቅኝ ግዛት፣ ባርነት፣ ብዝበዛ ነው፤ አዲስ የሆነ የልማት ሀሳብ ሊኖራት ይገባል።

Image copyright Cynthia Edorh

በአርባ ስምንት አመቱ ህይወቱ ያለፈው ቢንያንጋ ተቃውሞን የማይሸሽ፤ ብቻውን መቆም የማይፈራ ግለሰብ ነበር። ፖለቲካውን በግል ህይወቱ እስከ መጨረሻው ድረስ የኖረ፤ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ወንጀል በሆነባት ኬንያ፣ ስለ ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የፃፈ፤ እንዲሁም በተደጋጋሚ ድፍረት የተሞላባቸውን ንግግሮች ያደርግ የነበረ ነው።

"አደጋውን ስሰማ በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ" የረዳት አብራሪው ጓደኛ

ፀጉሩን ደማቅ ቀለብ ቀብቶ፣ ቀሚስ ለብሶ በአደባባይ ይታይ ነበር። ለምግብ ማብሰል ከፍተኛ ፍቅር የነበረው ቢንያቫንጋ ዋይናይና የቅብ ጓደኞቹ 'አብዛኛውን ጊዜ' ቅመም ቅመም ይሸታል ይሉታል።

የተለየ እሳቤን ለአፍሪካ በተለያየ ፅሁፎች ለማምጣት ከፍተኛ አላማ የነበረው ቢንያቫንጋ ክዋኒ የተባለ የፀሀፊዎች ስብስብን በመመስረት አፍሪካን ማዕከል ያደረጉ፤ የቅኝ ግዛት እሳቤን የጣሱ ፅሁፎን ማሳተም ችሏል።

ቢንያቫንጋ በ2002 የኬን ተሸላሚ የነበረ ሲሆን በ2014 ደግሞ ታይም መፅሔት ከዓለማችን 100 ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች መካከል አንዱአድርጎ አካትቶት ነበር።