በገላን የጋራ መኖሪያ ቤቶች አሰሪዋን በዘነዘና የደበደበችው እየታደነች ነው

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አርማ Image copyright ADDIS ABABA POLICE COMMISION/FB

ከትላንት በስትያ ከሌሊቱ 7 ሰዓት ገደማ በገላን ኮንደሚኒየም አንዲት የቤት ሠራተኛ አሠሪዋና ሓፃናት ልጆቿ ላይ በስለት እና በዘነዘና ጉዳት አድርሣ ተሰውራለች።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሕዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ለቢቢሲ እንደገለፁት የመግደል ሙከራው የተከሰተው ከትናንትና ወዲያ በአቃቂ ክፍለ ከተማ ገላን ኮንደሚኒየም ነው።

የቤት አሰሪዋ የ25 አመት ዕድሜ ያላቸው ቅድስት ሀብቴ ከልጆቿና አሁን ከተጠረጠረችው ሰራተኛ ፅጌ ምናቡ ጋር አብራ ትኖር ነበር።

"አሰሪዋ በተኛኝበት ጭንቅላቷን በዘነዘና በመምታት እንዲሁም የሶስት አመት ህፃን ልጅ በቢላዋ አንገቷንና እንዲሁም የአንድ አመት ጨቅላም በደረሰባት ጉዳት በአፏና በአፍንጫዋ አካባቢ ደም ፈሷታል" ብለዋል።

"የከተማ መስፋፋት የኢትዮጵያን ብዝሀ ሕይወት አደጋ ላይ ጥሏል" ዶ/ር መለሰ ማርዮ

በጉጂ አስር ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

ኬንያዊው ፀሀፊ ቢያንቫንጋ ዋይናይና ሲታወስ

ጉዳቱን ካደረሰች በኋላ የተሰወረች ሲሆን ፖሊስ አለችበት የምትባለው አካባቢ ፍለጋ እያደረገ መሆኑን ነው።

አሰሪዋም ሆነ ልጆቹ ለህይወታቸው የሚያሰጋ ምንም ነገር እንደሌለ ጤናቸው እያገገሙ መሆኑንም ተናግረዋል።

የፀቡ መንስኤ ምን እንደሆነ እስካሁን ድረስ እንዳልታወቀም ምክትል ዳይሬክተሩ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ