ታይላንድ፡ ኢንተርፖል 50 ህጻናትን ከጾታዊ ጥቃት ማዳኑን አሳወቀ

የበይነ መረብ ድረ ገጽ ባለቤት Image copyright Interpol

ጾታዊ ጥቃት ሲፈጸምባቸው በበይነ መረብ ሊተላለፍ ተዘጋጅተው የነበሩ 50 ህጻናት ማዳኑን ኢንተርፖል ገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም ዘጠኝ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል።

አብዛኞቹ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት ታይላንድ ውስጥ ቢሆንም፤ አውስትራሊያና አሜሪካ የሚኖሩ ግለሰቦችም መያዛቸውን ኢንተርፖል አስታውቋል።

የህጻናትን ዘረ መል ማስተካከል ክልክል ነው?

በመላው ዓለም 63 ሺ ተጠቃሚዎች ያሉት ሚስጥራዊ ድረ ገጽ ላይ ምርመራ የተጀመረው በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2017 ሲሆን፤ እስካሁን 100 የሚሆኑ ህጻናት ጥቃት ሲደርስባቸው በድረ ገጹ ተላልፏል ተብሏል።

ኢንተርፖል እንደገለጸው፤ ምርመራው የጀመረው ከ13 ዓመት በታች የሆኑ 11 ህጻናት ወንዶች ላይ ጥቃት ሲፈጸም በሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ምክንያት ነው።

የድረ ገጹ ተጠቃሚዎች ማንነታቸው እንዳይታወቅ የተለያዩ ሶፍትዌሮችን የሚጠቀሙ ሲሆን፤ "ለጊዜው ትኩረታችን የድረ ገጹ አስተዳዳሪዎችና መስራቾች እንጂ ተጠቃሚዎች አይደሉም" ብሏል ኢንተርፖል።

ስለ ወንዶች ፊስቱላ ምን ያህል ያውቃሉ?

ፖሊስ እንዳስታወቀው፤ ጥቃት ፈጻሚዎቹ የምርመራ ሂደቱን ከባድ ለማድረግ የህጻናቱን ፊት በመሸፈን የተለያዩ ምስሎችና ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በየሳምንቱ ለተጠቃሚዎች ያስተላልፋሉ።

ኢንተርፖል ምርመራው የሰመረለት፤ ባለፈው ዓመት የድረ ገጹ አስተዳዳሪ የሆነውን ሞንትሪ ሳላንጋም ታይላንድ ውስጥ እንዲሁም ሩዊቻ ቶክፑትዛ የተባለውን ሌላ የድረ ገጹ አስተዳዳሪ አውስትራሊያ ውስጥ በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ መሆኑን ይፋ አድርጓል።

ምግብ ማብሰልና ማጽዳት የቤት ውስጥ ጥቃቶችን ለመቀነስ

ሞንትሪ ሳላንጋም ባለፈው ዓመት ለፍርድ ቀርቦ የነበረ ሲሆን፤ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ 146 ዓመት ተፈርዶበታል። ሌላኛው በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው ሩዊቻ ቶክፑትዛ ደግሞ 40 ዓመት ተፈርዶበታል።