በቤኒሻንጉል ክልል ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ዋሉ

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰንደቅ አላማ Image copyright Wikipedia

በቅርቡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈጥሮ ለበርካታ ሰዎች ሕይወት መጥፋትና መፈናቀል ምክንያት በነበረው የፀጥታ ችግር የተጠረጠሩ የአካባቢ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ።

የአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት እንደዘገበው በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል የመተከል ዞን የፀጥታ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ፋንቻ አምሳያ እና የግልገል በለስ ከተማ ከንቲባ አቶ ጊሳ ዚፋህ እንደሚገኙበት ተጠቅሷል።

የተጠበቀውን ያህል የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች አልተመለሱም

"ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ተስፋና ስጋት አለ" ኦባንግ ሜቶ

የተጠቀሱት ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር የዋሉት በአካባቢው በተሰማራው የሀገር መከላከያ ሠራዊትና በፌዴራል ፖሊስ አባላት እንደሆነም ተጠቅሷል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፀጥታ ምክር ቤት ትናንት ባወጣው መግለጫ "የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥና በብጥብጡ ውስጥ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የተሳተፉ አካላትን ለሕግ ለማቅረብ" እንደሚሰራና ሕዝቡ ድጋፍ እንዲያደርግለት ጥሪ አድርጎ ነበር።

ቀደም ሲልም ክልሉ መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ተከስቶ ከነበረው ግጭት ጋር ተያይዞ በወንጀል የተጠረጠሩ 33 ግለሰቦችን በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውና ከእነዚህም መካከል አንዱ የክልሉ ፖሊስ አባል መሆኑ ተገልጾ ነበር።

ግጭቱ በተወሰኑ የክልሉ አካባቢዎች ተከስቶ ሞትና መፈናቀልን ካስከተለ በኋላ የመከላከያ ሰራዊትን ጨምሮ የፌደራል ፖሊስ ተሰማርቷል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ