የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለማሻሻያዎች ችኮላ እንደማይገባ ገለፁ

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ Image copyright EDUARDO SOTERAS

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሀገሪቱ ላይ ሊደረጉ ለሚገቡ ዋና ዋና ማሻሻያዎች ችኮላ እንደማይገባ የኤርትራን 28ኛ አመት የነፃነት ክብረ በዓል አስመልክቶ በዛሬው ዕለት ባደረጉት ንግግር ገልፀዋል።

ሁለቱ ሃገራት ጦርነትና ሰላም በሌለበት ሁኔታ ከሁለት አስርት አመታት ፍጥጫ በኋላ በሰላም በመቋጨቱ ማግስት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ፖለቲካዊ ማሻሻያዎችን ሊያውጁ ይችላሉ በሚልም በተለያዩ አገራት በሚኖሩ ኤርትራውያን ዘንድ እየተጠበቁ ነበር።

የኤርትራ 28ኛ ዓመት ነፃነት ከየት ወደየት?

የ "ጥርስ አልባው" ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ?

ታዋቂዎቹ ኤርትራዊያን በሙዚቃቸው ምክንያት ይቅርታ ጠየቁ

በኤርትራ መዲና አስመራ ባደረጉትም ንግግር "ሰላም የሰፈነበት የአዲሱ ዘመን ምኞትና ፍላጎት ፈተናዎቹን ሊጋርዱዋቸው አይገባም" ብለዋል።

በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ሰላም መፈጠሩን ተከትሎ በኤርትራውያን ዘንድ አዲስ የዲሞክራሲ ምዕራፍ ይፈነጥቃል የሚል ተስፋ ቢኖርም ፕሬዚዳንቱ ምንም አይነት ለውጥ አላመጣም በማለት በእምቢተኝነታቸው ቀጥለዋል በሚልም እየተተቹ ነው።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በአዲስ አበባና ሃዋሳ ጉብኝት ያደርጋሉ

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ሃገሪቷን አሁንም ቢሆን ያለ ህገ መንግሥት እየመሩ ሲሆን ብሔራዊ ምክር ቤቱን (ፓርላማ) እንደበተኑት ነው።

የተለያዩ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞችን፣ ጋዜጠኞችንና በዘፈቀደ በማሰር ይከሷቸዋል።

የሁለቱን ሃገራት እርቀ ሰላም ተከትሎ ለአስርት ዓመታት ተዘግተው የነበሩት የሁለቱም አገራት ድንበሮች ቢከፈቱም፤ ከጥቂት ወራት በፊት ምንም አይነት መግለጫ ሳይሰጥ ከኤርትራ በኩል ተዘግተዋል።