የጀርመን አይሁዶች መለያ ቆባቸውን እንዳያደርጉ ተመከሩ

ኪፓህ በአይሁድ ወንዶች የሚደረግ ቆብ Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ኪፓህ በአይሁድ ወንዶች የሚደረግ ቆብ

የጀርመን መንግሥት የፀረ አይሁዳዊነት ኮሚሽነር በሃገሪቱ የሚገኙ አይሁዶች የሃይማኖታቸው መገለጫ የሆነውን ቆብ ከማድረግ እንድቆጠቡ ጠየቁ።

ኮሚሽነሩ ፌሊክስ ክሌን ኪፓህ የሚባለውን መለያ ቆብ አይሁዳዊያን እንዳያደርጉ ያስጠነቀቁት በአንዳንድ የጀርመን ግዛቶች ውስጥ በአይሁዳዊያን ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እየጨመሩ በመምጣታቸው ነው።

ፊደል ያልቆጠሩት ኢትዮጵያዊት የቀዶ ህክምና ባለሙያ

ፌሊክስ ለአንድ ጋዜጣ እንደተናገሩት "ጀርመን ውስጥ አይሁዶች በየትም ቦታና ጊዜ መለያ ቆባቸውን እንዲያደርጉ አልመክርም" ብለዋል።

ባለፈው ዓመት ጀርመን ውስጥ በአይሁዶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን የመንግሥት መረጃ እንደሚያመለክትም ተገልጿል።

በአይሁዶች ላይ የተፈጸሙ የጥላቻ ወንጀሎችን በተመለከተ መንግሥታዊ አሃዞች እንደሚያመለክቱት ባለፈው ዓመት 1646 ጥቃቶች የተፈጸሙ ሲሆን ይህም ቀደም ካለው ዓመት በ10 በመቶ መጨመሩ ተነግሯል።

ማርገዟን ያላወቀችው እንግሊዛዊት መደብር ውስጥ ወለደች

በተጨማሪም በተመሳሳይ ወቅት በአይሁዶች ላይ የሚፈጸሙ አካላዊ ጥቃቶች በግምሽ ያህል ጨምሯል። ባለፈው ዓመት 62 አካላዊ ጥቃቶች ያጋጠሙ ሲሆን ቀደም ሲል ግን 37 እንደነበረ ተገልጿል።

የጀርመን የፍትህ ሚኒስትር ካታሪና ባርሌይ እየጨመረ ስለመጣው በአይሁዶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት ለአንድ የሃገሪቱ ጋዜጣ እንደተናገሩት "ለሃገራችን የሚያሳፍር ድርጊት ነው" ብለውታል።

ተያያዥ ርዕሶች