የጉግልና የሁዋዌ ፍጥጫ አፍሪካዊያንን የሚያሳስብ ነው?

የሞባይል ስልክ ሱቅ Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ አፍሪካ ውስጥ ያሉት አብዛኞቹ ስማርት ስልኮች የቻይና ምርቶች ናቸው

ሁዋዌ የአንድሮይድ ሶፍትዌርን እንዳይጠቀም በጉግል በኩል የተጣለበት ዕቀባ አፍሪካ ከአሜሪካ አሊያም ከቻይና ቴክኖሎጂ አንዱን እንድትመርጥ የሚያስገድዳት የቴክኖሎጂ ቀዝቃዛ ጦርነት ሊሆን እንደሚችል የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

አብዛኞቹ አፍሪካዊያን በዚህ ዘመን ኢንትርኔትን የሚጠቀሙት ቻይና ሰራሽ በሆኑ ዘመናዊ ስልኮችና በቻይና ኩባንያዎች በተገነቡ የሞባይል አገልግሎት ኔትወርኮች አማካኝነት ነው። ከዚህ ውስጥ ደግሞ ቢያንስ ግማሽ ያህሎቹ አሁን ውዝግብ ውስጥ በገባው ግዙፉ የቻይና የቴሌኮም ኩባንያ ሁዋዌ የተገነቡ ናቸው።

"ሁዋዌ በአፍሪካ የቴሌኮም መሰረተ ልማትን በመዘርጋት ሰፊ ድርሻ ያለው በመሆኑ አሜሪካ ኩባንያውን ለማዳከም የምትወስደው እርምጃ ከተሳካላት ውጤቱ በአፍሪካ እያደገ ባለው የቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ የሚያሳድረው ጫና ቀላል የሚባል አይሆንም" ይላሉ፤ ደቡብ አፍሪካ መቀመጫውን ያደረገው የቻይና አፍሪካ ባልደረባ የሆኑት ኤሪክ ኦላንደር።

በሁዋዌ ላይ በአሜሪካ የተከፈተውን ዘመቻ የሚመሩት ትራምፕ ሲሆኑ ወዳጆቻቸው ከቻይናው ኩባንያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያቋርጡ የተለያዩ ምክንያቶችን ሰጥተዋል። ከእነዚህም መካከል ኩባንያው የሚያቀርባቸው ቴክኖሎጂዎች ለቻይና መንግሥት ስለላ የሚያመቹ በመሆናቸው የደኅንነት ስጋት ናቸው ይላሉ።

ነገር ግን ሁዋዌ ይህንን ክስ በተደጋጋሚ ሲያስተባብል ቆይቷል።

በእጅ ስልክዎ በኩል እየተሰለሉ ቢሆንስ?

ሳምሰንግ እንደ መጽሐፍ የሚገለጥ ስልክ አመረተ

ዋትስአፕ ሲጠቀሙ እንዴት ራስዎን ከጥቃት መከላከል እንደሚችሉ ያውቃሉ?

የጉግል የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኤሪክ ሽሚት በኢንተርኔት አገልግሎት ዙሪያ ዓለም በሁለት ልትከፈል እንደምትችል ይተነብያሉ። "በቻይና የሚመራ የኢንትርኔት አገልግሎትና በአሜሪካ የሚመራ ኢንትርኔት መምጣቱ አይቀርም" ይላሉ።

ይህ ከተከሰተ አፍሪካ ከአንደኛው ወግና መቆም የለባትም ብለው ለቢቢሲ የተናገሩት ደግሞ በአፍሪካና ቻይና ግንኙነት ላይ ባለሙያ የሆኑት ሃሪተ ካሪዩኪ ናቸው። "ፍልሚያው የእኛ ስላልሆነ ለእኛ የሚሻለው ላይ ነው ማተኮር ያለብን" ሲሉ ይመክራሉ።

Image copyright AFP

ካሪዩ አክለውም የአፍሪካ ሃገራት በጋራ ሆነው ያላቸውን አማራጮች ለሕዝባቸው በማስረዳት የአውሮፓ ሕብረት ያወጣውን አይነት አፍሪካውያን ተጠቃሚዎችን የሚጠብቅ የመረጃ ጥበቃ ሕግ ለማውጣት መስማማት አለባቸው።

ተማሪዎች አስተማሪያቸውን በመግደል ተጠርጥረው ተያዙ

"ይህ ምናልባትም አፍሪካ እንዲሁ ዝም ብላ ገበያው የሚያቀብላትን ከመጠቀም ውጪ ለአህጉሪቱ ተስማሚ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን ለመፍጠር ጊዜው ሳይሆን አይቀርም። አፍሪካዊያን እየገፋ የመጣውን የዲጂታል ቅኝ ግዛት ለመጋፈጥ ራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው" ይላሉ።

'ስርሰራ በአፍሪካ ሕብረት ላይ'

በአሁኑ ወቅት በሁዋዌ ላይ የሚቀርበው ስጋት ትኩረት የሚያደርገው በምዕራቡ ዓለም ያለውን የመረጃ መረብ ደኅንነት ላይ ይሁን እንጂ፤ ቀደም ሲል አፍሪካ ውስጥ ተፈጸመ ከተባለ የመረጃ ደኅንት ጥሰት ጋር የቻይናው ኩባንያ ስም ተነስቶ ነበር።

ሁዋዌን የሚተቹት በማስረጃነት የሚጠቅሱት ባለፈው ዓመት ለ ሞንድ የተባለው የፈረንሳይ ጋዜጣን ነው። ጋዜጣው አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የአፍሪካ ሕብረት ጽህፈት ቤት ውስጥ በሁዋዌ የተዘረጋው የኮምፒውተር ሥርዓት ለመረጃ ስርቆት ተጋልጧል የሚል ዘገባ ነበር ያቀረበው።

መረጃው ጨምሮም ለአምስት ዓመታት ያህል ከሕብረቱ ጽህፈት ቤት ሰርቨር መረጃዎች እኩለ ሌሊት ላይ 8 ሺህ ኪሎ ሜትር ርቆ ቻይና ሻንጋይ ውስጥ ወደሚገኝ ሰርቨር ይተላለፍ እንደነበር መታወቁን አመልክቷል።

አምስት ካሜራ ያለው ተንቀሳቃሽ ስልክ

ነገር ግን በዚህ የጋዜጣ ዘገባ ላይ የቀረበውን ውንጀላ የአፍሪካ ሕብረትም ሆነ የቻይና መንግሥት ባለስልጣናት አስተባብለውታል።

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ የአፍረካ ሕብረት የመረጃ መረብ በሁዋዌ ተመዝብሯል መባሉን አስተባብሏል

ሁዋዌ አፍሪካ ውስጥ ዘመናዊ ስልኮች መሸጥ ጨምሮ እጅግ ግዙፍ የቴሌኮም ሥራዎችን የሚያከናውን ኩባንያ ነው።

በደቡብ አፍሪካው የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ኢንስቲቲዩት ውስጥ የቻይናና አፍሪካ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ኮበስ ቫን ስታደን ለቢቢሲ እንደተናገሩት በአፍሪካ ያሉትን አብዛኞቹን ፎርጂ የኢንትረኔት መረብን የዘረጋው ሁዋዌ ነው።

ሁዋዌአፍሪካ ውስጥ:

  • በ40 ሃገራት ውስጥ ይሰራል።
  • ቢያንስ 50% የአፍሪካን ፎርጂ የኢንተርኔት መረብ ዘርግቷል።
  • ለዘመናዊ ከተሞች ፕሮጀክት ቴክኖሎጂ ያቀርባል።
  • በርካታ የጋራ የምርምር ሥራዎችን ያከናውናል።
  • ዘመናዊ የሞባይል ስልኮችን በመሸጥ በአለም አራተኛ ነው ።

ምንጭ፡ አውስትራሊያን ስትራተጂክ ፖሊሲ ኢኒስቲቲዩት፣ ሁዋዌ፣ አይዲሲ

ሁዋዌ የመጀመሪያውን ጽህፈት ቤቱን በአፍሪካ ውስጥ የከፈተው ከ10 ዓመት በፊት ሲሆን የ5 ጂ ቴክኖሎጂን በአህጉሪቱ ውስጥ ለመጀመር የሚያስችለውን ኮንትራት ለማግኘት ከሚያስችለው ደረጃ ላይ ይገኛል።

ሁዋዌ አፍሪካ ውስጥ ላለው ሰፊ ተሳትፎ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረገለት በአፍሪካ ውስጥ ያለውን እምቅ የኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ኢኮኖሚ አቅም በመጠቀም በኩል የመጀመሪያው ኩባንያ በመሆኑና ይህንንም ለመደገፍ ገንዘብ በማውጣቱ ነው።

ለዚህ ደግሞ "ቻይና የምትሰጠው ድጋፍ የአፍሪካ መንግሥታት ከቻይና ኩባንያዎች ጋር እንዲሰሩ የሚያስገድዳቸው መሆኑ የበለጠ ጠቅሞታል" ይላሉ ቫን።

የቴክኖሎጂ ምርምር ተቋም የሆነው አይዲሲ እንዳለው በአሁኑ ወቅት ሁዋዌ፣ ቴክኖና ኢንፊኒክስ የተባሉ ምርቶችንና ሳምሰንግን ከሚያመርተው ከሌላኛው የቻይና ኩባንያ ትራንሽን ቀጥሎ በአፍሪካ ውስጥ አራተኛው ትልቁ የስማርት ስልኮች ሻጭ ነው።

አራቱም የስልክ ምርቶች በአሁኑ ጊዜ የሚጠቀሙት የጉግል አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሥርዓትን ነው።

ሁዋዌ ቻይና ከአሜሪካ ጋር የገጠመችው ፍጥቻ ወደ ቴክኖሎጂ ቀዝቃዛ ጦርነት የሚያድግ ከሆነና በአፍሪካ ያለውን ሥራውን የሚያሰጋው ከሆነ በአፍሪካ ያለው የበላይነትና ከአፍሪካ መንግሥታት ጋር ያዳበረው ግንኙነት በገበያው ላይ ለመቆት አመቺ እድልን ይፈጥርለታል።

ሞባይል ስልክዎ ላይ መከራን አይጫኑ

ጃፓን ከቀበሌ መታወቂያ ያነሰች ሞባይል ሠራች

ለርካሾቹ የቻይና ስልኮች ምስጋና ይግባቸውና በአሁኑ ወቅት አብዛኞቹ አፍሪካዊያን የኢንተርኔትን አገልግሎት ይጠቀማሉ። አብዛኞቹን አፍሪካዊ ከኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ይልቅ የሚያሳስባቸው ስልኮቹ ባለሁለት ሲም ካርድ መሆን አለመሆናቸውና ለረጅም ጊዜ የሚያገለግል ባትሪ ያላቸው መሆኑን ጨምሮ የስልኮቹ ዋጋ ውድ መሆን ነው።

ፉክክር በአሜሪካና በቻይና የኢንተርኔት አገልግሎት ላይ

በቻይናና አፍሪካ ግንኙነትና ኢንተርኔትን የተመለከቱ ጉዳዮች ጸሃፊ የሆኑት ኢጊኒዮ ጋግሊያርደን እንደሚሉት በአሜሪካና በቻይና መካከል የተፈጠረው እሰጥ አገባ ሁዋዌ በአፍሪካ ውስጥ ያለውን ገበያውን ለመጠበቅ የራሱን ሶፍትዌር እንዲጠቀም ሊገፋው እንደሚችል ገልጸዋል። ነገር ግን ይህንን ለማድረግ ርካሽና ቀላል እንደማይሆን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ቻይና ውስጥ እንደሚደረገው በጉግል ፋንታ ባይዱ፣ ከትዊተር ይልቅ ሲና ዌቦን ለመጠቀም የሚያስችለውን አይነት ዝግ የኢንተርኔት መጠቀሚያ ዘዴን አፍሪካ ውስጥ ለመጠቀም አስቸጋሪ ነው።

ነገር ግን የማኅበራዊ ሚዲያን፣ የመልዕክት መለዋወጫና የሞባይል ክፍያ መፈጸሚያ ያለውን ዊቻት የተባለው ባለብዙ ግልጋሎት መተግበሪያን በአፍሪካ ተግባራዊ ለማድረግ ይቻላል።

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ሁዋዌ በአፍሪካ ውስጥ አራተኛው ትልቁ የስማርት ስልክ ሻጭ ነው

አፍሪካ እንድትመርጥ ትገደድ ይሆን?

"የአፍሪካ ሃገራት ከአንዱ ወገን መቆም የለባቸውም፤ በዚህ የቴክኖሎጂ ፍልሚያ ውስጥ ገለልተኛ የሆነ እንቅስቃሴ በመጀመር የራሳቸውን ጥቅም ማስጠበቅ የሚችሉበትን አጋጣሚ ሊፈጥሩ ይችላሉ" ይላሉ ኢጊኒዮ ጋግሊያርደን።

በጥናታቸው ላይ የአፍሪካ ሃገራትን ቁጥጥር የምታደርግበትን የኢንተርኔት ሥርዓት እንዲጠቀሙ ቻይና አጥብቃ ገፍታለች የሚለውን ከጥርጣሬ ውጪ ማስረጃ እንዳላገኙለት ጠቁመዋል።

ነገር ግን ኢጊኒዮ ጋግሊያርደን እንደሚያስቡት ቻይና ጥቅሟን ለማስከበር ስትል ከአፍሪካ መንግሥታት ጋር ያላትን ግንኙነት በመጠቀም ኩባንያዎቿ በምዕራባዊያን ተፎካካሪዎቻቸው ላይ የበላይነት እንዲያገኙ የተቻላትን ሁሉ ልታደርግ ትችላለች።

ትውስታ- የዛሬ 20 ዓመት ኢትዮጵያ ሞባይል ስልክን ስትተዋወቅ

ሞባይል ለኢትዮጵያ እናቶችና ህፃናት ጤና

በቻይናና በአሜሪካ መካከል ሊቀሰቀስ ከጫፍ የደረሰው የቴክኖሎጂ ቀዝቃዛ ጦርነት ለአፍሪካ መልካም አጋጣሚ እንደሆነ የሚናገሩት ካሪዩኪ አህጉሪቱም ጎራ ለመምረጥ መገደድ እንደሌለባትም ይመክራሉ።

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ከሚገኘው የሞጃ ምርምር ኢንስቲቲዩት ባልደረባ የሆኑት ፋዝሊን ፍራንስማን እንደሚሉት "በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ውስጥ ከዳር እስከ ዳር የደረሰው የኢንተርኔት አገልግሎትና ቴክኖሎጂ በአብዛኛው የቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ባፈሰሱት መዋዕለ ነዋይ ነው።"

ከዚህ አንጻር ተመራማሪዋ ፍራንስማን በእራሷ እይታ ጉዳዩን ስትደመድምም "አፍሪካ በፍልሚያው ከማን ወገን እንደምትቆም ከወሰነች ቆይታለች፤ ቻይናን መርጣለች" ትላለች።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ