ከሰላሳ በላይ የጴንጤ ቆስጣል አማኞች አሥመራ ውስጥ ታሰሩ

ኤርትራውያን ሰላማዊ ሰልፍ ሲያካሂዱ Image copyright Anadolu Agency

ከሰላሳ የሚበልጡ የጴንጤ ቆስጣል እምነት ተከታዮች አሥመራ በደኅንነት ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተቀማጭነቱን ለንደን ያደረገው ሪሊዝ ኤርትራ የተባለው የሃይማኖቶች መብት ተከራካሪ ቡድን ለቢቢሲ አስታወቀ።

የእምነቱ ተከታዮች የተያዙት በሦስት የተለያዩ ቦታዎች በአምልኮ ላይ ሳሉ ተከብበው እንደሆነ የድርጅቱ ተወካይ ዶ/ር ብርሃነ አስመላሽ ገልፀዋል።

"አሁን ያገኘነው ሰላም ከሰው ሳይሆን ከአምላክ ነው"- ዘማሪ ሳሙኤል ተስፋሚካኤል

ኤርትራ የሃይማኖት እሥረኞችን ፈታች

ከጥቂት ሳምንታት በፊትም 141 የሚሆኑ ግለሰቦች በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው የነበረ ሲሆን፤ ከመካከላቸው ሃምሳዎቹ እንደተለቀቁ ገልፀዋል።

ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ ከኤርትራ መንግሥት ምላሽ ለማግኘት ቢሞክርም አልተሳካም። የኤርትራ መንግሥት የጴንጤ ቆስጣል እምነትን ያገደው በፈረንጆቹ ከ2002 ጀምሮ ነው።

የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች እንደሚሉት የኤርትራ መንግሥትን እገዳ በተጣለባቸው የሃይማኖች መሪዎችንና የእምነቶቹ ተከታዮች ላይ ጭቆናና እስርን ጨምሮ መጠነ ሰፊ ተቋማዊ የመብት ጥሰቶችን እንደሚፈጽም ይከሳሉ።

መስመር ያልያዘው የኢትዮ-ኤርትራ የንግድ ግንኙነት ወዴት ያመራል?

ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ 6 ነጥቦች

ኤርትራ አብያተ ክርስቲያናትን መዝጋትና የእምነቶቹ ተከታዮችን ማሰር ከጀመረች አንስቶ በየዓመቱ ለንደን ከሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመሆን በመንግሥት ላይ ተቃውሟቸውን እንደሚያሰሙ የሚናገሩት የሪሊዝ ኤርትራ ዳይሬክተር ዶክተር ብርሃነ ባለፈው ሳምንት ተመሳሳይ ነገር ማድረጋቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል።

ጨምረውም ባለፈው ሳምንት የሪሊዝ ኤርትራ፣ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን፣ የ 'ቸርች ኢን ቼይንስ' እና 'ክርስትያን ሶሊዳሪቲ ዎርልድ ዋይድ' አባላት በቦታው ተገኝተው የኤርትራ መንግሥት የሃይማኖት መብት እንዲያከብር የሚጠይቅ ደብዳቤ ለኤምባሲው እንዳስረከቡ ተናገረዋል።

ተያያዥ ርዕሶች