የምልክት ቋንቋ በብዛት የሚነገርባት መንደር

ካታ ኮሎክ የሚናገሩ ሰዎች Image copyright Mark Eveleigh

ቤንግካላ በምትባለው ትንሽ የኢንዶኔዢያ መንደር የሚወለዱ ሰዎች አብዛኛዎቹ መስማት የተሳናቸው ናቸው። ከስድስት ትውልዶች በላይ ያስቆጠረው ይህ አጋጣሚ በአካባቢው ሰዎች ዘንድ ከእርግማን የመጣ እንደሆነ ይታመናል።

ሳይንቲስቶች ግን በጤና እክል ምክንያት የሚመጣና ከወላጅ ወደ ልጆች የሚተላለፍ ችግር እንደሆነ ያስረዳሉ።

በዚህች መንደር መስማት የተሳናቸው ሰዎች የሚናገሩት ካታ ኮሎክ የተባለ የምልክት ቋንቋ አለ። ካታ ኮሎክ በኢንዶኔዢያኛ መስማት የተሳናቸው ሰዎች ቋንቋ እንደማለት ነው።

"አካል ጉዳተኛ መሆኔ ጥሩ ደረጃ እንድደርስ አድርጎኛል"

ሙዚቃ ሳይሰሙ መወዛዋዝ ይችላሉ?

ሲወለዱ ጀምሮ መስማት የተሳናቸው የዚህች መንደር ነዋሪዎች ከሌሎች መስማት የተሳናቸው ሰዎች የተሻለ ሕይወት ነው የሚመሩት። ምክንያቱም መስማት የሚችሉትም ግማሾቹ ነዋሪዎች ካታ ኮሎክ የተባለውንና በመንደሪቷ ብቻ የሚታወቀውን የምልክት ቋንቋ መናገር ይችላሉ።

ለብዙ ዘመናት በመንደሪቱ የኖሩት መስማት የተሳናቸው ሰዎች ስለሆኑና ጎረቤትም ሆነ አንድ የቤተሰብ አባል መስማት ስለማይችል ግማሽ የሚሆኑት ነዋሪዎች ለመግባባት ሲሉ የምልክት ቋንቋውን መማር ግዴታቸው ነው።

ዊንሱ የመንደሯ ነዋሪ ሲሆን ወጣት እያለ የባሊ ደሴትን ለቱሪስቶች በመስጎብኘትና የማርሻል አርትስ ጥብበ በማሳየት ሕይወቱን ይመራ ነበር። ለሥራ በተንቀሳቀሰባቸው የተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎችን ብዙ መስማት የተሳሳናቸው ሰዎችን የመተዋወቅ እድል አጋጥሞታል።

እሱ እንደሚለው አብዛኛዎቹ መስማት የተሳናቸው ሰዎች በጣም ቅርብ ከሚሏቸው የቤተሰብ አባላት ውጪ ከማንም ጋር አይነጋገሩም። ቋንቋቸውንም ለመማር ጥረት የሚያደርግ ሰው የለም።

በኢንዶኔዢያ መስማት የተሳናቸው ጥምረት ተወካይ የሆኑት ኬቱት ካንታ መስማት የተሳናቸው ሆነው ለሚወለዱ ሰዎች ከዚህች መንደር የተሻለ ቦታ የለም ብዬ አላምንም ብለዋል።

በዚህች ትንሽ መንደር መስማት የሚችሉት ሰዎች 'ኢግኔት' ተብለው የሚጠሩ ሲሆን መስማት ከተሳናቸው የመንደሪቱ ነዋሪዎች ጋር ተቀላቅለው የሆድ የሆዳቸውን ሲያወሩ መመልከት የተለመደ ነው።

Image copyright Mark Eveleigh

ከመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከ ሃይማኖት ተቋማት፣ ከገበያ ቦታዎች እስከ መዝናኛ ስፍራዎች ሁሉም ቦታ ለይ መስማት የተሳናቸውና ያልተሳናቸው ተቀላቅለው ነው የሚኖሩት።

በዓይነ ስውሯ የተሠራው የሚያይ ሻንጣ

''እግሬን ባጣም ትልቁን ነገር አትርፌ ለትንሹ አልጨነቅም''

በካታ ኮሎክ የምልክት ቋንቋ መሰረት ሁሉም ነገር በቀላሉ ለመረዳት እንዲቻል ተደርጎ ነው የተሰራው። ረጅም ለማለት እጅን ወደላይ በመስቀል ቁመትን ማሳየት እንዲሁም ትልቅ ለማለት ደግሞ እጆችን ሰፋ አድርጎ ምልክት ማሳየትን የመሳሰሉ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ።

በዚህ ምክንያት ማንኛውም ቋንቋውን የማይናገር ሰው እንኳን በቀላሉ መግባባትና የምልክት ቋንቋውን በአጭር ጊዜ መልመድ ይችላል።

በቤንግካላ መንደር መስማት የተሳናቸውን ያልተሳናቸው ለሚሰሩት ማንኛውም ዓይነት ሥራ እኩል ክፍያ ነው የሚፈጸመው። ነገር ግን ከመንደሯ ወጣ ብለው ሥራ ማግኘት የሚፈልጉ መስማት የተሳናቸው ሰዎች ብዙ ፈተናዎች እንደሚገጥሟቸው ይናገራሉ።