ህንድ፡ ክፍያ ባልከፈለ ተማሪ እጅ ላይ ማህተም የመታው ትምህርት ቤት ተወገዘ

ማህተም የተመታበት የተማሪ እጅ Image copyright BBC Punjabi
አጭር የምስል መግለጫ ትምህርት ቤቱ ተማሪው ማስታወሻ ደብተሩን ረስቶ በመምጣቱ በእጁ ላይ ማህተም ለማድረግ መገደዳቸውን ገልፀዋል።

ምን ዓይነት ትምህርት ቤት ነው የተማሩት? ከፍተኛ ክፍያ የሚፈፀምባቸው፣ መጠነኛ ክፍያ የሚፈፀምባቸው የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ወይስ ምንም የማይከፈልባቸው የመንግሥት ትምህርት ቤቶች?

ክፍያ በሚከፈልባቸው ትምህርት ቤቶች የተማራችሁት የትምህርት ክፍያ ስታሳልፉ መምህራኑ አሊያም ትምህርት ቤቱ የወሰደባችሁ እርምጃ ምንድን ነው? ስንገምት ወላጅ እንድታመጡ ልትጠየቁ ትችላላችሁ፤ አሊያም ደግሞ በስልክ ቤተሰቦቻችሁ ጋር ሊነጋገሩ ይችላሉ። ግፋ ካለም ከትምህርት ቤቱ ማሰናበት ሊሆን ይችላል።

የህንድ ፊልም አፍቃሪዎች ወተት እየሰረቁ ነው

የ'ሰከረ' አዋላጅ ሐኪም እናትና ልጅን ገደለ

በህንድ ፑንጃብ የሚገኘው ትምህርት ቤት የተፈፀመው ግን ባልተለመደ መልኩ ከዚህ ለየት የሚል ተግባር ነው።

ትምህርት ቤቱ የትምህርት ክፍያ ባልከፈለ ተማሪ እጅ ላይ ማህተም በመምታት ወደ ቤቱ ልኮታል።

ይህንኑ ተከትሎ በሰሜን ህንድ ግዛት ፑንጃብ የትምህርት ባለሥልጣናት የትምህርት ክፍያ ባለመከፈሉ በተማሪው እጅ ላይ ማህተም የመታው ትምህርት ቤት ላይ ምርመራ እያካሄዱ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የ13 ዓመቱ ታዳጊ ቤተሰቦች በበኩላቸው ተማሪው ላይ አሳፋሪ ነው ያሉት ድርጊት ከተፈፀመ በኋላ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ እንደማይፈልግ መናገሩን ገልፀዋል።

የዚሁ የግል ትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ድርጊቱን መፈፀማቸውን አምነው በተማሪው እጅ ላይ ማህተም የመቱት ማስታወሻ ደብተሩን ረስቶት በመምጣቱ እንደሆነ ተናግረዋል።

ለሴቶች የተከለከለ ተራራን የወጣችው የመጀመሪያ ሴት

ምንም እንኳን የማህተሙ ቀለም በቀላሉ በውሃ የሚለቅ ቢሆንም የመምህሩ ድርጊት ግን ያልተገባ ነው ሲሉ ርዕሰ መምህሩ ድርጊቱን አውግዘውታል።

የተማሪው ወላጆች ለተከታታይ ሁለት ወራት ክፍያ ያልፈፀሙ ሲሆን እንዲከፍሉም ማሳሰቢያ ቢላክላቸውም ችላ ማለታቸውን ትምህርት ቤቱ ገልጿል።

ትምህርት ቤቱ ምክንያቶችን ቢደረድርም የተማሪው ወላጆች ግን ድርጊቱን ያልተገባ ነው ሲሉ ኮንነውታል።

በባጃጅ ሹፌርነት ሕይወታቸውን እንደሚመሩ የሚናገሩት የተማሪው ወላጅ አባት " ግለሰቡ ክፍያ የጠየቀው ባልተገባ መንገድ ነው" ብለዋል።

ክፍያውን ለመፈፀም የተወሰነ ጊዜ እንዲሰጣቸው ትምህርት ቤቱን እንደጠቁ የሚናገሩት የተማሪው አባት በልጃቸው ላይ የተፈፀመው ድርጊት መላ ቤተሰቡን እንዳሳፈረ ተናግረዋል።

የአካባቢው የትምህርት ባለሙያ ስዋርንጀት ካውር " በጣም ስህተት ነው" በማለት ድርጊቱን የፈፀሙት ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ አስታውቀዋል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ