የዓለም ከትምባሆ ነጻ ቀን: ማጨስ ከጠቃሚ የሕይወት ዘይቤ ወደ ገዳይ ልማድ

ጊልስ ኤቨራርድ Image copyright Getty Images

እንደ የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ መሰረት ትምባሆ ከሚያጨሱ ሰዎች ግማሾቹ በሲጋራ ምክንያት ህይወታቸው ያልፋል። በየዓመቱ 6 ሚሊዮን ሰዎች በቀጥተኛ መልኩ ከትንባሆ ጋር በተያያዘ ምክንያት ህይወታቸው የሚያልፍ ሲሆን ምንም የማያጨሱ 600 ሺ ሰዎች ደግሞ ለሲጋራ ጭስ በመጋለጣቸው ሳቢያ ለሞት ይዳረጋሉ።

በአውሮፓውያኑ 2016 የአጫሾች ቁጥር ከዓለም ህዝብ 20 በመቶ የደረሰ ሲሆን በ2000 ላይ ግን 27 በመቶ ነበር። ይህ ደግሞ ትልቅ ለውጥ ነው ያለው የዓለም የጤና ድርጅት፤ አሁንም ቢሆን የዓለማቀፍ ስምምነት ከተደረሰበት ቁጥር ላይ ለመድረስ ብዙ እንደሚቀር ያሳስባል።

በቤታችን ውስጥ ያለ አየር የጤናችን ጠንቅ እንዳይሆን ማድረግ ያለብን ነገሮች

በዓለማችን 1.1 ቢሊየን አጫሾች ያሉ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት የሚገኙት መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት ውስጥ መሆኑ ደግሞ ነገሮችን ይበልጥ አሳሳቢ ያደርጋቸዋል።

ዛሬ የዓለም ከትምባሆ ነጻ ቀን ነው። ትምባሆ ማጨስ ከየት ተነስቶ እዚህ ደረሰ?

ለብዙ ዘመናት ትምባሆ ማጨስ የጤናማ ህይወት መንገድ ዘይቤ ተደርጎ የሚታሰብ የነበረ ሲሆን በትምባሆ ውስጥ የሚገኘው አነቃቂና ሱስ አስያዥ የሆነው ንጥረ ነገር 'ኒኮቲን' ስያሜውን ያገኘው በ16ኛው ክፍለ ዘመን ነበር። ይህ ንጥረ ነገርም ከፈጣሪ የተሰጠ የህመም ማስታገሻ ተብሎ ይጠራም ነበር።

የሚያስወርዱ ሴቶች ቁጥር ከሚወልዱ ሴቶች የሚበልጥባት ሀገር

ጊልስ ኤቨራርድ የተባለው ሆላንዳዊ ተመራማሪ በወቅቱ በነበረው አመለካከት የትምባሆ ጭስ የመድሃኒትነት ባህሪ አለው ከሚል በመነሳት በርካቶች ለተለያዩ ህመሞች የህክምና ባለሙያዎችን ድጋፍ ከመጠየቅ በመራቃቸው የሀኪሞችን ተፈላጊነት እስከ መቀነስ የደረሰ አቅም ነበር።

በ1587 በጻፈው መጽሃፍ ላይም እንደጠቀሰው በጊዜው የትምባሆ ጭስ የተመረዘ ሰውን ለማዳንና ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል በከፍተኛ ሁኔታ ጥቅም ላይ ይውል እንደነበር ጽፏል።

በአሁኖቹ ኩባ፣ ሃይቲ እና ባሃማስ በመሳሰሉት ሃገራት የተበከሉ ቦታዎችን ለማጽዳት፣ ድካም ለመቀነስና በሽታ ለመከላከል የትምባሆ ቅጠል ማቃጠል የተለመደ ተግባር እንደነበር ጣልያናዊው አሳሽ ክርስቶፈር ኮሎምበስ በ1492 በጻፈው መፍሃፍ ላይ ጠቁሟል።

የትንባሆ ቅጠልን ከኖራ ጋር በመቀላቀል ጥርስን ለማጽዳት የሚያገለግል ሳሙና መስራት በቬኒዙዌላ አካባቢ ይዘወተር የነበረ ሲሆን ህንድ ውስጥ ደግሞ አሁንም ድረስ ጥቅም ላይ ይውላል።

ሜክሲኮ ውስጥ አንገት አካባቢ የሚወጡ ቁስሎችን ለማዳን የወቅቱ የህክምና ባለሙያዎች አካባቢውን ከቀደዱ በኋላ ትኩስ የትንባሆ ቅጠል ከጨው ጋር በማቀላቀልና ከላይ በማድረግ ህክምና ይሰጡ ነበር።

በቤታችን ውስጥ ያለ አየር የጤናችን ጠንቅ እንዳይሆን ማድረግ ያለብን ነገሮች

በ16ኛውና 17ኛው ክፍለ ዘመን በዶክተሮች፣ የቀዶ ህክምና ባለሙያዎችና የህክምና ተማሪዎች ዘንድ ትምባሆ ማጨስ የተለመደ ነገር ነበር። ምክንያቱ ደግሞ ባለሙያዎቹ ለምርምር የሚጠቀሟቸው የሰው አስከሬን ሽታን ለመቀነስና ከሞቱ ሰዎች ሊተላለፉ የሚችሉ በሽታዎችን ለመከላከል በማሰብ ነው።

እንግሊዝ ውስጥ በ1655 ተከስቶ በነበረው ወረርሽኝ ምክንያት ህጻናት ተማሪዎች በትምህርት ቤት ውስጥ ትምባሆ እንዲያጨሱ ይደረግ ነበር። ትምባሆውን ያጨሱ ህጻናትም ከወረርሽኙ ነጻ ይሆናሉ፤ የተያዙትም ወደሌሎች አያስተላልፉም ተብሎ ይታመን ነበር።

የሞቱ ሰዎችን አስከሬን የሚቀብሩና የሚያቃጥሉ ሰዎችም ትምባሆ እንዲያጨሱ ይደረግ ነበር።

ነገር ግን የትንባሆን ጎጂነት ቀድመው የተረዱ ሰዎች አልጠፉም ነበር። እንግሊዛዊው ተመራማሪ ጆን ኮታ በ1612 ትንባሆ ካለው ጥቅም በተጨማሪ ለህይወት እጅግ አስጊ የሆነ ንጥረ ነገር በውስጡ እንዳለ ጽፎ ነበር።

ጫት የአእምሮ ጤናን እንደሚጎዳ ጥናት አመለከተ

ምንም እንኳን የትንባሆ ጎጂነት ቀስ በቀስ እየታወቀ ቢመጣም ተፈላጊነቱ ግን ከምንጊዜውም በበለጠ እየጨመረ ሄዷል። እስከ 18ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ የትምባሆ ጭስን ወደ ጆሮ ውስጥ በማስገባት የጆሮ ህመምን ለማከምም ጥቅም ላይ ይውል ነበር።

ከ1920 እስከ 1930ዎቹ ባሉት ጊዜያት ትምባሆ ማጨስ ብዙ የጤና እክሎች እንደሚያስከትል መታመን ሲጀምር በወቅቱ ታዋቂ የነበረው 'ካሜል' የተባለ የሲጋራ አምራች ድርጅት 'ዶክተሮች ሲጋራ ማጨስ ጠቃሚ እንደሆነ አረጋግጠዋል፤ እንደውም እራሳቸው ያጨሱታል' በማለት ማስታወቂያ አሰርቶ ነበር።

ከዚህ በተጨማሪ አፋኞች ድምጻቸው ጥርት እንዲልና ጉሮሯቸውን ለማጽዳት ሲጋራ እንዲያጨሱ ይመከር ነበር። በዚህም ምክንያት ታዋቂ ዘፋኞችና የሬድዮ ዝግጅት አቅራቢዎች በብዛት ሲጋራ ያጨሱ ነበር።

ባለፉት 30 ዓመታት ግን ሲጋራ በጤና ላይ ስለሚያደርሰው ጉዳት ብዙ ጥናቶች ይፋ መሆን የጀመሩ ሲሆን ሰዎችም ጉዳቱን በመገንዘብ ጥንቃቄ ማድረግ ጀምረዋል።

ወንዶች የማያወሯቸው አምስት አሳሳቢ ነገሮች

በዚህም ምክንያት ብዙ ሃገራት ህዝብ በተሰበሰበባቸው ቦታዎች ላይ ሲጋራ ማጨስ የሚከለክሉ ህጎችን እንዲያወጡ ግድ ብሏቸዋል። ከዚህ ባለፈም ስለ ሲጋራ ጉዳት የሚያትቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅቶች በየቦታው መታየት ጀምረዋል።

አንዳንድ ሃገራት ከዚህም አልፈው ሲጋራ ማጤስ በሳምባ እና ሌሎች የሰውነታችን ክፍሎች ላይ ስለሚያደርሰው ጉዳት የሚያብራሩ መልዕክቶች በሲጋራ ማሸጊያዎች ላይ እንዲለጠፍ የሚያስገድድ ህግ አውጥተዋል።

እርግዝና ላይ ያሉ ሴቶችም ቢሆን ሲጋራ ማጨስ በጽንሱ ላይ ስለሚያደርሰው ጉዳት መገንዘብ የጀመሩት ከ30 ዓመት በፊት አካባቢ ነበር።

ዓለማችን ካጋጠሟት ወረርሽኞች ሁሉ ትልቁ ትምባሆ ነው በማለት የዓለም ጤና ድርጅት ያስታወቀ ሲሆን ሃገራት የትምባሆ አጠቃም ላይ ጠበቅ ያለ ህግ እንዲያወጡም ይመክራል።

በዚህ መሰረትም ሃገራት ወጣቶች ትምባሆ እንዳያጨሱ የሚከለክሉ ፖሊሲዎች እንዲያወጡ፣ የትምባሆ ማስታወቂያዎች እንዲከለከሉና የትምባሆ አምራች ድርጅቶች ላይ ከበድ ያለ ግብር እንዲጣልባቸው ሃሳብ አቅርቧል።

ተያያዥ ርዕሶች