ፕሬዚዳንት ቡሃሪ ከእንስሳት ውጭ ቤሳ ቤስቲን የለኝም አሉ

ፕሬዚዳንት ቡሃሪ Image copyright Reuters

የናይጀሪያው ፕሬዚደንት ሙሃመዱ ቡሃሪ በአውሮፓውያኑ 2015 ምርጫ ከተመረጡ በኋላ ምንም ዓይነት ሃብትና ንብረት እንዳላፈሩ ለ'ዴይሊ ትረስት' ጋዜጣ ተናገሩ።

ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት ባለፈው ረቡዕ ለሁለተኛ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት መመረጣቸውን ተከትሎ ቃለ መሃላ ከመፈፀማቸው በፊት ሃብታቸውን በዝርዝር እንዲያሳውቁ በተጠየቁበት ጊዜ ነው። በጊዜውም 270 የቀንድ ከብቶች፣ 25 በጎች፣ 5 ፈረሶችና የተለያየ ዝርያ ያላቸው ወፎች እንዳላቸው አስታውቀዋል።

እንደ 'ዴይሊ ትረስት' ከሆነ የፕሬዚዳንቱ ሃብት በ2015ቱ ምርጫ ሲያሸንፉ ካሳወቁት ንብረት የተለየ ጥሪት አላፈሩም። ፕሬዚዳንቱ በናይጄሪያም ሆነ ከአገሪቱ ውጭ አዲስ ቤት የላቸውም፣ የአክሲዮን ድርሻም ሆነ አዲስ የሒሳብ ቁጥር (የባንክ አካውንት) የላቸውም።

"ቤቶች ከመፍረሳቸው በፊት ዜጎች መጠለያ የማግኘት መብታቸው መከበር አለበት" ባለአደራ ምክር ቤት

"የግንቦት 20 ታሪካዊነት አጠያያቂ አይደለም"

ይሁን እንጂ ጋዜጣው የፕሬዚዳንት ጽ/ቤቱን ጠቅሶ እንደዘገበው ቡሃሪ በካዱና፣ ዳውራ፣ ካኖ እና አቡጃ አምስት ቤቶች እንዲሁም ሁለት ሰፋፊ የእርሻ መሬት ያላቸው ሲሆን አንዱ በካኖ ሲገኝ ሌላኛው በፖርት ሃርኮርት ይገኛል።

አክሎም ቡሃሪ የእፅዋት እንዲሁም የእንስሳት ማርቢያ የእርሻ መሬት ያላቸው ሲሆን 270 የቀንድ ከብቶች፣ 25 በጎች፣ 5 ፈረሶች እና የተለያየ ዝርያ ያላቸው ወፎች እንዲሁም የተለያዩ ዛፎች ባለቤት እንደሆኑ ገልጿል።

ፕሬዚደንት ቡሃሪ ከሌሎች የአገሪቱ ፖለቲከኞች በተሻለ ለታማኝነታቸው አጥብቀው ይሰራሉ። በምርጫ ዘመቻቸውም መጥረጊያን እንደ ምልክታቸው የተጠቀሙ ሲሆን ዓላማቸውም በፖለቲካው ውስጥ ያሉ ችግሮችን ማፅዳት እንደሆነ ሲናገሩ ቆይተዋል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ