ካስተር ሰሜኒያ፡ የ800 ሜትር የኦሎምፒክ ሻምፒዮናዋ ለስዊዝ ፍርድ ቤት ይግባኝ አለች

ካስተር ሰሜንያ Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ሰሜንያ የኦሎምፒክ 800 ሜትር ሁለት ጊዜ አሸናፊ ነች

የ800 ሜትር የኦሊምፒክ ሻምፒዮና ካስተር ሰሜንያ ከፍተኛ 'ቴስቶስትሮን' የተሰኘው ሆርሞን ያላቸው ሴት ሯጮችን በተመለከተ የወጣውን ሕግ ተከትሎ ለዓለም አቀፉ የስፖርት የግልግል ዳኝነት ተቋም ቅሬታ አቅርባ ነበር።

ኤኤንሲ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑን ውሳኔ 'ዘረኛ' ነው አለ

"ሥልጣን ለደም ግፊት አጋልጦኛል" ኃይሌ ገብረሥላሴ

ሰሜኒያ በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌደሬሽን የተጣለውን አዲስ ሕግ በመቃወም ያቀረበችውን አቤቱታ የስፖርት የግልግል ዳኝነት ተቋም (ካስ) ውድቅ ካደረገባት በኋላ ወደ ስዊዘርላንድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ የጠየቀችው።

"እኔ ሴት እና ዓለም አቀፍ ሯጭ ነኝ" የምትለው የ28 ዓመቷ ካስተር ሰሜንያ ዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ማንነቴን ሊያስለውጠኝ አሊያም ሊያስቆመኝ አይችልም ብላለች።

ትናንት በተሰጠው መግለጫ ላይም ሰሜኒያ ዓለም አቀፉ የስፖርት የግልግል ዳኝነት ያሳለፈውን ውሳኔ ወደ ጎን በመተው የስዊዝ ፍርድ ቤት ገለልተኛ በሆነ መንገድ እንዲመለከተው እንደምትጠይቅ ተናግራለች። ዋነኛው ጥያቄዋም መሠረታዊ የሆኑ የሰብዓዊ መብቶች እንደሆኑ አስታውቃለች።

የሰሜኒያን ጉዳይ የሚከታተሉት ዶሮቴ ችራም "ዓለም አቀፉ የስፖርት የግልግል ዳኝነት ተቋም መሠረታዊ የሆኑትን የስዊዝ ፖሊሲ ጥሷል" ብለዋል።

ሰሜኒያና ሌሎች ሯጮች በ400 ሜትር ሩጫ ውድድር ላይ እንዲሳተፉ የሆርሞን ለውጥ ላይ ሕከምና ሊደረግላቸው አሊያም ደግሞ ሌላ የሩጫ ርቀት ሊሰጣቸው ይገባል የሚል አቋምም አላቸው- ዶሮቴ።

በዋግ ኸምራ አስተዳደር 7 የዳስ ት/ቤቶች አሉ

"የግንቦት 20 ታሪካዊነት አጠያያቂ አይደለም"

ባለፈው የስፖርት የግልግል ዳኝነት ተቋም አቤቱታዋን ውድቅ የተደረገባት ሰሜኒያም "ላለፉት አስርተ ዓመታት ዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ከዓላማየ ሊያደናቅፈኝ ሞክሯል፤ ይሁን እንጂ ይህ ጠንካራ እንድሆን አድርጎኛል፤ ተቋሙ ያስተላለፈው ውሳኔም ከዓላማዬ ሊያቆመኝ አይችልም" ብላለች ።

ድርጊቱ እንዲያውም ከፍ እያደረጋትና በደቡብ አፍሪካና በሌሎች ዓለማት የሚገኙ ወጣት ሴቶችንና ሯጮችን እንድታበረታታ ምክንያት እንደሆናት ተናግራለች።

ዓለም አቀፉ የስፖርት ግልግል ዳኝነት የወንድ ሆርሞን ከፍ ባለ መጠን ያላቸው ሴት ሯጮችን በተመለከተ ያወጣው ሕግ አግላይ ነው የምትለው ሰሜኒያ የሴት ሯጮችን ስሜትና ፅናት ለመጠበቅ ቢያንስ ሕጉ ምክንያታዊና የተመጣጠነ መሆን ነበረበት ስትል አስተያየቷን ሰጥታለች።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ