ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ስደተኞች ከሊቢያ ወደ ጣልያን ተወሰዱ

ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ስደተኞች Image copyright UNHCR Libya

ከአንድ መቶ አምሳ በላይ የሚሆኑ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ከሊቢያ መዲና ትሪፖሊ ወደ ጣልያን መወሰዳቸውን የተባበሩት መንግሥታት ገልጿል።

ከነዚህም ውስጥ ስልሳ አምስቱ ህፃናት ሲሆኑ፤ ከነሱም ውስጥ አስራ ሶስቱ ከአንድ አመት ዕድሜ በታች ናቸው ተብሏል።

ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ጨምሮ ከሱዳንና ከሶማሊያ የመጡ ስደተኞችም ተካተውበታል።

በኢትዮጵያ ስላሉ ስደተኞች አንዳንድ ነጥቦች

ስደተኞች በየዓመቱ 8 ቢሊዮን ዶላር ለቤተሰቦቻቸው ይልካሉ

በሊቢያ የባህር ዳርቻ ስደተኞች ሰጠሙ

አብዛዎቹ ስደተኞች በምግብ እጦት ሰውነታቸው ከስቶ፣ ገርጥተውና በተለያዩ ህመሞችም ተጠቅተው ነበር ተብሏል።

ብዙ ስደተኞች የተሻለ ህይወትን ፍለጋ ሽተው ወደ አውሮፓ ለመሄድ በሊቢያ በኩል የሚያቋርጡ ሲሆን፤ በቆይታቸውም እስርና እንግልት ይጠብቃቸዋል። ይህ ሁኔታ በሊቢያ ካለው የእርስ በርስ ግጭት ጋር ተያይዞ እንደከፋ ሪፖርቶች ያሳያሉ።

" ያሉበት ሁኔታ አስከፊ ስለሆን አገራት ስደተኞቹን በማስወጣት ሊረባረቡ ይገባል" በማለት የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መርጅያ ድርጅት የሊቢያ ቢሮ ኃላፊ ጂን ፓውል ካቫሊየሪ ገልፀዋል።