በቨርጂኒያው ጥቃት የተገደሉ 12 ሰዎች ማንነት ይፋ ተደረገ

የተኩስ ልውውጡ የተካሄደበት ህንፃ Image copyright Reuters

በአሜሪካዋ ቨርጂኒያ ግዛት በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ በተከፈተ የተኩስ እሩምታ የተገደሉ የ12 ሰዎች ስም ዝርዝር የከተማዋ ባለሥልጣናት ይፋ አደረጉ።

አውታር - አዲስ የሙዚቃ መሸጫ አማራጭ

ወደ ለንደን የሚሄደው አስደናቂው የትራምፕ ጓዝ

የከተማዋ አስተዳዳሪ የሆኑት ዴቭ ሃንሰን እንዳሉት 11ዱ የአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሠራተኞች ሲሆኑ አንዱ ደግሞ ኮንትራክተር ነው። የአካባቢው ባለሥልጣናት አንድ የፖሊስ ባልደረባ መጎዳቱንም ተናግረዋል።

ጥቃት አድራሹ ከፖሊስ ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርጎ ከመገደሉ በፊት ያገኘው ሰው ላይ በሙሉ ተኩስ ሲከፍት ነበር።

ፖሊስ እንዳለው፤ ተጠርጣሪው በከተማዋ የባህር ዳርቻ ለረዥም ጊዜ ያገለገለና በሥራ ላይ የነበረ የመንግሥት ተቀጣሪ ሲሆን፤ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑትም የራሱ ባልደረቦች መሆናቸው ታውቋል።

ፖሊስ ጥቃት አድራሹን ''ደስታ የራቀው'' ሲል የገለጸው ሲሆን ዲዋይን ክራዶክ በሚል መጠሪያ ሥም እንደሚታወቅ ጨምሮ አስታውቋል።

የጥቃቱ ሰለባዎች እነማን ናቸው?

ጥቃቱ የተፈፀመው የቨርጂኒያ የባህር ዳርቻ ከተማ አስተዳደር ሕንፃዎች በሚገኙበት ስፍራ ሲሆን፤ ጥቃት መድረሱ አንደተሰማ ፖሊስ በአካባቢው ደርሶ ወደስፍራው የሚገቡና የሚወጡትን በማገድ ሠራተኞቹን ከህንፃው አስወጥቷል።

እንደ የፖሊስ ኃላፊው ጀምስ ሴሬቫ ከሆነ፤ ከሟቾቹ መካከል አንዱ ከመኪናው ውጪ የተገደለ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ ግን በህንፃው ውስጥ ሳሉ ተገድለዋል። አራት የፖሊስ ባልደረቦች ወደ ህንፃው በመግባት ጥቃት አድራሹን በማግኘት ወዲያው የተኩስ ልውውጥ ተደርጎ መገደሉንም ገልፀዋል።

ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ስደተኞች ከሊቢያ ወደ ጣልያን ተወሰዱ

ፖሊስ በጥቃቱ የተገደሉ 11 የከተማ አስተዳደር ሠራተኞች ስምን ዝርዝር አሳውቋል። ከሟቾቹ መካከል ሮበርት ዊሊያም እና ክርስቶፈር ራፕ ይገኙበታል። ሮበርት የተሰኘው ግለሰብ በከተማ አስተዳደር ውስጥ ለ41 ዓመታት ያገለገለ ሲሆን ክርስቶፈር ደግሞ ሥራ ከጀመረ ገና 11 ወራትን ብቻ እንዳስቆጠረ የከተማዋ ኃላፊዎች ተናግረዋል።

ፖሊስን ጨምሮ አራት ሰዎች መጎዳታቸው የታወቀ ሲሆን የጉዳታቸው መጠን ግን አልተገለፀም።

ጥቃት አድራሹ ማነው?

የ40 ዓመት ጎልማሳው ጥቃት አድራሽ፤ በከተማ አስተዳደር ውስጥ መሃንዲስ ሆኖ የተቀጠረ ሲሆን ለ15 ዓመታት አገልግሏል። እንደ ኤፒ ዘገባ ከሆነ፤ ግለሰቡ በአሜሪካ ጦር ኃይል ውስጥ ያገለግል የነበረ ሲሆን ጉረቤቶቹም ''ፈገግ የማይል'' ሲሉ ይገልጹታል።

አንዳንድ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ጥቃት አድራሹ በቅርቡ ከሥራው ተባሯል ወይም ሊባረር ነበር ሲሉ ዘግበዋል። የከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ግን ግለሰቡ በወቅቱ በሥራ ገበታው ላይ እንደነበር እና ወደ ህንጻው ውስጥ መግባት የሚያስችል መታወቂያ ነበረው ብለዋል።

ጥቃት አድራሹ ጥቃቱን ለመሰንዘር ምን እንዳነሳሰው ፖሊስ አልገለጸም። ይህ ይሁን እንጂ ግለሰቡ በቅርቡ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን በሕጋዊ መንገድ ስለመግዛቱ ሪፖርቶች እየወጡ ነው።

ተያያዥ ርዕሶች