የስዊዝ ፍርድ ቤት ለካስተር ሰሜንያ ፍርድ ሰጠ

ካስተር ሰሜንያ Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ሰሜንያ የኦሎምፒክ 800 ሜትር ሁለት ጊዜ አሸናፊ ነች

ካስተር ሰሜንያ የቴስቴስትሮን መጠኗን ለመቀነስ መድሃኒት መውሰድ አያስፈልጋትም ሲል የስዊዝ ፍርድ ቤት የዓለም አቀፉን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕግን ላልተወሰነ ጊዜ አገደ።

ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቴስቴስትሮን ለሴት ሯጮች ከፍተኛ ጉልበት ስለሚሆን እንደ ሰሜንያ ያሉ ይህ ሆርሞን በከፍተኛ መጠን ያላቸው ሴት ሯጮች በውድድር ፍትሃዊ ያልሆነ ብልጫ ያሳያሉ በሚል ነው የቴስቴስትሮን መጠን በመድሃኒት መገደብ አለበት የሚል ህግ ያወጣው።

የ800 ሜትር ኦሎምፒክ ሻሚፒዮን የሆነችው የ28 ዓመቷ ደቡብ አፍሪካዊት ሯጭ ካስተር ሰሜንያ 'ቴስቶስትሮን' መጠንን ለመቀነስ መድሃኒት መውሰድ አለብሽ የሚለውን የዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌደሬሽን ውሳኔ በመቃወም ጉዳዩን ወደ የስፖርት የግልግል ዳኝነት ተቋም (ካስ) ወስዳዋለች።

ፆታዋ ያከራከረው ሯጭ በፍርድ ቤት ተረታች

ደቡብ አፍሪካዊቷ ሯጭ ለፍርድ ቤት ይግባኝ አለች

ጉዳዩን ሲመለከት የነበረው የስፖርት የግልግል ዳኝነት ተቋም (ካስ)ጥያቄዋን ውድቅ አድርጎባት ነበር።

የካስን ውሳኔ ተከትሎ "ላለፉት አስርት ዓመታት ዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ከዓላማዬ ሊያደናቅፈኝ ሞክሯል፤ ይሁን እንጂ ይህ ጠንካራ እንድሆን አድርጎኛል፤ ተቋሙ ያስተላለፈው ውሳኔም ከዓላማዬ ሊያቆመኝ አይችልም።" ያለችው ሰሜንያ፤ ጉዳዩን ወደ ስዊዘርላንድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመውሰድ ይግባኝ እንደምትል አስታውቃ ነበር።

እንዳለችውም ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የስዊዚ ፍርድ ቤት ካስተር ሰሜንያ የቴስቴስትሮን መጠኗን ለመቀነስ መድሃኒት መውሰድ አያስፈልጋትም በማለት የዓለም አቀፉን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕግን ላልተወሰነ ጊዜ አግዷል።

ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በኋላ ''የፍርድ ቤቱን ዳኞች ማመስገን እፈልጋለሁ። ከአሁን በኋላ በነጻነት መወዳደር እችላለሁ።'' ብላላች ሰሜንያ።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ