ኔይማር ደፍሮኛል ብላ የከሰሰችው ሴት ብራዚል ቲቪ ላይ ቀርባለች

እግር ኳሰኛው ኔያማር Image copyright Getty Images

ዓመቱ የኔይማር አይመስልም፤ ብዙዎችን እጅ በመዳፍ ባስያዘ ገንዘብ ከባርሴሎና ወደ ፒኤስጂ ያቀናው በጉዳት ምክንያት በርካታ ጨዋታዎችን መጫወት ሳይችል ቀርቷል።

አልፎም ማንቸስተር ዩናይትድ ክለቡ ፒኤስጂን ከቻምፒዮንስ ሊግ ሲያሰናብት ፍትሐዊ ያልሆነ ፍርድ ተሰጥቷል ብሎ በመቃወሙ በአውሮጳ እግር ኳስ አስተዳዳሪ ቅጣት ተጥሎበታል።

የብራዚል አሠልጣኝ የሆኑት ቲቶ አምበልነቱን ከ27 ዓመቱ ኔይማር ነጥቀው ለቡድን አጋሩ የሰጡት በያዝነው ወር ነው።

ኔይማር የቀረበበትን ወሲባዊ ትንኮሳ ክስ አጣጣለ

ዕለተ ረቡዕ ሃገሩ ብራዚል ከኳታር ጋር በነበራት ጨዋታ ጉዳት ደርሶበት ከሜዳ ሲወጣ ለኮፓ አሜሪካ እንደማይደርስ ታውቋል።

አሁን ደግሞ ኔይማር አስገድዶ ደፍሮኛል ያለች ሴት ብራዚል ውስጥ ቲቪ ላይ ቀርባ ደረሰብኝ ያለችውን በደል አሰምታለች።

ናጂላ ትሪኒዳዴ የተሰኘችው ይህች ሴት ባለፈው አርብ ነበር ኔይማር አስገድዶ ደፍሮኛል ስትል ክስ ያሰማችው።

ተጨዋቹ ክሱ ሃሰት ነው፤ እንደውም እነሆ በዋትስአፕ ያወራነው ሲል ከከሳሹ ጋር የተለዋወጠውን መልዕክት በማሕበራዊ ድር አምባ ገፆቹ ይፋ አድርጓል።

ከሳሿ ኔይማር ፓሪስ የሚገኝ አንድ ሆቴል ጠርቶኝ ነው የደፈረኝ ትላለች። መጀመሪያ ግን በፈቃደኝት እርሱ ወደ ሚገኝበት ሆቴል እንደደሄደች በመጠቆም።

የሳዑዲውን ልዑል መስሎ ሲያጭበረብር የነበረው ግለሰብ ታሰረ

የቴሌቪዥን ዝግጅቱ አቅራቢ 'የደረሰብሽ ጥቃት ነው ወይስ አስገድዶ መድፈር?' ሲል ለጠየቃት ምላሽ የሰጠችው ትሪኒዳዴ 'ጥቃትትም ደርሶብኛል፤ ተደፍሬያለሁም' ስትል መልሳለች።

ኔይማር በፅሁፍ መልዕክት ልውውጣቸው ከምታውቀው በተለየ በጣም ግልፍተኛ ሆኖ እንደጠበቃት ተናግራለች።

የጠባቸው መንስዔም 'በኮንዶም ወይስ ያለኮንዶም?' እንደሆነ አልሸሸገችም።

ኔይማርም ሆነ ወኪሉ እንዲሁም አባቱ ውንጀላው ውሃ አያነሳም፤ ሃሰት ነው ሲሉ አጣጥለውታል።

ኔይማር ከአስገድዶ መድፈሩ ክስ በተጨማሪ ከከሳሿ ጋር ያደረገውን የፅሁፍ ልውውጥ ያለፈቃዷ በመለጠፉ ሊከሰስ እንደሚችል ይጠበቃል።

የአፍሪካ እግር ኳስ ቅሌት