በዓመት 115 ሚሊዮን ህፃናት ወንዶች ያለዕድሜቸው ጋብቻ ያደርጋሉ

የወንዶች ያለዕድሜ ጋብቻ Image copyright Getty Images

ያለዕድሜ ጋብቻ ሲባል አብዛኛውን ጊዜ ጭንቅላታችን ላይ የሚመጣው በዕድሜ ያልጠኑ ሴቶች ከትልልቅ ወንዶች ጋር የሚያደርጉት ጋብቻ ነው።

ነገር ግን ይህ በህፃናት ሴቶች ብቻ ሳይሆን በወንዶችም እንደሚከሰት በቅርቡ የተባበሩት መንግሥታት የህፃነት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ያወጣው ሪፖርት ያሳያል።

ምንም እንኳን ከወንዶች ልጆች ይልቅ ሴት ህፃናት በከፍተኛ ሁኔታ የሚጋለጡ ቢሆንም ወንዶች ልጆችም ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እንዳለው ሪፖርቱ በተጨማሪ ይፋ አድርጓል።

"ምንም እንኳን በህፃንነታቸው የሚያገቡ ወንዶችና ሴቶች ባላቸው አካላዊና ማህበራዊ ልዩነት ለተመሳሳይ አደጋ ባይጋለጡም ይህ ልምድ ግን እድሜያቸው ያልደረሱ ህፃናትን መብት መጣስ ነው" በማለት በህፃናት ወንዶች ዘንድ ያለውን ያለዕድሜ ጋብቻ ሪፖርት የፃፉት ኮለን ሙሬይ ጋስተን፣ ክርስቲና ሚሱናስና ክላውዲያ ካባ ገልፀዋል።

የተነጠቀ ልጅነት

የኢትዮጵያ ፊልም ወዲያና ወዲህ

ድብቅ የህጻናት ጋብቻዎች

ጥናቱም ያለዕድሜ ጋብቻ ያስከተለባቸውን የኑሮ ፈተና የዳሰሰ ሲሆን "ልክ እንደ ህፃናት ሴቶች ወንዶችም ህፃናት ዕድሜያቸው የማይፈቅደውን የትልቅ ሰው ኃላፊነት ለመሸከም እንደሚገደዱም" ያስረዳል።

ጋብቻውም በልጅነት ወላጅነትን እንዲሁም የቤታቸውን ቀዳዳ ለመሙላት ሲባል ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫናና እንደሚሸከሙ የሚያስረዳው ሪፖርቱ እንዲሁም ትምህርትና ሌሎች ነገሮችንም በህፃንነታቸው ተነፍገው እንደሚያድጉ ሪፖርቱ ጨምሮ ያትታል።

እንደ ዩኒሴፍ መረጃ በዓለም ላይ በሁለቱም ፆታዎች 765 ሚሊዮን ህፃናት ያለ ዕድሜያቸው የሚጋቡ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 115 ሚሊየኖቹ ህፃናት ወንዶች ናቸው።

ምርምሩ የ82 ሃገራትን መረጃ የወሰደ ሲሆን፤ ከ20 እስከ 24 እድሜ ካሉ ወንዶች ውስጥ 4.5% ከ18 ዓመት በታች ያገቡ መሆናቸውን ያሳያል።

Image copyright Getty Images

በሪፖርቱ መሰረት የላቲን አሜሪካና የካሪቢያን ደሴቶች በ8.3% በአንደኛነት ሲቀመጡ፤ የእስያና ፓስፊክ ሃገራት በ5.9 % ሁለተኛውን ሲይዙ፤ የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ከ2% ባነሰ ቁጥር በትንሽነቱ ይጠቀሳሉ።

በአንደኛነት የሴንትራል አፍሪካ ሪፐብሊክ በ27.9% ስትመራ፤ ኒካራጓ በ19.4%ና ማዳጋስካር በ12.9% ተከታትለው የሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

ያለዕድሜ ጋብቻ ከሚፈፀምባቸው ቁጥራቸው ከፍተኛ ከሆኑት ሃያ ሃገራት መካከል ሰባቱ ላቲን አሜሪካ ይገኛሉ።

ከመቶ ቢሊዮን ብር በላይ ጭማሪ ያሳየው የኢትዮጵያ በጀት

ለዚህም እንደ ምክንያትነት የሚጠቀሱት በባህሉ ሰርፀው የገቡ የፆታ ሚናዎች በህፃንነታቸው እንዲያገቡ ጫና እንደሚያደርግባቸው በኒካራጓ የሚገኘው የዩኒሴፍ ተወካይ ማሪያ ሊሊ ሮድሪገዝ ይናገራሉ።

ከዚህም በተጨማሪ በማህበረሰቡ ለወንድነት የተሰጠው ትርጉም ህፃናት ወንዶችም ቢሆኑ "ወንድነታቸውን" ለማስመስከር ሴቶችን ማስረገዝ እንዳለባቸው እንዲያምኑ እንዳደረጋቸው ባለሙያው ይገልፃሉ።

ድህነት፦

ሌላኛው ወንዶች በህፃንነታቸው ያገባሉ ተብሎ እንደ ምክንያት የተጠቀሰው የትምህርትና የግንዛቤ እጥረት ሲሆን " ትምህርት ቤት በህፃንነታቸው የሚገቡ ወንዶች ወደ ትዳር አይገቡም" የሚሉት ሮድሪገዝ በላቲን አሜሪካ ባሉ ሃገራት የትምህርት ስርአት ውስጥ የ ስነ ተዋልዶና ፆታዊ ግንኙነት በጥልቀት አለመሰጠት እንዲሁም በቤታቸው በነዚህ ጉዳዮች ላይ ምንም አይነት ንግግር ባለመኖሩ ክፍተትን እንሚፈጥር ይናገራሉ።

በአመት አንዴ ብቅ የምትለው ከውሃ በታች ያለችው መንደር

ከዚህም በተጨማሪ ከደሃ ቤተሰብ የሚወለዱ ልጆች ነፃነታቸውን በቶሎ ለማረጋገጥ ወደ ትዳር እንደሚያመሩም ጥናቱ እንደሚያሳይ ማሪያ ገልፀዋል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ