1 ዩኒት ደም እስከ 5 ሺህ ብር ይሸጥ የነበረበት ጊዜ

ደም ለጋሾች በኢትዮጵያ ደም ባንክ

ድሮ ሠው ታሞ ደም ያስፈልገዋል ከተባለ ዙሪያው ገደል ነው የሚሆነው። አስታማሚም ታማሚም ማጣፊያው ሲያጥራቸው የሚያማክሩት ወገን ፍለጋ ወዲያ ወዲህ ሲሉ ማየት የተለመደ ነበር።

ቆፍጠን ብሎ ወደ ደም ባንክ የሄደ ደግሞ ደም ሰጥቶ ሕይወት ለማትረፍ የተሰለፈ ደም ለጋሽ፣ ደም ሸጦ የእለት ጉሮሮው ላይ ቁራሽ እንጀራ ለማኖር የሚጣደፍ 'ነጋዴ'፣ ደም ደልሎ የድርሻውን ሊቦጭቅ ያሰፈሰፈ ደላላ ጋር ይፋጠጣል።

ሕይወትን ለማትረፍ ደም በቀላሉ ማግኘት ዳገት የነበረት ጊዜ ነው ያዘመን። ሩቅ ይመስላል፤ ግን የትናንት ያህል የሚያስታውሱት አሉ።

ጠቅላይ ሚነስትር ዐብይ አህመድ በአክሱም ምን ተጠየቁ?

በሰው ክፋይ ሕይወት መዝራት - የኩላሊት ንቅለ ተከላ

ከ1981 ዓ.ም ጀምሮ ለ79 ጊዜ ደም ለግሷል። የ54 ዓመቱ ጎልማሳ አቶ ሠለሞን በየነ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ሲሆን ኑሮውን የመሰረተው በግል ሥራ ላይ ተሰማርቶ ነው።

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ስር ይተዳደር የነበረው የደም ባንክ በሚገኝበት ስታዲየም ዙሪያ የደም ሽያጭ ገበያ ደርቶ በነበረበት ወቅት ደማቸውን ለመሸጥ ከተሰለፉ ጋር ተጋፍቶ ደሙን በነጻ ይለግስ እንደነበር ያስታውሳል።

ደም ለጋሽ እንዲሆን ያደረጉትን አጋጣሚዎችም እንዲሁ አይረሳቸውም።

Image copyright Ethiopian Blood bank

ክፉ አጋጣሚ በጎ ትምህርት

አንደኛው አጋጣሚ ቀይ መስቀል በጎ ፈቃደኛ በመሆን አምቡላንስ ላይ ይሠራ በነበረበት ወቅት በጽንስ መቋረጥ የተጎዳች ሴት ደም አጥታ ሕይወቷ ሲያልፍ መመልከቱ ነው።

ሌላው ደግሞ ሆስፒታል ውስጥ በተመሳሳይ ምክንያት ብዙ ደም ፈሷት የነበረች ሴት ደም ተሰጥቷት ሕይወቷ ሲተርፍ መመልከቱ ነበር።

እነዚህ ሁለት አጋጣሚዎች ያለ ምንም ማቅማማት ለረዥም ዓመታት ደም እንዲለግስ የሁል ጊዜ የሕሊና ደወል እንደሆነለት ይናገራል።

የኢትዮጵያ ፊልም ወዲያና ወዲህ

«የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ

እንደ ሠለሞን ለዓመታት ከለገሱና ካነጋገርናቸው የደም ባንክ ሠራተኞች መረዳት እንደሚቻለው ደም እስከ አምስት ሺህ ብር ይሸጥ ነበር። ምንም እንኳ በሕክምና በሦስት ወር አንድ ጊዜ ብቻ ደም መስጠት የሚመከር ቢሆንም በሳምንት ሦስት ጊዜ ደማቸውን የሚሸጡ ምንዱባን እንደነበሩ ሠለሞን ያስታውሳል።

ስታዲየም ዙሪያ ደም ይሸጥ በነበረበት ወቅት ደም ሻጮችና ገዥዎች ብቻ ሳይሆኑ ደላሎችም የገበያው ተዋናዮች ነበሩ።

"የበሬ ንግድ ይባል ነበር" ሲል ያስታውሳል። የደም ሽያጭ ደርቶ የነበረው ደም ባንክ የምትክ ደም አሰራርን ይከተል በነበረበት ወቅት ነበር።

ለአንድ ታማሚ ይህን ያህል ደም ያስፈልጋል ሲባል፤ የሚያስፈልገውን ያህል ደም ሊሰጡ የሚችሉ የቤተሰብ አባላት ወደ ደም ባንክ ሄደው ደም ይሰጣሉ። በምትኩ ደም ባንክ ለበሽተኛው የሚያስፈልገውን የደም አይነት ታማሚው ለሚገኝበት ሆስፒታል ይልካል።

Image copyright Getty Images

ደም ሽያጭ እንዴት ቆመ?

በ2004 እንዲሁም በ2003 ዓ.ም የደም ባንክ ደጃፍ በደም ገዥና ሻጭ እንዲሁም ደላላ ግርግር የሞቀ ነበር። በእነዚያ ዓመታት ሆስፒታሎች ደግሞ እየተስፋፉ ነበሩ።

የሆስፒታሎቹ ደም ፍላጎት ሲጨምር የደም ሽያጭ ገበያ እንዴት ሊደራ እንደሚችል የተረዳው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በቀይ መስቀል ስር የነበረውን ደም ባንክ ተጠሪነት በቀጥታ ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አድርጎ ነገሮችን ለውጦ ምትክ ደም አሠራር እንዲቀር አደረገ።

በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ በአጠቃላይ 42 የደም ባንኮች ይገኛሉ።

ከእነዚህም የሐረርና የጅግጅጋ ደም ባንኮች ዛሬም የምትክ ደም አሠራርን እንደሚከተሉ አቶ ያክጋል ባንቴ፣ የብሔራዊ ደም ባንክ ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣ አልሸሸጉም። አጠቃላይ ከሚሠበሠበው ደም አንድ ሦስተኛው አዲስ አበባ ላይ ሲሰበሰብ ሁለት ሶስተኛው ደግሞ በክልል ደም ባንኮች የሚሠበሰብ ነው።

ከወለደች ከ30 ደቂቃዎች በኋላ ለፈተና የተቀመጠችው እናት

እንደ ሠለሞን ያሉ ለጋሾች ምስጋና ይግባቸውና ደም ባንክ ዛሬ ላይ የምትክ የደም አሠራርን ትቶ ደም ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ያለምትክ ደም እየሰጠ ይገኛል።

በደም ልገሳ ላይ መሻሻሎች ቢኖሩም ስኬት ላይ ነን ማለት የሚቻልበት ደረጃ ላይ አልተደረሰም ይላሉ የብሔራዊ ደም ባንክ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ።

ምክንያቱ ደግሞ የዓለም ጤና ድርጅት ከአንድ አገር አጠቃላይ ሕዝብ አንድ በመቶ የሚሆነው በፈቃደኝነት ደም የሚለግስ መሆን ይገባዋል ቢልም የኢትዮጵያ እውነታ ከዚህ የራቀ መሆኑን በመጥቀስ ነው።

ይህ ማለት ሳይንሱ እንደሚለው ከኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ ሚሊዮን የሚሆነው በበጎ ፈቃደኛነት በዓመት ሦስት ጊዜ ደም ቢለግስ ሦስት ሚሊዮን ደም ሊገኝ ይችል ነበር። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ደም ባንክ እየሰበሰበ ያለው በዓመት ሁለት መቶ ሺህ ደም ብቻ እንደሆነ ኃላፊው ይናገራሉ።

"በጣም በጣም ታች ነን ያለነው፤ ይህ ምንም ነው" በማለት ሁኔታውን ይገልፃሉ። ነገር ግን 2011 ዓ.ምን በምሳሌነት በማንሳት ምንም የደም እጥረት እንዳላጋጠመ ያስረዳሉ። እጥረቱ ያልተፈጠረው ግን ሆስፒታሎች በሙሉ አቅማቸው እየሰሩ ባለመሆኑ ነው።

በሌላ በኩል እጥረት የለም ማለት የሆስፒታሎች የደም ፍላጎት በመጠንም በዓይነትም ደም ባንክ አሟልቷል ማለት እንዳልሆነ ይልቁኑም የኔጋቲቭ ደም አይነቶች እንዲሁም የፕላትሌት እጥረት መኖሩን ይገልፃሉ።

ስለ ግንቦት 27፤ 1983 የጎተራው ፍንዳታ ምን ያስታውሳሉ?

ከኔጋቲቭ ደሞችም በይበልጥ በተለያየ ምክንያት እጥረት ያለው ለማንኛውም ህመምተኛ ሊሠጥ የሚችለው 'ኦ ኔጋቲቭ' የደም ዓይነት ነው። የዚህ የደም ዓይነት እጥረት የሚፈጠረው ደግሞ ይህ የደም አይነት ያላቸው ሠዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑና ለማንኛውም ሠው መስጠት የሚችል ደም በመሆኑ ነው።

በተጨማሪም ደግሞ በአስገዳጅ ጊዜ ብቻም ሳይሆን ሆስፒታሎች ቀድመው የበሽተኞችን ደም ሳይመረምሩ በመቅረት እንዲሁ ኦ ኔጋቲቭን መስጠታቸው እጥረት እንዲፈጠር ማድረጉን አቶ ያረጋል ያስረዳሉ።

የኦ ኔጋቲቭ የደም እጥረትን ለመፍታት በማሠብ የደም ባንክ ባለፈው ሠኔ 2 ቀን 2011 ዓ.ም የዚህ ደም በጎ ፈቃደኛ ለጋሾች ቡድን እንዲመሠረት ያደረገ ሲሆን ከ800 በላይ የሚሆኑ ኦ ኔጋቲቭ ሰዎች በእለቱ ግንዛቤ ለመፍጠር የእግር ጉዞ አድርገዋል።

Image copyright Mikhail Tereshchenko

"ለእናታችን ደም ስጥልን እኛ እንፈራለን"

ወጣት ጥበቡ ቢያድግ ከ17 ዓመታት በፊት ሰዎች ደም ሲለግሱ አብሮ በመሔድ በድንገት ነበር ደም መስጠት የጀመረው። እስከ አሁን 38 ጊዜ ለግሷል። ኦ ኔጋቲቭ ነው።

ደሙ ለማንም እንደሚሆን ከተረዳበት ጊዜ ጀምሮ በፍቃደኝነት ለመለገስ ወደኋላ ብሎ አያውቅም። የደም ባንክም የኦ ኔጋቲቭ ደም እጥረት ሲያጋጥም ከሚደወልላቸው ሰዎች መካከልም አንዱ ነው።

እሱና ጓደኞቹ በቡድን ሆነው ደም ለመስጠት ደም ባንክ ሲሄዱ በር ላይ ደላሎች 'ገንዘብ ማግኘት ስትችሉ ለምን በነፃ ትሰጣላችሁ' እያሉ ያዋክቧቸው እንደነበር ጥበቡ ያስታውሳል።

እሱና ጓደኞቹ ግን ከገንዘብ ይልቅ ከቀይ መስቀል የተሰጣቸውን 'እኔ ደም ለጋሽ ነኝ'፣ 'ደም ለጋሽ ጀግና ነው' የሚሉ ቲሸርቶችን ለብሰው አደባባይ መውጣት ኩራታቸው ነበር።

በዚህም ደም ለጋሽ እንደሆኑ ያወቁ በርካታ ሰዎች ለሕመምተኛ ቤተሰባቸውና ወዳጃቸው ደም እንዲሰጡላቸው ይጠይቋቸው ነበር።

በዚህም የማይረሳው አጋጣሚም አለ። አንዲት ጎረቤቱ ቀዶ ሕክምና ሊደረግላቸው ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ገብተው ልጆቻቸውም ወንድሞቻቸውም ደም መስጠት ይፈራሉ። ከዚያም ጥበቡን እባክህ ይሉታል።

ደም መስጠት ምንም ችግር እንደሌለውና እነርሱም ሊሰጡ እንደሚችሉ ቢነግራቸውም ስለፈሩ ልጆቻቸው ለእናታቸው ደም መስጠት አልቻሉም ይላል።

በመጨረሻ ለእናታቸው ደም እንደሚሰጥ ነገር ግን በቀጣይ እሱን አይተው እነርሱም ለጋሽ እንዲሆኑ ቃል አስገባቸው።

አምስት ጂ ኢንተርኔት ምን አዲስ ነገር አለው?

የወንዶች ያለዕድሜ ጋብቻ

እርሱ ለታማሚዋ እናት የሚያስፈልገውን ደም ሰጠ፤ እናትም ተረፉ። ጥበቡም ከቤተሰቡ ጋር ዘመድ ሆነ። የሴትየዋ ልጆች ግን ከዛሬ ነገ አብረንህ ሄደን ደም እንለግሳለን እያሉ ቆይተው በመጨረሻ ደም መስጠት እንደማይችሉ ነገሩት።

"ገርሞኝ ዝም አልኩ" ይላል ጥበቡ ሁኔታውን አስታውሶ "አንዳንዱ ደሙ የሚያልቅ ወይም የሚታመም ይመስለዋል፤ አንዳንዱ ደግሞ ደም ማነስ አለብኝ ደም አይነቴን አላውቀውም ይላል።"

ከወጣትነት እስከ...

የላብራቶሪ ቴክኒሻኑ ዳዊት ፍቅሩ የ37 ዓመት ወጣት ነው። ከ1995 ጀምሮ የበጎ ፈቃደኛ የደም ለጋሽ መሆኑን ይናገራል። የደም አይነቱ ደግሞ ብዙ ጊዜ የሚያጥረውና ለማንኛውም ሠው የሚሰጠው ኦ ኔጋቲቭ ነው።

ኦ ኔጋቲቭ መሆኑን ያወቀው ቀይ መስቀሎች በሚማርበት ትምህርት ቤት ተገኝተው በፍቃደኝነት ደም ይሰበስቡ በነበረበት ወቅት እንደነበር ያስታውሳል። ስለ ደም ልገሳ ቢያውቅም ስለ ኦ ኔጋቲቭ ደም የሚያውቀው ነገር ግን አልነበረም።

ዳዊት ስለ ኦ ኔጋቲቭ ደም ካወቀ በኋላ ግን ከደም ባንክ ቢደወልለትም ባይደወልለትም እስከ አሁን 38 ጊዜ ደም ሰጥቷል።

ዳዊት እርሱ በሚለግሰው ደም የሰው መርዳት በመቻሉ ደስተኛ ነው "የእኔ ደም ለማንም መሆን እንደሚችል አውቃለሁኝ። ስለዚህ ማንም ቢድንበት ደስታዬ ነው" ይላል።

ምትክ ደም በሚጠየቅበት ወቅት ለዓመታት ለሚያውቃቸውና በሚያውቃቸው ሰዎች ለመጡበት በርካታ ሠዎች ደሙን ሰጥቷል። በዚህ ረገድ ብዙ አጋጣሚዎችን ያስታውሳል።

እርሱ 'ተፈላጊውን' የደም ዓይነት በነፃ ሊለግስ በፈቃደኝነት በተደጋጋሚ ሲሄድ፤ ስታዲየም ዙሪያ በደም እስከ አምስት ሺህ ብር ይቸበቸብ እንደነበር እንደሚያስታውስ ይናገራል።

የበርካታ ዕፅዋት ከምድረ-ገፅ መጥፋት አሳሳቢ ሆኗል

ብሩ አያጓጓም ነበር ወይ? ለዳዊት ያነሳነው ጥያቄ ነበር። ገንዘብ ተሠርቶ በማንኛውም ጊዜ ሊገኝ ስለሚችል ዳግም የማይገኝ የሠው ህይወትን ማትረፍ ትልቅ እርካታ እንዳለውና ያኔ ደም ሲሸጥ ሲያይ እጅጉን ያዝን እንደነበር ያስታውሳል።

"ደም አጥተው የሚሞቱት የእኔ እናት፣ አባቴ ወይንም ጓደኛዬ ቢሆን ብሎ የሚያስብ ሰው ደም ለመሸጥም ሆነ ለመደለል አያስብም " ይላል።

የበጎ ፈቃደኛ ለጋሾች ጥምረት

ወጣት ፀደቀ ሞገስ ለ57 ጊዜ ደም ለግሷል። ሦስት በጎ ፈቃደኛ የደም ለጋሾች ቡድንም እንዲቋቋም አስተባብሯል።

እሱና ጓደኞቹ ቀደም ሲል ደም ይለግሱ የነበረ ቢሆንም በቡድን ደም መለገስ የጀመሩት የ1997ቱን ፖለቲካ ቀውስ ተከትሎ በተፈጠረው ችግር በጊዜው ከፍተኛ ደም እጥረት በነበረበት ወቅት ነበር።

በወቅቱ የደም እጥረት ስለነበር የደም ሽያጭ ገበያውም ደርቶ እንደነበር ፀደቀ ያስታውሳል።

ሠዎችን በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሽ ማድረግ ግድ እንደሆነ የሚናገረው ፀደቀ ብዙዎችን ማሰባሰብ የቻለው ቤተክርስቲያን አካባቢ እንደሆነ ይገልፃል።

ለእናታቸው ወይም ለአባታቸው ደም አንሰጥም ያሉ ሰዎች ፀደቀንም አጋጥመውታል። በብዙ ሰዎች ዘንድ ደም ስለመስጠት ግንዛቤ አለመኖሩ ደም ለጋሽ እንዳይሆኑ አድርጓል ይላል ፀደቀ።

በሌላ በኩል እንደሱ ያሉ ለዓመታት ያለማቋረጥ ደም የሚለግሱ ሰዎች በሰብዓዊነት ሳይሆን በሆነ ጥቅም እንደሆነ የሚያስቡም ብዙ መሆናቸውን ይናገራል።

"በእኛ ደም እየበላ" መባሉንም ፀደቀ ያነሳል።

"ባለቤቴ ከምትሞት እኔ ደም ሰጥቻት ልሙት"

ሲስተር አሰጋሽ ጎሳ በብሔራዊ ደም ባንክ የትምህርትና ቅስቀሳ ባለሙያ ሲሆኑ የበጎ ፈቃደኛ የደም ለጋሽም ናቸው። በግምት ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ ለ72 ጊዜ ደም ለግሰዋል።

በመጀመሪያ ጊዜ ደም የሰጡበትን አጋጣሚ ሁሌም ያስታውሳሉ። የምትክ ደም አሠራር በነበረበት ወቅት ነው። ባለቤቱ ሆስፒታል የተኛችና የሁለት ሠው ደም እንዲያመጣ የተነገረው ከገጠር የመጣ አንድ ሰው "ባለቤቴ የልጆቼ እናት ከምትሞት እኔ ደሜን ሰጥቻት ልሙት" ይላቸዋል።

ሲስተር አሠጋሽ ሠውዬው ደም መስጠት እንደሚገድል እንዳሰበ ተረድተዋል። በጣም ተጨናንቆ አዝኖ ነበር ይላሉ በወቅቱ የነበረውን መለስ ብለው ሲያስታውሱ።

ሠውዬው የተፃፈለት ሁለት ዩኒት ደም እንዲያመጣ ስለነበር አንደኛውን ሲስተር አሠጋሽ በበጎ ፈቃደኝነት ሲሰጡ ሌላኛውን ሌሎች የደም ባንኩ በጎ ፈቃደኞች ከሠጡት እንደተገኘለት ያስታውሳሉ።

"መነሻዬ ያ ባለቤቱን የሚወድ ሰው ነው" የሚሉት ሲስተር አሰጋሽ ለሚስቶቻቸው ደም ላለመስጠት የሚያንገራግሩ ባሎች አጋጥሟቸዋል። የምትክ ደም አሠራር ለደም ባንኩ ከባድ ጊዜ ለሰራተኞቹም አስቸጋሪ እንደነበር ይገልፃሉ።

እንደ ገቢ ማግኛ በቀን ሁለት ጊዜ ደም የሚሠጡ፣ የጤናቸውን ሁኔታ ደብቀው ደማቸውን የሚሸጡም እንደነበሩ ይናገራሉ።

የሱዳንን መፃዒ ዕድል የሚወስኑት የጦር አበጋዝ

አንድ ሠው ክብደቱ 45 ኪሎ፣ እድሜው ከ18 እስከ 65 ከሆነ፣ ምንም ዓይነት መድኃኒት የማይወስድ ማንኛውም ሠው በየሦስት ወሩ ደም መስጠት እንደሚችል ሲስተር አሠጋሽ ይናገራሉ።

ሌላው ያነጋገርነው ደም ለጋሽ አቶ ዳዊት ተስፋዬ ነው። የስድስት ልጆች አባት የሆነው አቶ ዳዊት ደም መስጠት ከመጀመሩ በፊት ማለትም ተማሪ ሳለ የቀይ መስቀል በጎ ፈቃደኛ ነበር።

በ25 ዓመታት ውስጥ ለ75 ጊዜ ያህል ደም ለግሷል። "እኔ በሰጠሁት ደም ሁለት መቶ የሚሆኑ ሰዎች ተጠቅመዋል ብዬ አስባለሁ" ይላል።

የዓለም የጤና ድርጅት ሀገራት በ2020 ወጣት ዜጎቻቸው በፈቃደኝነት ደም እንዲሰጡ በማድረግ የሀገራቸውን የደም ፍላጎት እንዲያሟሉ ጥሪ ያቀርባል። በአሁኑ ሰአት በዓለም ላይ 80 ሚሊየን ዩኒት ደም የሚሰበሰብ ቢሆንም በተለይ በታዳጊ ሀገራት ከፍተኛ እጥረት መኖሩን ይገልፀዓል

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ