የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ልጆቻቸው 'ሞባይል' እንዳይጠቀሙ የሚያግዱት ለምን ይሆን?

A young boy staring at a tablet Image copyright Getty Images

አሁን ከመዳፋችን ተለይቶ የማውቀውን ተንቀሳቃሽ ስልክን የሚዘውሩ መተግበሪያዎችን [አፕሊኬሽን] የፈጠሩ ሰዎች ልጆቻቸው ከሞባይል ስልክ እንዲርቁ ያደርጋሉ።

የሲሊከን ቫሊ ሥራ ፈጣሪዎች ተብለው ከሚታወቁቱ አብዛኛዎቹ አሁን ትዳር መሥርተው ወላጆች ሆነዋል።

አሁን በሕይወት የሌለው የአፕል ፈጣሪ ስቲቭ ጆብስ 2011 ላይ ልጆቹ ቤት ውስጥ ስልኮቻቸውንም ይሁን ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን ለተወሰነ ሰዓት ብቻ እንደሚጠቀሙ ተናግሮ ነበር።

ኢትዮ ቴሌኮም... ወዴት? ወዴት?

የውጪ ሀገር ጥሪዎች ለምን በኢትዮጵያ ቁጥር ይወጣሉ?

የማይክሮሶፍት ባለቤት እና ፈጣሪ የሆነው ቢል ጌትስም ቢሆን ልጆቹ ለዉሱን ሰዓት ብቻ ወደ 'ሞባይል ስክሪን' ብቅ እንደሚሉ ጠቁመው ነበር። የፌስቡክ ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ፤ አቻምና ለተወለደች ልጁ በፃፈው ደብዳቤ ላይ «ወደ ውጪ ወጥተሽ ተጫወች» የሚል ቀጭን ትዕዛዝ አስፍሮ ነበር።

ለመሆኑ ለምን ይሆን የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ልጆቻቸው ከሞባይል ስክሪን እንዲርቁ የሚፈልጉት?

ኢኮኖሚያዊ ተቃውሞና ያስከተለው ውጤት

ቴክ-ነፃ ልጅነት

የሦስት ልጆች አባት ነው፤ ቴክ ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚሠራው ፒዬር ሎረንት። በርካታ የሥራ ባልደረቦቹም ሆነ እርሱ ልጆቻቸው ከቴክኖሎጂ እንዲርቁ አብዝተው ይመክራሉ።

ልጆቻቸውን የሚሰዱበት አስኳላም ቢሆን 'ልጆቻችሁን ከቴክኖሎጂ አርቁ' ሲል ሁሌም ያስታውሳቸዋል።

«በልጅነትህ ከምታየው ስክሪን ላይ አይደለም ትምህርት መቅሰም ያለብህ። የሰው ልጅ የስሜት ህዋሳቱን ተጠቅሞ ነው ነገሮችን መከወን ያለበት። አእምሮ ነገሮች እንዴት እንደሚሠሩ በሂደት ሊረዳ ይገባል።»

በራስ መተማመን፣ ዲስፕሊን፣ ነፃ አስተሳሰብ፣ የቡድን ሥራ፣ ጥበባዊ አገላለፅ፤ እኒህ ከሞባይል ስክሪን ላይ የማይገኙ ጥበቦች ናቸው ሲል ይከራከራል ሎረንት።

Image copyright Getty Images

ሁለት አባቶች፤ የተለያየ ምክር

ምንም እንኳ የሲሊከን ቫሊ ወላጆች ልጆቻችን ከቴክኖሎጂ መራቅ አለባቸው ብለው ቢከራከሩም፤ ቴክኖሎጂ ለ21ኛው ክፍለ ዘመን አስፈላጊ ነው ሲሉ የሚሞግቱ ወላጆች አልጠፉም።

መርቬ ላፐስ በዘርፉ 'ጥርስ የነቀሉ' ባለሙያ ናቸው። «እርግጥ ነው፤ ቴክኖሎጂ በዝባዥ ነው። ግን እንዴት አድርገን ነው ልንጠቀመው የምንችለው? ምክንያቱም ሕፃናት ቴክኖሎጂን ተጠቅመው ሊበለልፅጉ ይችላሉና። ከቴክኖሎጂ ውጪ ያለውን ዓለም ደግሞ እንዲሁ ማጣጣም አለባቸው።»

ኤርትራውያን ኢሳያስን ለመጣል'#ይበቃል' የተሰኘ እንቅስቃሴ ጀመሩ

የዓለም ጤና ድርጅትም በቅርቡ ሕፃናት ምን ያህል ጊዜ ስክሪን መጠቀም እንዳለባቸው የሚጠቁም መመሪያ አዘጋጅቷል።

እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ያሉ ሕፃናት ብቻቸውን ቴሌቪዥንም ሆነ ሌሎች ስክሪኖችን ማየት የለባቸውም ይላል መመሪያው። አክሎም በቀን ከአንድ ሰዓት በላይ ስክሪን ላይ አፍጥጠው እንዳይቆዩ ይመከራል።

ላፐስ «እኔ ምግብ በማበስልበት ጊዜ ልጆቼ 'ሰሲሚ ስትሪት' የተሰኘውን የልጆች ሾው ይመለከታሉ። ይህ ለአንድ ወላጅ ግልግል ነው። ግን ምን ተማራችሁ ብዬ እጠይቃቸዋለሁ።»

የሕፃናት እና ስክሪን ግንኙነት ጉዳይ አከራካሪነቱ ቢቀጥልም ባለሙያዎች ስክሪን እንጂ ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን መከልከል አስፈላጊ ነው ብለን አናስብም ይላሉ።

ተያያዥ ርዕሶች