በዲሞክራቲክ ኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ስርጭት "እጅግ አስበርጋጊ" ነው ተባለ

በዲሞክራቲክ ኮንጎ 1400 ሰዎች በኢቦላ ቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። Image copyright MARIA SANTTO / FINNISH RED CROSS / IFRC HANDOUT

በሕክምና ምርምር ሥራዎች ላይ ቀዳሚ የሆነው የበጎ አድራጎት ድርጅት ኃላፊ በዲሞክራቲክ ኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ "እጅግ አስበርጋጊ" ነው አሉ።

በኮንጎ 1400 ሰዎች ያህል በኢቦላ ቫይረስ ተይዘው መሞታቸው ታውቋል።

የዌልካም ትረስት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ጄርሚ ፋራር እንዳሉት የተከሰተው ወረርሽኝ ከ2013ቱም ሆነ ከ2016ቱ የከፋ ሲሆን ምንም "የመቆም ምልክት አይታይበትም" ብለዋል።

በሽታው ወደ ጎረቤት ሀገር ኡጋንዳ ተስፋፍቶ አንድ የአምስት ዓመት ህጻን መሞቱ ሲረጋገጥ፤ አያቱ እና እናቱም ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

ይህም በኡጋንዳ በበሽታው የተያዘ ሰው ሪፖርት ሲደረግ የመጀመሪያው ነው።

አሜሪካዊቷ አምስት ልጆቿን የገደለው የሞት ፍርድ አይገባውም ብላለች

ኢቦላ ወደ ኡጋንዳ እየተዛመተ ነው

የኢትዮጵያ ፊልም ወዲያና ወዲህ

የኡጋንዳ መንግሥት እንዳስታወቀው በአሁኑ ሰዓት ሰባት ሰዎች ቫይረሱ ሊኖርባቸው ይችላል በሚል ጥርጣሬ በማቆያ ውስጥ ይገኛሉ።

ዶ/ር ፋራር በመግለጫቸው ላይ እንዳሉት "አስበርጋጊ ነው ነገር ግን አስደናቂ አይደለም" ብለዋል።

አክለውም ሌሎች አዳዲስ ታማሚዎች እንደሚኖሩ በመግለፅ ሙሉ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብንና የሀገሪቱ መንግሥት ምላሽን ይጠይቃል ብለዋል።

"ዲሞክራቲክ ኮንጎ ይህንን ብቻዋን ልትጋፈጠው አትችልም" ሲሉም ያክላሉ።

ኢቦላ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወደ ኡጋንዳ መዛመቱ ከተሰማ በኋላ ሩዋንዳ በድንበሮቿ ላይ የኢቦላ በሽታ ቁጥጥርን አጠናከረች።

ሩዋንዳ በምዕራብ በኩል ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፤ በሰሜን በኩል ደግሞ ከኡጋንዳ ጋር ትዋሰናለች።

የሩዋንዳ የጤና ጥበቃ ሚንስትር ለቢቢሲ ሲናገሩ፤ ''ሩዋንዳ በጎረቤት ሃገራት የተከሰተውን የኢቦላ ወረርሸኝ አጽንኦት ሰጥታ ትከታተለዋለች'' ብለዋል።

በዲሞክራቲክ ኮንጎ እስካሁን ድረስ ብቻ 1400 ሰዎች በኢቦላ ቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን ይህም በበሽታው ከተያዙት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው መሞታቸውን ያሳያል።

ኢቦላ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንደ ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ ከኮንጎ ውጪ በበሽታው ምክንያት ሰው ሲሞት የኡጋንዳው ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው።

ኢቦላ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሲከሰት ይህ ሁለተኛው ትልቁ የኢቦላ ወረርሽኝ ነው ተብሏል።