በተበከለ ደም አራት ወንድሞቹ የሞቱበት እንግሊዛዊ

ጆን ኮርኔስ

ጆን ኮርኔስ የተባለው እንግሊዛዊ ከአምስት ወንድሞቹ ውስጥ አራቱ በተበከለ ደም እንዴት እንደሞቱ ሰሞኑን ለአጣሪው ኮሚቴ አስረድቷል።

ደም ያለመርጋት ችግሩን ለመታከም በሄደበት ወቅት በተነካካ ደም ምክንያት በጉበት በሽታ እንደተያዘ ይናገራል።

የ58 ዓመቱ ጆን ኮርኔስ ለአጣሪው ኮሚቴው እንደገለፀው ሶስቱ ወንድሞቹ ጥንቃቄ በጎደለው በተበከለ ደም ምክንያት በኤች አይ ቪ ቫይረስ ተጠቅተው በ1990ዎቹ ሞተዋል።

የኤድስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ

ሳይንቲስቱ መንትዮች ኤች አይ ቪ እንዳይዛቸው ዘረ መላቸውን አስተካከለ

የ26 አመቱ ጌሪ በ1992፣ ሮይ በ26 አመቱ በ1994ና ጎርደን በ40 አመቱ በ1995 ህይወታቸው በኤች አይ ቪ ያለፈ ሲሆን፤ ሌላኛው ወንድሙ በጉበት በሽታ ከሁለት አመት በፊት ሞቷል።

ቤተሰቡን ቤተሰብ እንዳይሆኑ የማይሽር የህሊና ጠባሳ ባደረሰው በዚህ የደም መበከል ቀውስ በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር ከ1970-1980 ባሉት አስር አመታት ውስጥ 4ሺህ 800 የደም መርጋት ችግር ያለባቸው ሰዎች በሄፐታይተስ እንዲጠቁ ተደርገዋል።

ከነዚህም ውስጥ ከ2ሺዎቹ በላይ ሞተዋል።

በእንግሊዝ ሃገር በጤናው ላይ ከተከሰቱት ቀውሶች አስከፊው ተብሏል።

Image copyright SPL

ጆን እንደሚናገረው ወንድሙ ሮይ ባለማወቅ አንዲት ሴት ላይ ኤችአይቪ እንዳስተላለፈባትና የሱ ህይወት ከማለፉ በፊት እንደሞተች ነው።

"የሀገሪቱ ሚዲያ ዜናውን ከሰሙ በኋላ ለአመታትም "ተውሳኮቹ" "ባለኤድሳሞቹ ቤተሰቦች" በሚል ቅጥያ ስም ሚዲያው ሲያሸማቅቃቸው እንደነበር የሚናገረው ጆን ወንድሙ ጌሪ በሞተበት ወቅት አምሳ ሪፖርተሮች ተደብቀው የቀብር ስርአቱን ፎቶ ሲያነሱ እንደነበር ያስታውሳል።

ዚምባብዌ ኤች አይ ቪ እፈዉሳለሁ ያለዉን ፓስተር ቀጣች

ኮንዶም መጠቀም እያቆምን ይሆን?

የጌሪ ባለቤትም ባለቤቷ ከሞተ ከአምስት አመት በኋላ በኤችአይቪ ሞተች።

ከዚህም ጋር ተያይዞ "ብዙ አባት ወይም እናት የሌላቸው የወንድምና የእህት ልጆች አሉኝ" ይላል።

"ቢያንስ ከ30 የማያንሱ ቤተሰቦቼ ቀጥታ ተጎድተዋል፤ እዚህ የመጣሁት የተጠቁትን ወክየ ሳይሆን ተፅእኖ የደረሰባቸውንም እንጂ" ብሏል።

ቤተሰቦቹ ላይ የደረሰውን ጉዳት በጎርጎሳውያኑ 1974 በርሚንግሃም ላይ የደረሰውን የቦምብ ፍንዳታ ተከትሎ በአየርላንድ ማህበረሰብ ላይ የደረሰውን ጭቆና ያስታውሰዋል።

" አየርላንዳዊ ከሆንክ መንገድ ላይ ከተገኘህ ትደበደባለህ፤ የሚሰቀጥጥ ጉዳይ ነበር" የሚለው ጆን " በቤተሰባችን ላይ የደረሰው ተመሳሳይ ነው፤ "ባለኤድሳሞቹ" ቤተሰቦች እንባል ነበር። የነሱ ስህተት እንዳልነበረው በኛም ላይ የተፈጠረው የኛ ስህተት አልነበረም፤ ተጠቂዎች ነን" ይላል።

በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር በ1970ዎቹ ለደም አለመርጋት ችግሩ ህክምና ሲከታተል የነበረው ጆን "ህፃን እያለን ደሙን ለማቆም ደም በመለገስ ነው"

መደረግ ስለሚገባው ጥንቃቄም ሆነ ስለ ህክምናው ችግሮች ተነግሮት እንደሆነ የተጠየቀው ጆን ምንም ነገር እንደማያውቅና " ስለ ቫይረሱም ምንም አይነት እውቀት አልነበረንም" ብሏል።

ተያያዥ ርዕሶች