የኬንያ ፓርላማ አባሉ ሴት ባልደረባቸውን በጥፊ በመምታታቸው ተያዙ

የኬንያ ፓርላማ Image copyright Reuters

አንድ የኬንያ ፓርላማ አባል ለተመረጠቡት አካባቢ ገንዘብ አልመደቡልኝም በሚል ባልደረባቸውን በጥፊ ተማተዋል ተብለው በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ራሺድ ቃሲም የተባሉት የፓርላማ አባል፣ የፓርላማው በጀት ኮሚቴ በቀጣይ ዓመት የሃገሪቱ በጀት ላይ እየተወያየ ባለበት ነው የኮሚቴው አባል የሆኑትን ፋጡማ ጌዲን በጥፊ የተማቱት።

የእንግሊዝ ፓርላማ አባላት የረሃብ ሚኒስቴር ይሾምልን እያሉ ነው

ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላ አፋቸው አካባቢ ደም እየታየ የሚያለቅሱት ፋጡማ ጌዲ ፎቶግራፍ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ሲሰራጭ ቆይቷል።

Image copyright Twitter

ይህንን ተከትሎም ወንድ የፓርላማው አባላት በተፈጸመው ጥቃት ዙሪያ በማሾፋቸው ሴት አባላት ድርጊቱን በመቃወም ምክር ቤቱን ጥለው ወጥተዋል።

ከኬንያ ሰሜን ምስራቅ ዋጂር ከሚባለው አካባቢ ተመርጠው የመጡት ቃሲም በፓርላማው የመኪና ማቆሚያ ስፍራ ላይ ከምክር ቤት አባሏ ፋጡማ ጌዲ ጋር ለተመረጡበት አካባቢ በጀት ለምን እንዲመደብ እንዳላደረጉ ከተጨቃጨቁ በኋላ በጥፊ እንደመቷቸው ተነግሯል።

ወንድ የፓርላማ አባላትም ከዚህ ክስተት በኋላ በሴት አቻዎቻቸው ላይ እንደተሳለቁባቸው ሳቢና ዋንጂሩ የተባሉ ሴት የፓርላማ አባል "አንዳንዶቹ ቀኑ የጥፊ እለት ነው" ማለታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ይህንንም ተከትሎ ሴት የፓርላማው አባላት ጥቃት ፈጻሚው ግለሰብ በፖሊስ እንዲያዝ በመጠየቅ ፓርላማውን ረግጠው የወጡ ሲሆን ግለሰቡም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።
የኡጋንዳ ፓርላማ አባላት እርስ በርስ ተደባደቡ