በሠርግ ዕለት ማታ የሚጠበቀው 'የደም ሻሽ (ሸማ)' ምንን ያመላክታል?

ዘመድ አዝማድ ደም የነካ አንሶላ ይዘው

በሕይወታችሁ ከምትደሰቱበት ቀን አንደኛው የሠርጋችሁ ዕለት ነው። ይሁን እንጂ የወንዶች የበላይነት ተንሰራፍቶ ባለባቸው ሃገራት ለሚኖሩ ሴቶች ምሽቱ አስፈሪ ቅዠት ይሆንባቸዋል። በጥንታዊው ልማድ ዕለቱ ሴቶች የሥነ ልቦናና አካላዊ ስቃይን የሚያስተናግዱበት ነው። አንዳንዴ ችግሩ የረጅም ጊዜ የጤና ቀውስ ሆኖም ይቀጥላል።

ኤልሚራ (ለዚህ ታሪክ ሲባል ስሟ የተለወጠ) "ልክ የሠርጋችን ምሽት ከፊት ለፊቴ ቆሞ ልብሱን ማወላለቅ ሲጀምር በጣም ፈርቼ ነበር" ትላለች ከሠርጓ በኋላ ስለተፈጠረው ስታስታውስ።

"ምንም እንኳን እንዳገባሁ ራሴን ለማሳመን ብሞክርም፤ ይህንኑ ለራሴ ደግሜ ደጋግሜ ብነግረውም ሊያረጋጋኝ ግን አልቻለም፤ ማሰብ የቻልኩት ልብሴ ማውለቅ እንደነበረብኝ ነው" ትላለች።

ተጭበርብራ የተሞሸረችው ሴት አፋቱኝ እያለች ነው

ቻይና ቅጥ ያጡ ሰርጎችን ልትቆጣጠር ነው

ኤልሚራ የዩኒቨርሲቲ ትምህርቷን ስታጠናቅቅ የ27 ዓመቷ የነበረ ሲሆን የራሷን ሥራ በመፍጠርም ትሰራ ነበረ። ባሏን የመረጡላት ቤተሰቦቿ ሲሆኑ እርሷም ጋብቻውን ለመፈፀም ተስማማች። ምክንያቷ ደግሞ እናቷን ማስደሰት ነበር።

"ጎረቤታችን ነበር፤ ነገር ግን ምንም የሚያመሳስለን ነገር አልነበረም፤ እሱ አልተማረም፤ በቃ አንድ የሚያደርገን ምንም ነገር የለም" ስትል ስለ ባሏ ትናገራለች።

ኤልሚራና ባሏ የተዋወቁት በወንድሟ አማካኝነት ነው፤ ጥሩ ባል ሊሆናት እንደሚችልም ተነግሯታል። እናቷም ጎረቤታቸውን በማግባቷ ደስታቸው ወደር አልነበረውም።

ይሁን እንጂ ኤልሚራ ቤተሰብ መመስረት እንደማትፈልግ ለእናቷ በተደጋጋሚ ነግራቸዋለች። በዚህን ጊዜ ይህች ልጅ 'ጎጆ መቀለስ አሻፈረን አለች' ሲሉ ለቅርብ ዘመዶቻቸው አልሚራን እንዲያግባቧት ስሞታ ተናገሩ። ጋብቻውን እምቢ ማለቷ ድንግል አይደለችም የሚል ጥርጣሬን ፈጠረባቸው።

እንደ እውነቱ ከሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ግብረ ሥጋ ግንኙነት ያደረገችው የሠርጓ ዕለት ነበር።

"ባሌ ይህንን እያወቀ ስሜቴንና ክብሬን ለመጠበቅ ቅንጣት ታህል አልተጨነቀም ነበር" በማለት ዕለቱን ታስታውሰዋለች።

" ብር አምባር ሰበረልዎ፣

ጀግናው ልጅዎ ! " ተብሎ እንደተዘፈነው እርሱም ጀግነቱን በወንድነቱ ለማስመስከር ተጣድፏል።

እርሷ እንደምትለው ተነስቶ ከላይዋ ላይ ተከመረባት፤ በሁኔታው እጅግ ተደናገጠች ። ከሚቀጥለው ክፍል የመንኳኳትና 'ቀስ በል! ምን ዓይነት ጭካኔ ነው' የሚል የሴት ድምፅ ሰማች።

ድብቅ የህጻናት ጋብቻዎች

ኬንያዊው በአንድ ሰርግ ሁለት ሚስቶች አገባ

ከበሩ በስተጀርባ የነበሩት እናቷ፣ ሁለት አክስቶቿና ሌሎች ዘመዶቿ ነበሩ። ሲጮሁና በሩን ሲያንኳኩ የነበሩትም እነርሱ ናቸው። በዚያ ሁኔታ ከበሩ ሥር የተኮለኮሉት ከባለቤቷ ጋር የምታደርገውን አካላዊ ግንኙነት ለመከታተልና የእርሷን ድንግል መሆን ለማረጋገጥ ነበር።

"እስኪ አምጡት ደሙን ሸማ - እንዳንታማ፣

እስኪ አምጡት የደሙን ሻሽ- እንዳንሸሽ..." በሚለው ዘፈን በኩራት ለመውረግረግ ጓጉተዋል።

"የሚያወሩት እያንዳንዱ ድምፅ ይሰማን ነበር" የምትለው ኤልሚራ ሰውነቷ ሲንቀጠቀጥና በግንኙነቱ ምክንያት የተፈጠረው ህመም ሲበረታባት ጋብቻ ማለት ይህ ነው? ስትል ራሷን እንድትጠይቅ አድርጓታል።

አብዛኞቹ ያገቡ የሴት ዘመዶች ሙሽሮቹ ካሉበት ቀጣይ ክፍል በመሆን አዲስ ያገባች ሴትን ተከትለው በመሄድ 'ኢንጊ" የተባለውን ሚና ይወጣሉ።

የእነዚህ ሴቶች አንደኛው ሚናቸው የግብረ ሥጋ ግንኙነት በማድረግ ልምድ የሌላትን ሙሽራ ማማከር ሲሆን ሌላኛው ደግሞ 'የደሙን ሻሽ' ወይም ለመጀመሪያ ጊዜ ግንኙነት የፈፀሙበትን አንሶላ ማንሳት ነው።

"የሠርጌ ምሽት በጭንቀት የተሞላ ድራማ ነበር"

በካውካሰስ ባህል ከሠርጉ ማግስት ጠዋት አንሶላ ይዞ ወጥቶ ማሳየት የተለመደ ነው። ለዘመድ አዝማዱ ደሙን ማሳየት ድንግል የመሆኗ እና የክብር ማሳያ ነው። ከዚያም በአንሶላው ላይ ደሙን ያዩ ቤተሰቦች አዲሶቹን ሙሽሮች እንኳን ደስ አላችሁ ይሏቸዋል፤ ደስታቸውንም ይገልፃሉ።

"ለዚህ ነው የሠርግ ምሽት በእስጨናቂ ድራማ የሚሞላው፤ በሠርጉ ማግስት አንሶላው ምንን ነው የሚያመለክተው?" ሲሉ በአዘርባጃን የሴቶች መብት አጥኚ የሆኑት ሻክህላ ኢስማኢል ይጠይቃሉ።

አንሶላው ላይ ደም መታየት ካልቻለ ሴቷ ትገለላለች ወደ ቤተሰቦቿም በሃፍረት ተሸማቃ እንዲትመለስ ይደረጋል።

ከዚያም ከባሏ እንደተፋታች ስለምትቆጠር በድጋሚ ለማግባት ትቸገራለች። ከቤተሰቦቿ ቁጣና ስድብን ለማስተናገድም ትገደዳለች።

በአዘርባጃን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንደሚሉት ይህ ልማድ አሁንም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎችም እንደተስፋፋ ነው። አንዳንዴ እንደውም ከጋብቻው በፊት ሴቷ ድንግል መሆን አለመሆኗ በሃኪም እንዲረጋገጥ ይደረጋል።

ይህ ድርጊት በተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የተወገዘ ነው፤ ይህ በትንሹ በ20 አገራት ተግባራዊ የሚደረገው ልማድ እንዲያከትም የተባበሩት መንግሥታትና የዓለም ጤና ድርጅት ጥሪ አቅርበው ነበር። ድርጊቱ የሴቶችን መብት የሚጥስና ለሥነ ልቦና ችግር የሚዳርግ ነው ሲሉም አውግዘውታል።

በመግለጫቸው ላይም የህክምና ሳይንስ ድንግልና የሚባል ፅንሰ ሃሳብ እንደሌለና ይህ ሃሳብ ባህላዊ፣ ኃይማኖታዊና እና ማህበራዊ አስተሳሰብ እንደሆኑነ ጠቅሰዋል።

'ቀይ አፕል'

በጎረቤት አገር አርሜኒያ፣ ጆርጂያ እና በሰሜናዊ ካውካሰስ እንዲሁም በሩሲያ ሪፐብሊክ ተመሳሳይ ልማድ አለ።

በአሜሪካ ከበር ባሻገር የሚቀመጡ የዐይን እማኞች አይኖሩም። ልማዱ ቀይ አፕል (red apple) ይባላል። ስያሜው በአንሶላ ላይ የሚፈስን የደም ጠብታ ለማመላከት የተሰጠ ነው።

ከዋና ከተማዋ የሬቫን ውጭም ድርጊቱ በተመሳሳይ መልኩ ይፈፀማል።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ ኒና ካራፔሺያን እንደሚሉት አንዳንድ ጊዜ የሙሽራዋ ዘመዶች እና ጎረቤቶች ልጃቸው ንፁህና ያልተነካካች መሆኗን እንዲያረጋግጡ ይጋበዛሉ።

በመሆኑም በመንደሩ ያሉ ሰዎች በሙሉ በልማዱ ምክንያት የተገኘውን ደስታ ይጋራሉ።

በገጠር አካባቢዎች ሴቶች ዕድሜያቸው 18 ሲሞላ ወዲያውኑ ይዳራሉ። አብዛኞቹ ምንም ዐይነት ሥራም ሆነ ሌላ ክህሎት የላቸውም። በመሆኑም እነዚህ ሴቶች የቀይ አፕሉን ምርመራ ካላለፉ ምን አልባት ቤተሰቦቻቸው ሊክዷቸውም ይችላሉ ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ አክለዋል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ