ለመሆኑ ኢንተርኔቱን ማን አጠፋው?

የተቆለፈ ኢንተርኔት Image copyright ullstein bild

ይህ ለቢቢሲ ጋዜጠኞች የሚሊዮን ብር ጥያቄ ሆኖ ነበር የሰነበተው። በቀን ሚሊዮን ዶላሮችን እያጣ የነበረው ቴሌም ቢሆን ለዚህ ጥያቄ ድፍንም ሆነ ዝርዝር ምላሽ የለውም።

የዋናው ሥራ አስፈጻሚ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሪት ጨረር አክሊሉ ከትናንት በስቲያ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ሊሉ የቻሉት

በንቅለ ተከላ ዕይታው የተመለሰለት ኢትዮጵያዊ ታዳጊ

ኢትዮቴሌኮም ኢንተርኔት ለምን እንደተቋረጠ መግለፅ እንደማይችል አስታወቀ

"ለተወሰኑ ሰዓታት ተቋርጦ ነበር። ኢትዮ ቴሌኮም አሁን በዚህ በዚህ ምክንያት ነው የተቋረጠው ብሎ መግለጽ አይችልም። ምናልባት ሌላ አካል ሊገልጸው ይችላል። እኛ ግን ይህ ነው ብለን የምንገልጸው አይደለም። "

ለመሆኑ ኢንተርኔቱን ማን አጠፋው?

ኢንተርኔት በመጥፋቱ የደረሰውን ሁሉን አቀፍ ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳት የሚያሰላ ምናባዊ ካልኩሌተር የለም እንጂ፤ ቢኖር ኖሮ...ለነገሩ እሱም ኢንተርኔት መፈለጉ አይቀር ይሆናል...

ብቻ ያም ሆነ ይህ ቴሌ በቀን ስንት እንደከሰረ ተደርሶበታል። 'ኔትብሎክስ' የተሰኘ የኢንተርኔት ጥናት ቡድን ለቢቢሲ በሰጠው ቃል ቴሌ በቀን ሊያውም በትንሹ 4.5 ሚሊየን ዶላር አይኑ እያየ ያመልጠዋል ብሏል።

"በኢትዮጵያ የአንድ ቀን የኢንተርኔት መዘጋት ቢያንስ 4.5 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ያሳጣል"።

አምስት ጂ ኢንተርኔት ምን አዲስ ነገር አለው?

ይህ ወደ አገር ቤትኛ (ብር) ሲመነዘር እንደ ድሀ አገር በሦስት ቀናት ቢያንስ 360 ሚሊዮን ብር የሚደርስ አጥተናል። ይህ ገንዘብ ሁለት የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በገጠሪቱ ኢትዮጵያ አንፈላሶ አያስገነባም?

የቁልፍ ምልክት ከኮዶች ፊት
Getty
ኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት በመዝጋቷ

 • በየ1 ሰዓቱ 5,296,006 ብርታጣለች።

  Source: Netblocks

  ለመሆኑ ኢንተርኔቱን ማን አጠፋው?

  ምናልባት ብዙዎች መላምት እንደመቱት 1.2 ሚሊዮን ተማሪዎች ለብሔራዊ ፈተና መቀመጣቸው ይሆን?

  የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚያብሔር ኢንተርኔቱን አጥፉልን ብለው ተማጽነው ይሆን? ሰሞኑን ደውለንላቸው ይህን ነበር ያሉን፤

  "ከቴሌ ጋር አቋርጡልን ብለን? እንደዚህ ሰርተን አናውቅም። እኛ ምን አቅም አለን?" በፈገግታ ታጅበው መልሳቸውን ሰጥተውናል።

  ታዲያ ኢንተርኔቱን ማን አጠፋው? ምናልባት እንደሚወራው ትምህርት ሚኒስቴር ቢሆንስ? ወደዚያው ደወልን። ወይዘሮ ሀረጓ ማሞ የከፍተኛ ትምህርትና ሳይንስ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ባልደረባ ናቸው። የሚያውቁት ነገር ይኖር ይሆን?

  "ምንም መረጃ የለኝም። መቆራረጡ ከፈተና ጋር የተያያዘ ነው ብዬም አላምንም"።

  ለጊዜው ኢንተርኔቱ ጠፋብኝ እንጂ አጠፋሁት የሚል መሥሪያ ቤት አልተገኘም።

  ለመሆኑ ኢንተርኔቱን ማን ነው ያጠፋው?

  በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ