ህንድ አሜሪካን ይጎዳል የተባለ የንግድ ታሪፍ ልታስተዋውቅ ነው

የህንድ ኖት Image copyright Reuters

ህንድ ከእሁድ ጀምሮ የለውዝና የአፕል ምርቶችን ጨምሮ 28 የአሜሪካ ምርቶች ላይ አዲስ ታሪፍ ልታስተዋውቅ መሆኑን ገልፃለች።

አዲሱ ታሪፍ ህንድ የብረትና አሉሚኒየም ምርቶችን ወደ አሜሪካ በምትልክበት ወቅት ለጫነችባት ከፍተኛ ግብር ምላሽ ነው ተብሏል።

አሜሪካ ግብሩን ዝቅ አድርጊ ብትባል በእምቢተኝነቷ ቀጥላለች።

በዚህ ወር ፕሬዚዳንት ትራምፕ አሜሪካ ለህንድ በንግዱ ዘርፍ የምታደርግላትን የተለየ ጥቅማጥቅም እንደምታቆም ገልፀው ነበር።

ኢሳያስን ለመጣል'#ይበቃል' የተሰኘው የኤርትራውያን እንቅስቃሴ

ኢኮኖሚያዊ ተቃውሞና ያስከተለው ውጤት

በምላሹም ህንድ እስከ 120% የሚደርስ ታሪፍ በአሜሪካ ምርቶች እንደሚጫን በባለፈው አመት ህንድ አስታውቃ የነበረ ቢሆንም በውይይቶች ምክንያት አተገባበሩ ዘግይቶ ነበር።

በባለፈው አርብ ግን የህንድ የገንዘብ ሚኒስትር ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ሲባል ውሳኔው ተግባራዊ እንደሚሆን አሳውቀዋል።

በአሜሪካና በህንድ ያለው የሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነት በባለፈው አመት 142 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን ይህም ከአስራ ሰባት አመት በፊት ከነበረው ቁጥር ጋር ሲወዳደር ሰባት እጥፍ ነው ተብሏል።

ነገር ግን 5.6 ቢሊዮን ዶላር የሚሆነው የህንድ ወጪ ንግድ አሜሪካ ከቀረጥ ነፃ አድርጋላት የነበረ ሲሆን አሜሪካ ይህንን የንግድ ግንኙነት ማቆሟ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ተፅእኖ ሊያደርስ እንደሚችል ተንታኞች ይናገራሉ።

የትራምፕ እና የለንደኑ ከንቲባ ሳዲቅ ካህን እሰጣገባ

የትራምፕ አስተዳደር "ኢፍትሐዊ" የንግድ ስርአትን ለማስተካከል በሚል እንቅስቃሴያቸው ነው እንዲህ አይነት የንግድ መጠቃቀም ግንኙነት እንዲቀሩ ያደረጉት።

ይህንንም ተከትሎ በሁለቱ ኃገራት ያለው የንግድ ግንኙነት የሻከረ ሲሆን በባለፈው አመትም ህንድ ለዚህ ምላሽ የሚሆን የታሪፍ ጫናን አስተዋውቃለች።

ትራምፕ በበኩላቸው ህንድ ከኢራን ነዳጅ እንዲሁም ከሩሲያ ኤስ 400 ሚሳይል ለመግዛት የያዘችውን እቅድ የማታቆም ከሆነ ማእቀብ ይጣልባታል ሲሉ አስፈራርተዋል።

የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ልጆቻቸው 'ሞባይል' እንዳይጠቀሙ የሚያግዱት ለምን ይሆን?

የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራሃማንያም ጃይሻንካርና አቻቸው ማይክ ፖምፔዮ ጃፓን በሚካሄደው የጂ-20 ጉባኤ ላይ የሚወያየዩ ሲሆን፤ ፕሬዚዳንት ትራምፕና ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በቅርቡ ተገናኝተው እንደሚወያዩ ይጠበቃል።