"ለአውሮፕላኑ መከስከስ ፓይለቶች ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም" አቶ ተወልደ ገብረማርያም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወልደ ገብረማርያም

ባለፈው መጋቢት ወር መጀመሪያ ላይ ነበር 157 ሰዎችን ያሳፈረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 መብረረር በጀመረ 6 ደቂቃ ጊዜ ውስጥ የተከሰከሰው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወልደ ገብረማርያም ለዚህ አደጋ በምንም ዓይነት ፓይለቶች ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም ይላሉ።

ለአደጋው መከሰት ፓይለቶችን የሚወቅሱ እጅጉን የተሳሳቱና መረጃው የሌላቸው ናቸው ይላሉ ዋና ሥራ አስፈፃሚው።

አንድ የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ለተፈጠሩት አደጋዎች ፓይለቶች ናቸው ተጠያቂ ሊሆኑ የሚችሉት ማለታቸውን ተከትሎ ነው ዋና ሥራ አስፈፃሚው ምላሽ የሰጡት።

"የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ

ኢቲ 302 የተከሰከሰበት ምክንያት ቅድመ-ሪፖርት ዛሬ ይወጣል

የቦይንግ ምርት የሆነው 737 ማክስ የተሰኘው አውሮፕላን በአምስት ወር ጊዜ ሁለት ጊዜ ነው የተከሰከሰው፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢንዶኔዥያው ላየን ኤይር።

የሁለቱም አደጋዎች የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ከበረራ ቁጥጥር 'ሲስተም' ጋር የተያያዘ እክል ለአደጋው ምክንያት እንደሆነ ያስረዳል።

የኮንግረስ አባል የሆኑት ሳም ግሬቭስ ግን 'የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቶች ላይ የሠፈረው የአደጋ ምክንያት የፓይለቶች ስህተት ነው፤ ሲሉ ተደምጠዋል።

"አደጋውን ስሰማ በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ" የረዳት አብራሪው ጓደኛ

አክለውም 'አሜሪካ ውስጥ የሠለጠኑ ፓይለቶች ነበሩ እኒህን አውሮፕላኖች በደንቡ ሊቆጣጠሩ የሚችሉት' የሚል ሃሳብ ሰንዝረዋል።

አቶ ተወልደ፤ ሳም ግሬቭስ 'ትክክለኛው መረጃ እጃቸው ላይ የለም፤ ሪፖርቱ ደግሞ የሚጠቁመው ፓይለቶቹ የሚፈለገውን ሁሉ እርምጃ እንደወሰዱ ነው' ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

'ኤምካስ በመባል የሚታወቀው 'ሲስተም' በከባድ ጊዜ እንኳ አውሮፕላኑ ለፓይለቱ እንዲታዘዝ ተደርጎ የተገጠመ ነው። ነገር ግን በሁለቱም አደጋዎች ወቅት ይህ ሲስተም አውሮፕላኖቹ አፍንጫቸውን ወደፊት እንዲደፉ አስገድዷል፤ ፓይለቶቹ አውሮፕላኑን ሊያዙት ቢሞክሩም ሊታዘዝ አልቻለም' ሲል የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ ይጠቁማል።

ከኢንዶኔዥያው አደጋ በኋላ ቦይንግ ኤምካስ ስለተሰኘው ሲስተም ለአየር መንገዶች ማብራሪያ ልኳል። የኮንግረስ አባሉ ግን የኢቲ302 አብራሪዎች ይህንን ማብራሪያ በደንቡ አልተከታተሉትም ሲሉ ይወቅሳሉ።

የቦይንግ ኃላፊ የሟቾችን ቤተሰቦች በይፋ ይቅርታ ጠየቁ

ግሬቭስ ወቀሳውን ሲያቀርቡ በሥፍራው የነበሩት የአሜሪካ ፌዴራል አቪየሽን ጊዜያዊ አለቃ በኮንግረስ አባሉ ሃሳብ የተስማሙ ሲሆን የአብራሪዎቹን ድርጊት 'ዕድለ-ቢስ' ብለውታል።

አቶ ተወልደ ወቀሳውን ሊቀበል የሚገባው ማን እንደሆነ በጣም ግልፅ እኮ ነው ይላሉ፤ «አውሮፕላኑ ችግር እንዳለበት እኮ ዓለም ያወቀው ነው። ለዚያ መስሎኝ አውሮፕላኖቹ ከሥራ ውጭ ሆነው ማስተካከያ እየተደረገባቸው ያለው።»

አብራሪዎችን የሚወቅሱ ሰዎች አንድ ጥያቄ ራሣቸውን እንዲጠይቁ እፈልጋለሁ። 'ችግሩ የአብራሪዎች ከሆነ በዓለም ዙሪያ ያሉ 380 ቦይንግ አውሮፕላኖችን ከሥራ ውጭ ማድረግ ለምን አስፈለገ?»

ምናልባት አሜሪካ ወቀሳውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዲወስደው ፈልጋ ይሆን ወይ የሚል ጥያቄ ከቢቢሲ የተሰነዘረላቸው አቶ ተወልደ አይደለም የሚል ድምፅ ያለው ምላሽ ሰጥተዋል።

የቦይንግ አለቃ ዴኒስ ሚዩልበርግ 'ቦይንግ ለአየር መንገዶች ጋር በሥርዓት የመረጃ ልውውጥ አላደረገም፤ ቦይንግ ስህተት ሰርቷል' ሲሉ አምነዋል።

ጨምረውም ቦይንግ 737 ማክስ በያዝነው ዓመት ወደሥራ ይመለሳል ብለው እንደሚያስቡ ተናግረዋል።

ኬንያውያን የኢትዮጵያ አየር መንገድንና ቦይንግን ሊከሱ ነው

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ