አምነስቲ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ለውጥ እንዲደረግበት ጠየቀ

አምነስቲ ኢንተርናሽናል Image copyright Amnesty International

ሃገሪቱ ከነበረችበት የጭቆና ታሪክ ተላቃ የሰብአዊ መብት ጥሰት የተፈጸመባቸው ሰዎች ፍትህ እንዲያገኙ ለማስቻል እንዲያግዝ በሚያስችል ሁኔታ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ለውጥ እንዲደረግበት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት የሆነው አምነስቲ በ2008 እና 2009 መንግሥታዊው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ያወጣቸውን ሁለት የምርመራ ሪፖርቶችን ከገመገመ በኋላ ነው መግለጫውን ያወጣው።

አምነስቲ እንዳለው ኮሚሽኑ የምርመራ ሥራውን ያከናውን የነበረው ከሚታወቀው የሰብአዊ መብቶች ማዕቀፎችና መመዘኛዎች ውጪ በመሆኑ የተከተላቸው ዘዴዎችና ውጤቶቹ ላይ ጥርጣሬን ከመፍጠሩ ባሻገር ለጥሰቶች ተጋልጠው የነበሩ ሰለባዎች ተገቢውን ፍትሕ እንዳያገኙ አድርጓል ብሏል።

የአክሱም ሙስሊሞች ጥያቄ መቼ ምላሽ ያገኝ ይሆን?

ሴት እግር ኳሰኞች እና ቡድኖች ስንት ይከፈላቸው ይሆን?

"ግምገማችን እንደሚያመለክተው ኮሚሽኑ በአሁኑ ወቅት ሃገሪቱ ከነበረችበት የመብቶች ጭቆና ለመላቀቅ ለምታደርገው ጥረት ብቁ ባለመሆኑ ከዓለም አቀፉ ደረጃና መልካም ተሞክሮዎች አንጻር ለውጥ ሊደረግበት የአዲሱን አስተዳደር ጥረቶችን በሚያግዝ መልኩ ለውጥ ሊደረግበት ይገባል" ሲሉ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪካ ቀንድና የምሥራቅ አፍሪካ እንዲሁም የግሬት ሌክስ ዳይሬክተር ጆአን ኒያኑኪ ተንግረዋል።

አምነስቲ እንዳለው በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ለሕዝብ ይፋ የተደረጉ ሰባት ያህል ሪፖርቶችን የተመለከተ ሲሆን ምርመራዎቹ የተጠቀሙት ዘዴዎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ለመመርመር ከሚያስፈልገው አንጻር ጉልህ ክፍተት እንዳለባቸው አመልክቷል።

በተለይ ደግሞ ከሁለት ዓመታት በፊት በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ያጋጠሙ ተቃውሞዎችን ተከትሎ ተፈጸሙ የተባሉ ሰቆቃዎችንና የከፉ አያያዞችን በተመለከተ ለተወካዮች ምክር ቤት ኮሚሽኑ ያቀረባቸውን ሁለት ሪፖርቶች ገምግሟል።

በዚህም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በጸጥታ ኃይሎች ተፈጽመዋል የተባሉ የመብት ጥሰቶችን በጥልቀት በመመርመር ከማጋለጥ ይልቅ፤ በጥድፊያ የተቃዋሚ ፓርቲዎችንና የሰብአዊ መብት ጥሰት ሰለባዎችን ጥፋተኛ አድርጓል።

ኢትዮቴሌኮም ኢንተርኔት ለምን እንደተቋረጠ መግለፅ እንደማይችል አስታወቀ

ታንዛኒያ በዊግና ሰው ሰራሽ ጸጉር ላይ ከፍተኛ ቀረጥ ጣለች

"ሰለባዎቹን የሚጎዳ ያፈጠጠ ወገንተኝነትና ያቀረቡትን ቅሬታም የማጣጣል አቋም ኮሚሽኑ በተቃዋሚዎች ግድያና የእስር ሁኔታ ለሰለባዎቹና ለሁሉም ዜጋ ነገሮችን ከማስተካከል አንጻር የነበረውም መልካም አጋጣሚን አባክኗል" ሲሉ ጆአን ኒያኑኪ ተናግረዋል።

አምነስቲ በመግለጫው ላይ የሰብአዊ መብቶች መከበርን ለማገዝ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን መሰረታዊ ማስተካከያዎች እንዲደረጉበት ሃሳብ ያቀረበ ሲሆን፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም የኮሚሽኑን ግልጽነት፣ ሁሉን አካታችነትና ወገንተኛ ያልሆኑ አመራሮችን ለመመደብ በሚያስችል ሁኔታ ኮሚሽኑን ለመመስረት የወጣውን አዋጅም ማስተካካያ እንዲያደርግ ጠይቋል።