መፈንቅለ መንግሥቱና የግድያ ሙከራዎች

አዲሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንን Image copyright FBC

መፈንቅለ መንግሥት በአማራ ክልል መስተዳደር ላይ ባህር ዳር ከተማ ውስጥ ተሞክሮ እንደ እንደከሸፈ ከተነገረ ከሰዓታት በኋላ በሃገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ላይ የግድያ ሙከራ መፈጸሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አረጋገጡ።

ባህር ዳር ውስጥ ስለተሞከረው መፈንቅለ መንግሥት ዝርዝር መረጃ እየተጠበቀ በነበረበት ጊዜ ዕኩለ ሌሊት ገደማ በወታደራዊ የደንብ ልብስ ብሔራዊው ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው መግለጫ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሠራዊቱ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንን ላይ የመግደል ሙከራ መፈጸሙን ገልጸዋል።

ጓድ መንግሥቱ እንባ የተናነቃቸው 'ለት

የከሸፈው መፈንቅለ መንግሥት ሥዕላዊ መግለጫ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ላይ እንደገለጹት ባህር ዳር ከተማ ውስጥ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ የተደረገው የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ስብሰባ በማካሔድ ላይ በነበሩበት ጊዜ ነው።

በመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው ወቅት ጥቃት ከተፈጸመባቸው መካከል "ከፊሉ መሞታቸውንና ከፊሉ መቁሰላቸውን" ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩ ሲሆን ጉዳቱ የደረሰባቸው እነማን እነደሆኑ የሰጡት ምንም አይነት ማብራሪያ።

ጨምረውም ከአመሻሽ በፊት በባህር ዳር ከተማ ተሞክሮ በከሸፈው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ጉዳት መድረሱን አመልክተው፤ አዲስ አበባ ውስጥ በኤታማዦር ሹሙ ላይ የተፈጸመው የመግደል ሙከራ ከመፈንቅለ መንግሥቱ ሙከራ ጋር ግንኙት እንዳለው አመልክተዋል።

ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን መገደላቸው ተነገረ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ኤታማዦር ሹሙ ከመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው ጋር በአማራ ክልል የተከሰተውን ችግር ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት እየመሩ እንደነበርጠቁመው ጥቃቱም ምሽት ላይ "ቅጥረኞች" ባሏቸው ሰዎች እንደተፈጸመባቸው ገልጸዋለ።

በኤታማዦር ሹሙ ላይ የመግደል ሙከራውን የፈጸሙት ግለሰቦች መያዛቸውንና በቀጣይነትም በድርጊቱ ውስጥ እጃቸው አለበት የሚባሉትን በቁጥጥር ሥር ለማዋል እየተሰራ መሆኑን ተናግረው፤ ለመከላከያ ሠራዊትና ለፌደራል ፖሊስ አባላት ባቀረቡት ጥሪ ሃገራቸውንና ባንዲራቸውን አስቀድመው በአንድነት በሃገር ላይ የሚሰነዘርን ጥቃት በመመከት ጀግንነታቸውን ዳግም እንዲያረጋግጡ ጥሪ አቅርበዋል።

አዲስ አበባ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ተጎድተዋል ከተባሉት የመከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም በተጨማሪ አንድ የቀድሞ ጀነራልም ጥቃት እንደተፈጸመባቸው እየተነገረ ነው።

ተያያዥ ርዕሶች