ኢትዮጵያ የተገደሉ ባለስልጣናትና ጄኔራሎችን ለመዘከር የሃዘን ቀን አወጀች

የተወካዮች ምክር ቤት Image copyright Anadolu Agency

ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በአማራ ክልል ተሞከረ በተባለው መፈንቅለ መንግሥትና ግድያ ህይወታቸውን ላጡት የክልሉ ባለስልጣናትና የመከላከያ ሠራዊት ጄኔራሎችን ለመዘከር በመላው አገሪቱ ዛሬ ሰኔ 17 የሃዘን ቀን ሆኖ እንዲውል የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትናንትናው እለት አውጇል።

የአማራ ክልል መንግሥትም ለተገደሉት ሁለት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ሁለቱ ጄኔራሎች ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚቆይ የሃዘን ጊዜ ማወጁ ተሰምቷል።

በአማራ ክልል የተሞከረውን መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንንና አማካሪያቸው አቶ እዘዝ ዋሴ እንዲሁም የሃገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንንና ጡረታ ላይ የነበሩት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንን ጄኔራል ገዛኢ አበራ መገደላቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን መገደላቸው ተነገረ

ስለመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውና ስለግድያው እስካሁን የምናውቀው

በሃየሎም ይምሉ የነበሩት ጄነራል ሰዓረ መኮንን ማን ናቸው?

በመፈንቅለ መንግሥቱ ሙከራ የተገደሉ ባለስልጣናትና ጄኔራሎችን ሥርዓተ ቀብር የሚያስፈፅም ኮሚቴ መዋቀሩን ትላንትና የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል።

ተያያዥ ርዕሶች