በቅዳሜው ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው አቶ ምግባሩ ከበደ አረፉ

አቶ ምግባሩ ከበደ

ቅዳሜ ዕለት በአማራ ክልል በተፈፀመው ጥቃት የመቁሰል ጉዳት ከደረሰባቸው ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል አንዱ የሆኑት የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ምግባሩ ከበደ በዛሬው ዕለት ህይወታቸው አልፏል።

አቶ ምግባሩ ሰኔ 15/2011 ዓ.ም አማራ ክልል ዋና ከተማ ባህር ዳር ውስጥ ተሞከረ በተባለው "መፈንቅለ መንግሥት" ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና ሲደረግላቸው ቆይተው ዛሬ ህይወታቸው ማለፉን የአማራ ቴሌቪዥን በሰበር ዜናው ገልጿል።

ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን መገደላቸው ተነገረ

ስለመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውና ስለግድያው እስካሁን የምናውቀው

የሥራ ኃላፊነታቸውን "ከባድና የሚያስጨንቅ... ነው" ያሉት ዶ/ር አምባቸው ማን ነበሩ?

በአማራ ክልል ተሞከረ የተባለውን "መፈንቅለ መንግሥት" ተከትሎ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንንና አማካሪያቸው አቶ እዘዝ ዋሴ እንዲሁም የሃገሪቱ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንንና ከፍተኛ ወታደራዊ መኮነን ጄኔራል ገዛኢ አበራ ተገድለዋል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ