በሱዳን የተቋረጠው ኢንተርኔት ለአንድ ጠበቃ ብቻ መሥራት ጀመረ

አብደል አድሄም ሀሰን Image copyright Abdel-Adheem Hassan

በሱዳን ጠበቃ የሆነው አቤል አድሀም ሀሰን በሀገሪቱ ለሶስት ሳምንታት ኢንተርኔት ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም ለእርሱ ብቻ መስራት እንደጀመረ ለቢቢሲ ተናገረ።

የቴሌኮም አቅራቢውን ዛይን በመከላከያ ኃይሉ ታዝዞ ኢንተርኔት ካቋረጠ በኋላ ጠበቃው ፍርድ ቤት ፋይል ከፍቶ በመክሰስ ረትቶታል።

ነገር ግን በፍርድ ቤት ጉዳዩን ማሸነፍ ቢችልም ውሳኔው ተጠቃሚ ያደረገው እርሱን ብቻ ነው፤ ምክንያቱ ደግሞ ክሱን ሲመሰርት ራሱን ብቻ ወክሎ ስለሆነ የተከራከረው ኢንተርኔት ሊለቀቅ የቻለውም ለእርሱ ብቻ ነው።

በሱዳን ኢንተርኔት የተቋረጠው መከላከያ ኃይሉ በካርቱም ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ የነበሩ ሰልፈኞችን በኃይል ከበተነ በኋላ ነው።

ራሱን አጥፍቷል የተባለው የጄነራል ሰዓረ ጠባቂ ሆስፒታል እንደሚገኝ ተገለፀ

በሃየሎም ይምሉ የነበሩት ጄነራል ሰዓረ መኮንን ማን ናቸው?

የሰኔ 16ቱ ጥቃትና ብዙም ያልተነገረላቸው ክስተቶች

ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ የወታደራዊ ኃይሉ አገዛዝ አብቅቶ የሲቪል አስተዳደር ስልጣኑን እንዲረከብ ይፈልጋሉ።

የሕግ ባለሙያው ሀሰን እንደሚሉት በአሁኑ ሰአት ከሱዳን ነዋሪዎች እርሳቸው ብቻ ናቸው ኢንተርኔት መጠቀም የሚችሉት።

ነገርግን ዛሬ ወደ ፍርድ ቤት ዳግመኛ በማምራት በርካታ ሱዳናውያንን በመወከል ፋይል እንደሚከፍቱና የቴሌኮም አቅራቢውን ለመሞገት አቅደዋል።

"ሰሞኑን በሚኖረን የፍርድ ቤት ክርክር መርታት ከቻልን አንድ ሚሊየን ሰዎች ኢንተርኔት እንዲለቀቅላቸው እናደርጋለን " ብለዋል የሕግ ባለሙያው።

በሱዳን አሁንም ኢንተርኔት እንደተቋረጠ መሆኑን ቢቢሲ ማረጋገጥ ችሏል።

ጠበቃው እንደሚሉት "የቴሌኮም አቅራቢው ኢንተርኔት እንዲያቋርጥ የታዘዘበትን የጽሁፍ ማስረጃ ማቅረብ አልቻለም"

"ማንም ሰው ተጠያቂ መሆን አልፈለገም፤ ሁሉም ኃላፊነት ይሸሻል። ይህ የአለም ዓቀፉ የሰብአዊ መብት ጥሰትና ወንጀል ነው"

ሰኞ ዕለት የተባበሩት መንግሥታት የሱዳን ባለስልጣናትን የሰብአዊ መብት ቡድኖች ወደ ሀገሪቱ ገብተው በተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ የደረሰውን "አፈና" እንዲያጣሩ ጠይቆ ነበር።

የተባበሩት መንግሥታት ኃላፊ የሆኑት ማይክል ባቼሌት በጄኔቫ ባደረጉት ንግግር ላይ የሱዳን ወታደራዊ ኃይል የኢንተርኔት ማቋረጡን እንዲያቆም ጠይቀው ነበር።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ