የቀድሞው የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ላሚን ዲያክ ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

የቀድሞው የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አለቃ ላሚን ዲያክ Image copyright Getty Images

የቀድሞው የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማሕበር [አይኤኤኤፍ] ፕሬዝደንት የነበሩት ላሚን ዲያክ ዛሬ ፈረንሳይ የሚገኝ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የ86 ዓመቱ ዲያክ የ ፌዴሬሽኑ አለቃ በነበሩበት ወቅት ፈፅመዋቸዋል በተባሉት የሙስና እና የሕገ-ወጥ ገንዘብ ዝውውር ክስ ነው ፍርድ አደባባይ የሚውሉት።

ሴኔጋላዊው ዲያክ ክሱ ከተመሠረተባቸው ጊዜ ጀምሮ ለአራት ዓመታት ያክል በቁም እሥር ላይ ይገኛሉ።

የካፍ ፕሬዝደንት በፈረንሳይ ፖሊስ ለምን ታገቱ?

የዲያክ ታላቅ ልጅ የሆነው ፓፓ ማሳታ ዲያክም በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ ይፈለጋል፤ ቢሆንም ሴኔጋል በመግባቱ ምክንያት ሊገኝ አልቻለም።

አባት እና ልጅ ምንም የፈፀምነው ስህተት የለም ሲሉ ክሱን ውድቅ አድርገውታል።

በወጣትነት ዘመናቸው በዝላይ ውድድር ሃገራቸውን ያስጠሩት ዲያክ የዓለም አትሌኢተክስ ፌዴሬሽኖች ማሕበርን ለ16 ዓመታት ያክል መርተዋል።

ዲያክ ከተጠረጠሩባቸው ወንጀሎች አንዱ የሩስያ አትሌቶች አበረታች መድሃኒት መውሰዳቸውን ለመደበቅ ረብጣ ሽልንግ ተቀብለዋል የሚል ነው።

የአውሮፓን እግር ኳስ የሚዘውረው ሃብታሙ 'ደላላ'

ዲያክ የምርጫ ድምፅን በገንዘብ ገዝተዋል ተብለውም በፈረንሳይ መርማሪዎች ይጠረጠራሉ።

አንድ ሰሞን የሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር ከንቲባ የነበሩት ዲያክ የማሕበሩ ዋና ፅ/ቤት 'ሚገኝበት ሞናኮ ድልቅቅ ያለ ሕይወት ይገፉ እንደነበር ተነግሯል።

ዲያክን ጨምሮ ሌሎች አራት ግለሰቦች ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ከበድ ያለ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው እየተነገረ ነው።

ሴኔጋል የዲያክ ልጅ ፓፓ ማሳታ ዲያክን አሳልፋ እንድትሰጥ በተደጋጋሚ ብትጠየቅም አሻፈረኝ እንዳለች ነው።

የአፍሪካ እግር ኳስ ቅሌት

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ