"ብ/ጄነራል አሳምነው በባጃጅ ለማምለጥ ሲሞክሩ ነው የተገደሉት''

Asamminewu Tsiggee

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ የሰጠው የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ሰሞኑን በአማራ ክልል የተፈጸመው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ሃገሪቱ የተያያዘችውን ሽግግር አያደናቅፍም ብሏል።

በአዲስ አበባ እና በባህር ዳር የተፈጸሙ ግድያዎችን የማጣራት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑም ያስታወሱት የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም፤ በአሁኑ ወቅት የፌደራል እና የአማራ ክልል በቅርበት አብረው እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

“የኢህአፓና መኢሶን ነገር አማራ ክልል ላይ ሊከሰት ይችላል ብዬ ነበር”

"ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብተናል. . . ግን እናሸንፋለን"

"በዚህ መንገድ መገደላቸው ከፍተኛ የፀጥታ ችግር መኖሩን ያሳያል" ጄነራል ፃድቃን

በአማራ ክልል የተሞከረው መፈንቅለ መንግሥት አራት ቁልፍ ቦታዎች ላይ ያተኮረ እንደነበረ ፕሬስ ሴክሬታሪዋ ተናግረዋል።

በወቅቱ በባህር ዳር የነበረውን ሁኔታ ሲያስረዱ ''በቅድሚያ ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ በክልሉ ፕሬዝዳንት ቢሮ በመገኘት የተፈጸመውን ግድያ ትዕዛዝ ሲሰጡ ነበር'' ብለዋል።

ብ/ጄነራል አሳመነው የስብሰባ አደራሽ ውሰጥ አይግቡ እንጂ በግቢ ውሰጥ ሆነው ትዕዛዝ ሲሰጡ ነበር ያሉት ፕሬስ ሴክሬታሪዋ ይህም የክልሉ ፕሬዝደንት ዶ/ር አምባቸው መኮንን እና በሌሎች ላይ ጥቃት የተሰነዘረበት ቦታ መሆኑን አስታውሰዋል።

ብ/ጄነራል አሳምነው ከክልሉ ፕሬዝዳንት ቢሮ ወደ የክልሉ ባለስልጣናት መኖሪያ ወደሆነው ስፍራ (ገስት ሃውስ) ማቅናታቸውን ቢልለኔ ስዩም ይናገራሉ።

''በዚህም ስፍራ (የባለስልጣናት መኖሪያ ስፍራ) ሌሎች ባለስልጣናትን ከማፈን በተጨማሪ ወደ የአማራ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጋር በመደወል ኦፕሬሽኖች መወሰዳቸውን እና ቀጣይ እርምጃን በተመለከተ መግለጫ እንደሚሰጥ ለህዝብ እንዲያሳውቅ ትዕዛዝ አስተላልፈው ነበር።''

''ሶስትኛው ስፍራ የክልሉ ፖሊስ ከፖሚሽን ቢሮ ነው።'' ያሉት ብልለኔ፤ በዚሁ ስፍራ የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽን እና የክልሉን ልዩ ኃይል አዛዥ ለስበሰባ በመጥራት ታፍነው እንዲያዙ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። በዚህም ምክንያት ሁለቱ የጸጥታ ኃይል ሃላፊዎች እየተካሄደ የነበረውን የመፈንቅለ መንግሥት ማክሸፍ ሥራን ማገዝ እንዳልቻሉ ጠቁመዋል።

አራተኛው ስፍራ ደግሞ የክልሉ ምክትል ፖሊስ ኮሚሽነር መኖሪያ ቤት እንደሆነ እና እሳቸውም ሊገደሉ በእቅድ ከተያዙ ሰዎች መካክለ እንደሚገኙበት ፕሬስ ሴክሩታሪዋ ተናግረዋል።

የክልሉ እና የፌደራል ጸጥታ ኃይል አባላት እርምጃ ሲበረታ ብ/ጄነራል አሳምነው ጉዳት እንደደረሰባቸው እና በቪ 8 መኪና ታጅበው ማምለጣቸውን ተነግሯል።

ከሁለት ቀናት በኋላም በባለ ሶስት እግር መኪና ወይም ባጃጅ ወደ ጎንደር ሊያመልጡ ሲሉ ዘንዘልማ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ በክልሉ ልዩ ኃይል መገደላቸውን ቢልለኔ ስዩም አስታውቀዋል።

ተያያዥ ርዕሶች