ጥሩ ሰው ምን አይነት ነው?

ሰዎችን መርዳት Image copyright TIM GANDER/BATH UNI

የሰዎችን ጥሩ ጎን በቀላሉ ማየት ይችላሉ ወይስ ሁሉም ሰው ሊያጠቃዎት እንደሆነ ያስባሉ? ከሰዎች ጋር በሚያደርጉት ንግግር ሁሌም ግልጽ ነዎት ወይስ ሁሉንም ነገር አስልተውና ተጠንቅቀው ነው የሚናገሩት?

ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚሰጡት ምላሽ በዕለት ተዕለት የህይወት ዘይቤዎ በቀላል አገላለጽ "ቅዱስ" የሚባሉ አይነት ሰው ስለመሆንዎ እና አለመሆንዎ የመናገር አቅም አላቸው። በቅርቡ የሥነ አእምሮ ባለሙያዎች ባወጡት መዘርዝር መሰረት ሰዎችን ጥሩ የሚያስብሏቸው ምን አይነት ባህሪያት እንደሆኑና መጥፎም የሚያስብሏቸው የትኞቹ እንደሆነ አስቀምጠዋል።

ጓደኛ ለማፍራት ማወቅ ያለብን ጠቃሚ ነጥቦች

ከሁለት አስርታት በፊት የወቅቱ የሥነ አእምሮ ባለሙያዎች የሰው ልጅን ጥሩም ሆነ መጥፎ ባህሪያትን ለመረዳት በማሰብ ሦስት ዋና ዋና መገለጫዎችን ለይተው ነበር። የመጀመሪያው ከእራስ ጋር በፍቅር መውደቅ ወይም 'ናርሲሲዝም' ተብሎ የሚታወቀው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የራስን ጥቅም ለማስጠበቅ የትኛውንም ነገር ለማድረግ ዝግጁ መሆንን የተመለከተ ነው። የመጨረሻው መገለጫ ደግሞ ከባድ የሥነ ልቦና ችግር ማስተናገድ ነው።

ከዚህ ግኝት በኋላ የዘመኑ የሥነ ልቦና ባለሙያዎች እነዚህን መገለጫዎች ግምት ውስጥ በማስገባት ሰዎች በሥራ ቦታ እንዴት ስኬታማ እንደሚሆኑ፣ ግንኙነቶች እንዴት እንደሚመሰረቱና እንደሚፈርሱ እንዲሁም ውስጣዊ እርካታ እንዴት እንደሚገኝ ለማጥናት ሞክረዋል።

በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ልቦና ባለሙያና መምህር የሆኑት ስኮት ቤሪ ኮፍማን እንደሚሉት ሰዎች ብዙ ጊዜ ከጥሩው ባህሪያቸውና ማንነታቸው ይልቅ ወደ መጥፎውና በመጠራጠር የተሞላውን ውስጣዊ ስሜት እንደሚመርጡ ይናገራሉ።

"ልናበረታታውና ሁሌም ልንንከባከበው የሚገባንን ባህሪ ለምን ገሸሽ እንደምናደረገው አይገባኝም'' ይላሉ።

Image copyright Getty Images

ስኮት ቤሪ ኮፍማን ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን በሰሩት ጥናት መሰረት ደግሞ ሰዎች ጥሩ ባህሪ እንዳላቸው ማሳያ ሊሆኑ የሚችሉ መገለጫዎችን አስቀምተዋል። በዚህም መሰረት በጥናቱ የተሳተፉት ሰዎች፤ የሰዎችን ጥሩ ጎን በቀላሉ ማየት እና ይቅር ባይነት፣ የሌሎችን ስኬት ማድነቅ እንዲሁም ሰዎችን ያለፍላጎታቸው አንድ ነገር እንዲያደርጉ ከማስገደድ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ምልክቶችን አሳይተዋል።

የመጀመሪያው መገለጫ 'ሂዩማኒዝም' ወይም ሰብአዊነት ነው። ይህም የሰዎችን ክብርና ሙሉ አቅም በቀላሉ መረዳት መቻል ነው። ሁለተኛው 'ካንቲያኒዝም' የሚባል ሲሆን ስያሜው ኢማኑኤል ካንት ከተባለው ፈላስፋ የመጣ ሲሆን ሰዎችን ከእራሳችን መነጽር ብቻ መመልከት እንደሌለብን የሚያትት ነው።

ሦስተኛው ደግሞ 'ፌዝ ኢን ሂዩማኒቲ' በሰው ልጆች እምነት መጣል እንደ ማለት ሲሆን በዚህኛው መገለጫ ሰዎች ሁሌም ጥሩ ናቸው ብሎ መረዳትና የትኛውም ሰው ማንንም ለመጉዳት አያስብም ብሎ ማሰብን ያካትታል።

የ 'ምን ልታዘዝ' ድራማ ሰምና ወርቅ

የሥነ ልቦና ባለሙያው ዊሊያም ፍሊሰን እንደሚለው የሰው ልጆች በባህሪያቸው ጥሩ ናቸው ብሎ ማሰብ የሁሉም ነገር መሰረት ነው። እሱ እንደሚለው ሰዎች በአጠቃላይ ጥሩ ናቸው ብለን ባሰብን ቁጥር እራሳችንን ከሰዎች መከላከል አለብን የሚለው ተፈጥሮአዊ ስሜት እየቀነሰ ይመጣል።

ስለዚህም መጥፎ ነገር እንኳን ቢፈጽሙ ለመቅጣት ወይም ተመጣጣኝ እርምጃ ለመውሰድ ከማሰብ ይልቅ ይቅርታ ማድረግ ቀላል ይሆናል ማለት ነው።

ስኮት ቤሪ ኮፍማን አረጋግጫለሁ እንደሚሉት በሄዱበት ሁሉ ለሰዎች ደግነትንና ጥሩነትን የሚያሳዩ ሰዎች በህይወታቸው ደስታና የእርካታ ስሜትን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። ከዚህም ባለፈ ከፍ ያለ የራስ መተማመንና በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ይስተዋልባቸዋል።

ነገር ግን የጥሩ ሰዎች መገለጫዎች ምንድናቸው? ፍቅር፣ ደግነት፣ የቡድን ሥራ፣ ይቅር ባይነት፣ አመስጋኝነት፣ በሰዎች ስኬት አለመቅናት፣ አሳቢነት ወይስ ለብዙዎች ጥቅም መቆም?

መረር ያለና መጥፎ ሊባል የሚችል አይነት ባህሪ ያላቸው ሰዎች ብዙ ጊዜ ነገሮችን በቀላሉ ማከናወን የሚችሉና ደፋሮች ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ሰዎችን የመምራትና የፈጠራ አቅማቸው ከፍ ያለ እንደሆነ ጥናቱ ይጠቁማል።

በጂንስ የተሞሸሩት ጥንዶች

ስለዚህ ሙሉ በሙሉ ጥሩ የሚባል ባህሪ ያላቸው ሰዎች ያለምንም ችግር ስኬታማ ይሆናሉ ማለት ከባድ ነው። ምክንያቱም አንዳንድ ጊዜ መጥፎ የሚባሉትን ባህሪዎች መቀላቀል ከባድና አስቸጋሪ የሚባሉ ሁኔታዎችን ለመወጣት በእጅጉ ሊጠቅሙ ይችላሉ።

ዋናው ሚስጥር ያለው ጥሩ በሚባሉትና መጥፎ በሚባሉት ባህሪያት መካከል ማረፍያ ቦታ ማግኘት መቻል ነው።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ