"ኢስላማዊ ባንክ ለኢትዮጵያ ምን ይፈይዳል?"

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋከልቲ ያስተማሩትንና የዓለም አቀፉ የቢዝነስ ጥናት ኩባንያ ዴሎይት የኢትዯጵያ ቢሮ የሂውማን ካፒታል ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ሙከሚል በድሩን Image copyright Mukemil
አጭር የምስል መግለጫ ላለፉት ለ11 ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋከልቲ ያስተማሩትንና የዓለም አቀፉ የቢዝነስ ጥናት ኩባንያ ዴሎይት የኢትዮጵያ ቢሮ የሂውማን ካፒታል ሥራ አስኪያጅ የነበሩትን አቶ ሙከሚል በድሩ።

ለመሆኑ ኢስላማዊ ባንክ እስከናካቴው ቢቀርብን ምን ይቀርብናል? የብሔር ዘመም ባንኮች አልበቃ ብሎ አሁን ደግሞ ሃይማኖታዊ ባንክ መምጣቱ አደጋ የለውም? ደግሞስ እንዴት ነው ባንክ ያለ ወለድ አትራፊ የሚሆነው? ላለፉት ለ11 ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋከልቲ ያስተማሩትንና የዓለም አቀፉ የቢዝነስ ጥናት ኩባንያ ዴሎይት የኢትዮጵያ ቢሮ የሂውማን ካፒታል ሥራ አስኪያጅ የነበሩትን አቶ ሙከሚል በድሩን አነጋግረናቸዋል።

'ክርስቲያን ባንክ' ብለን አናውቅም 'ኢስላሚክ ባንክ' ለምን እንላለን? በሃይማኖት ስም ባንክ መክፈት ስጋት አያሳድርም?

ተገቢ ስጋት ሊሆን ይችላል። የስጋቱን ምንጭ መረዳት ነው ቁምነገሩ። አንዱ አሁን የዓለም ስጋት የሆነው ሽብርተኝነት ነው። ይህ ስጋት ከኢስላሙ ዓለም ጋ አብሮ ስለሚነሳና ከገንዘብ ጋ ንክኪ ሲያደርግ ስጋት ቢፈጠር የሚገርም አይሆንም።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ አሥመራ ካቀኑ እነሆ አንድ ዓመት፤ ምን ተለወጠ?

ሌላው ደግሞ ሰዎች ካላቸው የግንዛቤ ማነስ የሚመነጭ ነው። "ኢስላሚክ" የሚለውን ስም ሲሰሙ ቢዝነስ ሳይሆን ወደ አእምሯቸው የሚመጣው መስጊድ ወይም መጅሊስ ነው።

[መታወቅ ያለበት ግን] የማንኛውም ንግድ የአሠራር ሂደቱንና አተገባበሩ ከየትኛውም ፍልስፍናና እምነት ሊመነጭ ይችላል። በተመሳሳይ ይህ የባንክ አሠራር ከሸሪዓ የወሰዳቸው ደንቦች አሉት። መርሆቹን ከሸሪዓ መውሰዱ ግን የእምነት ተቋም አያሰኘውም። ወለድ አልባ ባንክ በአጭሩ ቢዝነስ እንጂ ሌላ አይደለም።

ለአንድ ባንክ ሁለቱንም አገልግሎት መሳ ለመሳ መስጠት ምንድነው ችግሩ? በወለድም ያለ ወለድም ማለቴ ነው

በእምነት ምክንያት ወይም በግል የሕይወት መርህና ፍልስፍና ወለድን የማይጠቀሙ የኅብረተሰብ ክፍሎች አሉ። ልክ አራጣን እንደሚጸየፉ የተለያየ እምነት ተከታዮች ሁሉ፤ ወለድን የማይፈቅዱ የኅብረተሰብ ክፍሎች አሉ። እነኚህን ለማካተት የፋይናንስ አማራጭ ማቅረብ አለብን። ለዚያም ነው ወለድ አልባ ባንክ 'ኢንክሉሲቭ ባንክ' የሚባለው። 'አካታች ባንክ' እንደማለት። በአገር ደረጃ ብዙ ቁጥር ነው ይሄ። እነዚህን [የኅብረተሰብ ክፍሎች] ወደ ፋይናንስ ተቋም ካላመጣናቸው ምጣኔ ሀብቱ የተቀነጨረ የተወሰነ የኅብረተሰብ ክፍል እየፈጠርን ነው ማለት ነው። ይህ ደግሞ ዞሮ ዞሮ አገርን ይጎዳል።

ራሱን የቻለ 'ኢስላሚክ' ባንክ ማቋቋም ለምን አስፈለገ ነው የኔ ጥያቄ? ወለድ ነጻ የሚፈልግ ተገልጋዮች የባንክ መስኮቶች አሉላቸው አይደለም እንዴ? ለዚያውም 10 ባንኮች...

በብዙ ደረጃ [የተንሸዋረረ] አስተሳሰብን ያዘለ ጥያቄ ነው የጠየቅከኝ።

አንደኛ ባንክ ማቋቋም መብት ነው። በቂ ሱቆች አሉና ንግድ ፍቃድ አታውጡ ይባላል እንዴ? በቢዝነስ መርህ የሚያስኬድም አይደለም። አዋሽ ባንክ እያለ ለምን ዳሽን ተከፈተ እንደማለት ነው። በአመክንዮም ስሜት የሚሰጥ ነገር አይደለም። አገልግሎቱን አስፍቼ ብከፍት ያዋጣኛል ያለን ነጋዴ/ባለሀብት ግዴለም ጠባብ መስኮት ይበቃሃልና ይቅርብህ አይባልም።

በኦሮምኛና በትግርኛ አፋቸውን የፈቱ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ባለውለታዎች

ሁለተኛ የዛሬ 10 ዓመት ገደማ ነው ብሔራዊ ባንክ ለወለድ ነጻ አገልግሎት በኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍላጎት አለ የሚል ጥናት ያወጣው። በመስኮት ደረጃ ያሉ ባንኮች የሚሰጡት አገልግሎት ደግሞ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። [የወለድ ባንክ ሊያቀርባቸው የሚችሉ] አገልግሎቶቹ ተሟልተው እየተሰጡ አይደለም። አገልገሎቱ በደንብ እየተሰጠ ነው የሚባለው ምናልባት 'ሙራባሃ' የሚባለው ሰርቪስ ብቻ ነው። ይቺ ግን አንድ አገልግሎት ብቻ ናት። በአሁኑ ሰዓት በመስኮት የማይሰጡ በጣም ብዙ የወለድ ነጻ የፋይናንስ አገልግሎቶች አሉ። መስኮቱ ጠባብ ነው። ይሄን ያዩ ሰዎች መስኮቱን ባንክ እናድርገው ቢሉ ምንድነው ችግሩ?

ሦስተኛ ከወለድ ጋ [በሩቁም ቢሆን] አልነካካም ብሎ ከፋይናንስ ዘርፉ ገለል ያለ በርካታ ሕዝብ አለ። ይህንን የምልህ ባንክ ተጠቃሚን ብቻ አይደለም። ባንክ ላይ ባለቤት መሆን የሚፈልግም ጭምር ነው የምልህ። አሁን [ለምን ራሱን የቻለ] የወለድ ነጻ ባንክ ትከፍታለህ ስትለው በሌላ ቋንቋ ምን እያልከው ነው...ግዴለም ከኔ ሱቅ ስኳርም ሳሙናም ግዛኝ። አንተ ግን ሱቅ እንዳትከፍት እያልከው ነው።

በወለድ የሚሠሩ ባንኮች ከወለድ ነጻ አገልግሎት እየሰጡም ከነሱ ጋ መሥራት የማይፈልግ ሰዎች አሉ እያሉኝ ነው?

[ትክክል] ለዚህ ሌላ ማሳያ የሚሆን ነገር ልንገርህ። በወለድ ምክንያት ከባንኮች ጋ ላለመነካካት በርካታ ሰዎች ኮንዶሚንየም ዕድልን አሳልፈዋል። ብዙ ጥናቶች ዜጎች በወለድ ከሚሠሩ ባንኮች ጋ ላለመነካካት ገንዘባቸውን ወደ ባንክ ይዘው እንደማይመጡ አሳይተዋል።

ዜጋን በሚከተለው መርህና እምነቱ ከፋይናንስ ተጠቃሚነት ማግለል ደግሞ ኢፍትሃዊነት ነው።

ባለ አምስት ኮከቡ የኖርዌይ እስር ቤት

ይህን በምሳሌ ላስረዳህ። በ2017/18 የግል ባንኮቻችን ወደ 20 ቢሊዮን ጥቅል ትርፍ አትርፈዋል። ከዚያ ውስጥ ግማሹ የንግድ ባንክ ነው። ወለድ ነክ ባንክ ጋር መሥራት የማይፈልጉ ዜጎች አሉ። በእምነታቸው ምክንያት ሊሆን ይችላል ይሄ፣ በሌላ ምክንያት ሊሆንም ይችላል። እነዚህን በመስኮት ብቻ ይወሰኑ ስትል ከዚህ 20 ቢሊዮን ትርፍ እያገለልካቸው ነው።

ምን ማለቴ ነው... የባንክ ባለድርሻ መሆን የሚፈልጉ አሉ። 'እኔ [በተዘዋዋሪም ቢሆን] ከወለድ አልነካካም ስላሉ ብቻ በእጅ አዙር ከዚህ ግዙፍ ትርፍ ለምን ታገላቸዋለህ?

ለምንድነው ከወለድ ነጻ አገልግሎት ከሚሰጥ ባንክ ጋርም ቢሆን መሥራት የማይፈልጉት?

በእምነትም ሆነ በሌላ የግል ምርጫቸው ይሄን የማይፈልጉ አሉ። ይህን የባንክ ዘርፍ ልዩ የሚያደርገው በባንኩ የሚንቀሳቀሰው ገንዘብ በሁሉም መልኩ ንጹህ መሆን አለበት ብሎ መነሳቱ ነው። ለምሳሌ ቢራ ፋብሪካ በዚህ ባንክ መስተናገድ አይችልም። ኅብረተሰብን ይጎዳሉ፤ የሞራል ዝቅጠት ያደርሳሉ የሚባሉ ዘርፎች በሙሉ ወለድ ነጻ ባንክ በሩቁም ቢሆን አይነካካም። መጠጥ፣ ዝሙት፣ ቁማርና ሌሎች ለኅብረተሰብ ጠንቅ ናቸው በሚባሉ ቢዝነሶች/ኢንዱስትሪዎች ንክኪ የለውም። ማስታወቂያ አይሰጥም፣ አያበድርም፣ ተቀማጭም አያደርግም...ወዘተ።

ኢስላሚክ ባንቢቀር ምን ይጎድልብናል? ቢኖርስ ምን ይፈይዳል?

አንዱ በእምነቱ ምክንያት ከዘርፉ የራቀን ሰፊ ማኅበረሰብ ፋይናንሱን ይዞ መጥቶ ወደ ኢኮኖሚው እንዲያስገባው ማስቻሉ ነው። በትንሹ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ወለድ አይፈልግም ብንል [ሌላውን ትተን ማለቴ ነው] እንደው በትንሹ 30 ምናምን ፐርሰንት ኢትዮጵያዊ ከፋይናንስ ተገለለ ማለት ነው። የሱ ጉዳት ደግሞ የአገር ጉዳት ነው።

ሁለተኛ እንደ አገር ከገንዘብ ንክኪ የራቀ ማኅበረሰብ መፍጠር ይፈለጋል። ይህ የብዙ አገር ግብ ነው። ከባንክ የተገለለ ማኅብረሰብ ማለት ብሩን እንሥራ ውስጥ ያስቀመጠ ማኅበረሰብ ማለት ነው። [ ከወለድ ነጻ አገልግሎት ይቅርብ ስንል] ኢኮኖሚው ውስጥ ሊዘዋወር ይችል የነበረን ግዙፍ ገንዘብ እንሥራው ውስጥ እንደተቀመጠ ይቅር ማለት ነው።

የጥላቻ ንግግርን የሚያሠራጩ ዳያስፖራዎች እንዴት በሕግ ሊጠየቁ ይችላሉ?

አሁን እንኳ በወለድ አልባ መስኮቶች 30 ቢሊዮን ብር ይንቀሳቀሳል። ይህ የሚያሳየን ሰፊ ፍላጎት እንዳለ ነው።

ከዚህ ሌላ በመደበኛ ባንክ የሌለ በዚህኛው ባንክ ሊመጣ ተጨማሪ ነገር አለ? መጠነኛ የሥራ ዕድል ከመፈት ባሻገር ማለቴ ነው።

ማኅበራዊ ኃላፊነት ከመወጣት አንጻር ልንመለከተው እንችላለን።

ከወለድ ነጻ ባንክ አንዱ ግዴታ ድህነት ቅነሳ ላይ መሳተፍ ነው። በዚህ ረገድ እነዚህ ባንኮች መደበኛው ባንክ ከሚያወጣው በብዙ እጥፍ ያወጣሉ። ይህም ከባለሐብት ገንዘብ ተቀብሎ ለድሀ ማከፋፈል ነው። ለምሳሌ በመደበኛ ባንክ አሠራር በየወሩ ደንበኛው መክፈል ሲኖርበት ሳይከፍል ሲቀር ወለድ ይከመርበታል። በዚህኛው ግን ወለድ ስለሌለ ቅጣት የሚጣልበት ሁኔታ አለ። ከዚህ የቅጣት ገንዘብ የተወሰነች ፐርሰንት ወደ ማኅበረሰብ ችሮታ የምትሄድ ናት። ይህ ለድህነት ቅነሳ ከፈተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል። ለምሳሌ 2017 በዚህ መንገድ በተቀረው ዓለም 518 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ተደርጓል።

ወሲባዊ ትንኮሳ ያደረሰባት አለቃዋን በማጋለጧ የታሠረችው ሴት

የፋይናንስ መረጋጋትን ከመፍጠር አንጻርም ከወለድ ነጻ ባንኮች ይጠቀሳሉ። የዓለም የገንዘብ ቀውስን ታስታውሳለህ። በደፈናው ችግሩን የፈጠረው በትንቢት ላይ የተመሠረተ የፋይናንስ አሠራር ነበር። በወለድ ነጻ ባንክ አሠራር ግን ስቶክ ገዘተህ ይጨምራል ይቀንሳል እያልክ መቆመር አትችልም። ይህ አይፈቀድም። ሁሉም ነገር የሚመሠረተው ከንብረትና ከምርታማነት ጋር በተያያዘና በሚጨበጥ ነገር ላይ ነው። ለዚህ ነው ያ ሁሉ የፋይናንስ ተቋም ሲንኮታኮት ወለድ አልባ ባንኮች ያን አስቸጋሪ ጊዜ ያለፉት።

በአገራችን ሁኔታም ተያያዥ ነገር ማንሳት ይቻላል።

ልማት ባንክን ውሰድ። በጋምቤላና ሌሎች ቦታዎች ለሰፋፊ እርሻዎች ከፍተኛ ገንዘብ ለቀቀ። ባለሃብቶቹ [እርሻውን] ለይስሙላ ነካኩትና ገንዘቡን ከተማ መጥተው ፎቅ ሠሩበት። ባንኩ አሁን ችግር ውስጥ ገብቷል። የተበላሸ የብድር መጠኑ 40 ከመቶ አልፏል። ይሄ ዓይነቱ አጋጣሚ በወለድ ነጻ ባንክ አሠራር ሊከሰት የሚችልበት ዕድል ጠባብ ነው። ለምን ካልከኝ የሚከተለው የቢዝነስ ፍልስፍና [ንብረት መር] ወይም 'አሴት-ባክድ' ስለሆነ ነው።

አዲሱ የፌስቡክ ዲጅታል ገንዘብ አፍሪካን ያጥለቀልቅ ይሆን?

በዚህ ወለድ አልባ ባንኪንግ አሠራር ንብረቱን እንጂ ገንዘቡን አትከተልም። ምን ማለት ነው ባንኩ ገንዘቡን አይሰጥህም። ገንዘብ ሰጥቶህ ትርፉን በወለድ አይጠብቅም። ይልቅስ ሄዶ አብሮህ ነው የሚሠራው። ትርፍና ኪሳራን ነው የሚጋራው። ትራክተር ግዛ ብሎ ብር አይሰጥህም። ራሱ ነው የሚገዛው፤ ሥራ ማስኬጃ ብሎ ጥሬ ገንዘብ አይሰጥም። አብሮህ ነው የሚያመርተው። ስለዚህ ተመሳሳይ ውድቀቶች የመከሰት ዕድላቸው ዝቅተኛ ይሆናል።

ከወለድ አልነካካም የሚለው ሕዝብ ቁጥሩ ይታወቃል?

ይሄ በብሔራዊ ደረጃ መረጃ ማሰባሰብ ይጠይቃል። ቀላል ቁጥር እንዳልሆነ ግን ደግሜ መናገር እችላለሁ። የተወሰኑ ለ2ኛ ዲግሪ ማሟ የተሰሩ የጥናት ወረቀቶችን ይህንን ያመላክታሉ። ሰዎች ወደ ባንክ ለምን አይሄዱም ተብለው ለሚነሱ ጥናቶች አብዛኛው ድምዳሜ ከእምነቴና አስተሳሰቤ ጋር አይጣጣምልኝም የሚለው ብዙ ቁጥር ይይዛል። ከአካባቢዬ ደግሞ ልነሳልህ። እጅግ ቁጥሩ በርካታ የሆነ ሰው ኮንዶሚንየም ዕድልን አሳልፏል። በእምነቱ የተነሳ። የወለድ ሲስተም ውስጥ ላለመግባት።

እንዲሁ በየትኛውም ምክንያት ወደ [ማንኛውም ዓይነት] ባንክ ተደራሽ ያልሆነ ሕዝብ ቁጥር ከ50 በመቶ አያንስም። የእኔን ግምት ከጠየቅከኝ ከዚህ ውስጥ ብዙውን ቁጥር ከእምነት ጋር ሊያያዝ የሚችል እንደሆነ መገመት ይቻላል።

ከሙስሊም አገራት ውጭ ይህ የባንክ ዘርፍ ምን ያህል ይሠራበታል? በኛ አገርስ ባንኩ ለእስልምና ተከታዮች ብቻ ነው የሚከፈተው?

አንዱ የግንዛቤ እጥረት ይሄ ነው። አንደኛ ይሄን ባንክ ሊጠቀም የሚችለው ብቻ ሳይሆን ሊመሠርት የሚችለውም ከአንድ እምነት የሚመጣ ነው አይደለም። ይሄ ቢዝነስ እንጂ ሃይማኖት አይደለም። ትርፍ ያመጣልኛል ያለ ማንም መሥራች ሊሆን ይችላል። ከግንዛቤ እጥረት የተነሳ ኢስላሚክ ባንክ የሙስሊም ባንክ ሆኖ ይታየናል እንጂ ማንኛውም ዜጋ የባንኩ ባለቤትም ሆነ ተጠቃሚ መሆን ይችላል። በብዙ አገራት የሚሠራበት ነው።

ነገሩ እንደ ተጨማሪ አማራጭ ነው መታየት ያለበት።

አንድ የሰፈርህ ሱቅ እኔ ቢራ አልሸጥም፤ ለስላሳ መጠጥ ነው የምሸጠው ሊል ይችላል። የሱቁ ባለቤት የትኛውንም ሃይማኖት ሊከተል ይችላል። ደንበኞቹም እንዲሁ።

ከሙስሊም አገራት ውጭ...

አዎ...እንዳልኩህ በርካታ አገራት የሚሠራበት ነው። ከአረቡ ዓለም ውጭ በዚህ ባንክ ብዙ ልምድ ያላት እንግሊዝ ናት። አል-ረያን የሚባለው ከወለድ ነጻ ባንክ ግዙፉ የሪቴይለር [ችርቻሮ] ባንክ ነው በእንግሊዝ። ከ8 ዓመት በፊት ባንኩ ከነበሩት ደንበኞች ከአስሩ አንዱ ብቻ ነበር ሙስሊም ያልሆነው። በ2018 ምን ሆነ...ከሦስቱ የባንኩ ደንበኞቹ አንዱ ብቻ ነው ሙስሊም ያልሆነው።

በደቡብ ወሎ እውን የህፃናት ስርቆት አለ?

ኋላ ላይ ጥናት ተሠራ። ለምን ቁጥሩ በከፍተኛ ሁኔታ አደገ የሚል። ግንዛቤ ሲጨምር ነው ሁኔታዎች የሚለወጡት።

ወልድ አልባ ባንኮች በሆንግ ኮንግ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ በኬንያም ከፍተኛ ገበያ አላቸው።

አሁን ባሉ 16 ባንኮች የሌለ ምን ምን ትሩፋት ሊኖር ይችላል? ከተጠቃሚ አንጻር...

16ቱ ባንኮች ያላቸው አገልግሎት ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ነው።

160 ቢሊየን ብር ወደ ገበያ በብድር መልክ አስገብተዋል 16 ባንኮች በድምሩ። ይህ ገንዘብ የመጣው በዋናነት ከአስቀማጩ ከሚሰበስቡት ገንዘብ ነው። ከሰበሰቡት ገንዘብ ለብድር የሚያውሉት በጣም ትንሽ መጠን ነው። ትርፋቸውን በዲቪደንድ ይከፋፈሉታል። ሌላው ለካፒታል ኢንቨስትመንት ያውሉታል። ለብድር የሚያውሉት የሰበሰቡትን ነው። ይህ ደግሞ አንጻራዊ መልኩ በጣም ትንሽ መጠን ነው። ወለድ አልባው ባንክ ግን ገንዘቡን አብዛኛውን አብሮ ለመሥራት ነው የሚያውለው...

ሌላው ወለድ አልባ ባንኮች ሲመጡ ደግሞ አዲስ አማራጭ ይዘው ይመጣሉ።

ለምሳሌ ለሥራ ፈጠራ ያላቸውን አማራጭ ማንሳት ይቻላል።

ጥሩ ሰው ምን አይነት ነው?

በርካታ ወጣቶች ሐሳብ ይዘው ፋይናንስ አጥተው ተቀምጠዋል። ወለድ አልባው ባንክ አሠራሩ ትርፍና ኪሳራን የመጋራት ዘዴ ነው። ስለዚህ ሐሳብ አለኝ ካልክና አዋጪነቱ ከታመነበት ባንኩ ካሽ ላይሰጥህ ይችላል። ሲያምንበት ግን አብሮህ ይሠራል። ይሄ [እንደኛ የሥራ አጥ ቁጥር ለበረከተበት አገር] መልካም ዜና ይመስለኛል።

አሁን ባሉት 16 ባንኮች ግን ይሄ የለም። ባንክ በራሱ ኢንቨስትመንት ውስጥ አይገባም። ሊያደርግ የሚችለው ምንድነው በከፍተኛ ወለድ ገንዘብ ቢያበድርህ ነው። እሱም መያዣ ትጠየቃለህ። ሙሻረካና ሙዳረባ አገልግሎት ግን ከዚህ በተቃራኒው ነው የሚሰሩት።

ነገሩን ካነሱት አይቀር...ምንድነው ሙሻረካ-ሙዳረባ? እንዴት ነው ያለ ወለድ ባንክ አትራፊ የሚሆነው? ለምንስ ሰው ወለድ የማያገኝ ከሆነ ብሩን ወደ ባንክ ይዞ ይመጣል? እስኪ በቀላል ምሳሌ ያስረዱን...

እንደምታውቀው በመደበኛው ባንክ ተቀማጭና ተንቀሳቃሽ ሒሳብ የሚባል አለ። ደንበኛው ባስቀመጠው ገንዘብ ከ7 እስከ 9 በመቶ ወለድ ያገኝበታል። በወለድ አልባ ያለው ግን ሙዳረባና ሙሻረካ የሚባል የሒሳብ ዓይነት ነው፤ በዋናነት።

መሠረታዊው ልዩነት በወለድ አልባ አስቀማጩ ገንዘቡን የሚያስቀምጠው ባንኩ በተቀመጠው ገንዘብ ሠርቶ ከሚያገኘው ትርፍና ኪሳራ ለመጋራት ወስኖ ነው። ስለዚህ ገንዘቡን ያለ ወለድ ቢያስቀምጥም ምንም ጥቅም አያገኝም ማለት አይደለም።

«ሙሉ ቤተሰቤን በኢትዮጵያው አውሮፕላን አደጋ አጥቻለሁ»

በመደበኛ ባንክ ልክ ገንዘብ ስታስቀምጥ በእርግጠኝነት ወለድህን ታገኛለህ፤ የተተመነውን። በወለድ አልባው ግን አስቀማጩ ወይም ባንኩ በመረጠው መንገድ ተነግዶበት ከሚያመጣው ትርፍ ላይ ተካፋይ ለመሆን ነው ገንዘቡን የሚያስቀምጠው። ስለዚህ ብር ስታስቀምጥ ትርፍ አታገኝም ማለትም አይደለም፤ ታገኛለህ ማለትም አይደለም።

በአጭሩ አንድ አስቀማጭ ሲመጣ ባንኩ ካተረፈ ልጋራ፣ ከከሰረም ልከስር ብሎ ነው የሚገባው።

ከወለድ ነጻ በመስኮት ብቻ እኔና አንተ በምናወራበት ሰዓት 30 ቢሊዮን ብር ተሰብስቧል። ይሄ ገንዘብ ግዴለም ወለድ አይሰጠኝ ያለ ሰው ያስቀመጠው ገንዘብ ነው። ስለዚህ እነዚህ ባንኮች ሲከፈቱ እንዲህ የሚሰበሰው ብር አስቀማጩ ጋ በሚደረግ ስምምነት ቢዝነስ ይሠራበታል ማለት ነው። ቢዝነሱ ሲሳካ አስቀማጩ ያተርፋል፤ ሲከስር ይከስራል።

ዋና ዋና የሚባሉት አገልግሎቶቹን በቀላሉ በምሳሌ ቢያስረዱን ብዬ ነበር...

ብዙ ናቸው። ሦስቱን ብቻ እናንሳ...

አንዱ ሙራባሃ ይባላል። 10 የሚሆኑት ወለድ አልባ መስኮቶች ይህን አገልግሎት ይሰጣሉ።

እንበልና መኪና መግዛት ፈለክ። ባንኩን በሙራባሃ መኪና መግዛት እፈልጋለሁ ስትለው መኪናውን ባንተ ፍላጎት ተመሥርቶ ራሱ ይገዛዋል። መኪናውን ገዝቼልህ ላንተ ስሸጥልህ ማትረፍ የምፈልገው 40ሺህ ብር ነው ሊለው ይችላል። ይደራደራሉ። ገንዘቤን መቼ ትሰጠኛለህ ሲለው ከ2 ዓመት በኋላ ሊለው ይችላል፤ ደንበኛው። ዝርዝሩ ብዙ ነው ብቻ ባንኩ ይገዛና ለደንበኛው አትርፎ ይሸጥለታል። ክፍያውን የሚቀበለው ግን በቁርጥ ዋጋ ለመክፈል በተስማማበት ጊዜ ነው። መኪናውን ግን በስሙ ነው የሚገዛው ባንኩ። ሪስኩን የሚያካክሰው በስሙ በመግዛት ነው። ልክ እንደ ነጋዴ ገዝቶ አትርፎ ነው የሚሸጥልህ፤ ትርፉም ባንኩ ያተርፈኛል በሚለው በድርድር የሚወሰን ነው። ባንኩ ነጋዴ ይሆናል ማለት ነው።

ከመደበኛው ባንክ የሚለየው ደንበኛው በውሉ መሠረት መጨረሻ ላይ መኪና ተገዝቶ ስለተሰጠው የሚከፍለው ገንዘብ የተቆረጠ መሆኑ ነው። ከፍና ዝቅ ማድረግ አይቻልም።

ከባንኩ ጋ በሽርክና መሥራት ብለውኝ ነበር ቅድ...

ልመጣልህ ነው...ሁለተኛው አገልግሎት ሙዳረባ ይባላል።

ለምሳሌ ካፌ መክፈት ብፈልግ ባንኩን አነጋግረዋለሁ። በሙዳረባ አካውንት ብቻ የሚያስቀምጡ ደንበኞች ይኖሩታል ባንኩ። አስቀማጮቹ ምን ይላሉ 'ባንኩ እኔን ወክሎ፣ ቢዝነስ ሐሳብ ያለውን ሰው ተቀብሎ፣ ገምግሞ አዋጪ ነው በሚለው ዘርፍ እኔን ወክሎ ይነግድልኝ' ሊሉ ይችላሉ። ስለዚህ ክህሎትና ሐሳብ ያለው ሰው፣ ነገር ግን ብር የሌለው ሰው ሲመጣ ባንኩ ደግሞ ብሩን ይዞ ይገባል። ንግድ ይነግዳሉ ትርፍንም ኪሳራንም ይጋራሉ ማለት ነው። ይሄ በተለይ ለወጣት ሥራ ፈጣሪዎች በጣም ጠቃሚ ነው።

ሦስተኛው ሙሻረካ ይባላል። ይህ እንደ ሙዳረባ ሆኖ ነገር ግን የቢዝነስ ሐሳብ አመንጪው በገንዘብም ይሳተፋል። በአጭሩ የሽርክና ቢዝነስ ማለት ነው። ሲያተርፉም ሲከስሩም አብረው ነው።

ዲሚኒሺንግ ሙሻረካ የሚበልም ዘርፍ አለ። እዚሁ ላይ፤ ምን ማለት መሰለህ እየቀነሰ የሚሄድ ሽርክና ማለት ነው። ባንኩ ለምሳሌ እኔ ንብረቱን አልፈልግም ስለዚህ እየቀነሰ በሚመጣ ሽርክና እንግባ ካለ ሽርክናውን በጋራ ይጀምሩና ባንኩ ቀስ እያለ ከሽርክናው ይወጣል። ባለቤትነቱም በተወሰነ ዓመታት የግለሰቡ ይሆናል።

ለምሳሌ አንድ ግለሰብ ይመጣና ሪልስቴት ልገዛ ፈልጌ ነው ይለዋል። አንድ ሚሊዯን ብር ቢሆን ቤቱ ደንበኛው 4 መቶ ሺህ አለኝ ቢል ባንኩ 600 ሺህ ይከፍልና ቤቱ የሁለቱም ይሆናል። ልብ ማለት ያለብህ ቤቱ የደንበኛው ብቻ አለመሆኑን ነው። ቤቱ የባንኩም ጭምር ነው። ቤቱ እየተከራየ ነው ብንል ግለሰቡ የኪራይ ብሩን በስምምነታቸው መሠረት ለባንኩ እየከፈለ ይቀንሳል። ባንኩ ከቤቱ የስምምነቱን አትርፎ ግለሰቡን ሙሉ የቤት ባለቤት ያደርገዋል። ይሄ ሲሆን ቫሊዊሸን የንብረት ዋጋ ግምት እንዳለ ሆኖ ለባንኩ የኪራይ ዋጋ ለገዛበት ዋጋ እየከፈለ በሆነ ዓመት ቤቱን ለደንበኛው ለቆለት ይወጣል።

“በአሁኗ ኢትዮጵያ በፀረ ሽብር ሕጉ ክስ መኖር የለበትም” ዳንኤል በቀለ

ለምሳሌ ቤቱ 10ሺ ቢከራይ ባንኩ በየወሩ የኪራይ ብር 9ሺህ ሲያገኝ ለሱ ትርፉ ያ ነው። 90 በመቶ ለከፈለለት ደግሞ ገዢው በየዓመቱ 10 ፐርሰንት እያስለቀቀ ይመጣል።

ሌላውና ሦስተኛው ኢጃራህ የሚባል ነው። ይሄ ከሊዝ ፋይናንሲንግ ጋ የሚመሳሰል ነው።

ባንኩ የሆነ ማሽን ይገዛና ላንተ በኪራይ ያከራይሃል። ስምምነታችሁ የ10 ዓመት ቢሆን ማሽኑን ለ10 ዓመት ያከራይሃል። ሳልቬጅ [ሲያረጅ] ትገዛኛለህ አይልህም። በ11ኛው ዓመት የግዴታ ማሽኑን ትገዛለህ ተብለህ አትገደድም። ስለዚህ ቅድም ባንኩ ነጋዴ ሆኖ ነበር አሁን ደግሞ ባንኩ አከራይ ሆነ ማለት ነው።

አሁን በመስኮት ደረጃ የሚሠሩት ባንኮች ብዙ ብር ሰብስበዋል። ወለድ አልባ ባንኮች ሲከፈቱ ፍልሰት አይገጥማቸውም? ሕልውናቸው አያሰጋም?

አሁን በመስኮት የሚሰሩት ዝም ብለው ይወድቃሉ ማለት አደለም። በጣም ጠንካራ ልምዱ ያላቸው እነሱ ናቸው። ቁጭ ብለው አያዩም። ውድድር ነው። ብዙ ተወዳዳሪ የሚሆኑ ይመስለኛል። ገና ለገና ባንኮቹ ውድድር ሊገጥማቸው ይችላል ተብሎ ግን ወለድ አልባ ባንክ አይከለከልም። አዲስ የሚመጣው ባንከጅ ተጨማሪ አማራጭ ይሆናል እንጂ አሁን ያሉትን ያንኮታኩታል ማለት አይደለም።

በርካታ ኢስላሚክ ባንኮች ምሥረታ ላይ እንደሆኑ ይሰማል። አሁን እንኳ በሥራ ላይ ያሉት ባንኮች ለመጣመር እየሞከሩ አዲስ የሚመጡት ተፈረካክሰው ነው። ለምን?ለመሆኑ የውጭ ባንክ መምጣት ኢስላሚክ ባንክን አያሰጋውም?

[ያው እኔ ኢስላሚክ ባንክ ከሚለው ይልቅ ወለድ ነጻ ባንክ የሚለው አጠራር ነው የሚመቸኝ፤ እንደሱ እያልኩ ልቀጥልልህ]

የውጭ ባንክ ሲመጣ ወለድ አልባ ባንክን በደንብ ያሰጋዋል። በቅርብ ካሉት እንኳ ብናይ እነ ኬሲቢ [የኬንያው] በደንብ ነው ልምድ ያላቸው፤ የደቡብ አፍሪካውም እንዲሁ። ካፒታል አቅማቸውም ግዙፍ ነው። አንዱ አዲስ ለሚመሠረቱ ባንኮች ያላቸው ዕድል የችርቻሮ ባንኪንግ ዕድል ነው። በየገጠሩ እየገቡ በመሥራት ጫነውን መቋቋም ይችላሉ።

ተበታትነው ለምን ይመሠረታሉ ላልከው...

እኔ አሁን የታየውን ነገር ታፍኖ እንደተለቀቀ ሙቀት ነው የማየው...ማኅብረሰቡ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሮ ነበር፤ [ለዓመታት ዘርፉ ባለመፈቀዱ]። ልክ ሲፈቀድ ሰው ተፈጥሯዊ ምላሽ ነው የሰጠው፤ ሲፈቀድ ሩጫ ጨመረ፤ ይሄ ለምን ሆነ አይባልም። [እየመጡ ያሉት] ብዙ ሊመስልህ ይችላል እንጂ በቅርቡ አውቀዋለሁ...አሁን ላይ ያለኝ መረጃ ብሔራዊ ባንክ ሄደው የተመዘገቡት 3 ብቻ ናቸው። ከ3ቱ ሁለቱ አንድ ለመሆን ድርድር ላይ ናቸው። ስለዚህ ምናልባት ቢበዛ ሁለት ወይ ሦስት ባንኮች ቢወጡ ነው።

ሰዎች ባንክ በዛ ይላሉ። ማርኬት በጣም ሰፊ እንደሆነ አይረዱም። 40 ሚሊዮን ሕዝብ ኖሯቸው 70 ባንክ ላላቸው አገራት እያሉ ለኛ ሦስትና አራት ባንክ ብዙ ነው ብዬ አላምንም።

የነዚህ ባንኮች ፈተና ምንድነው ይላሉ?

ከሰው ኃይልና ከመሠረተ ልማት አንጻር ፈተና ይኖራል። ወለድ አልባ ፋይናንስኢንግ የሚያሰለጥን ከፍተኛ ተቋም የለንም። ሌላው ፈተና በተለይም ከሬጉሌሽን አንጻር ብዙ ሥራ ይጠበቃል። ሜዳውን ምቹ የማድረግ ሥራ ከብሔራዊ ባንክ ያስፈልጋል። ብሔራዊ ባንክ በዚህ ረገድ ያለው ዝግጁነት አመርቂ የሚባል አይደለም።

የመጨረሻ ጥያቄ ላንሳ፡ አንድ ቢራ ፋብሪካ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ይዞ ከወለድ ነጻ ባንኮች ሂሳብ ልክፈት ቢል ይፈቀድለታል?

አይችልም።

አመሰግናለሁ!

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ