የኦሎምፒክ ተወዳዳሪው በመስጠም ላይ የነበረን ሙሽራ ታደገ

ማኒኒ በኦሎምፒክ እና ዓለም ሻምፒዮን ሜዳሊያዎችን ማሸነፍ ችሏል Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ማኒኒ በኦሎምፒክ እና ዓለም ሻምፒዮን ሜዳሊያዎችን ማሸነፍ ችሏል

ከሁለት ቀናት በፊት ትዳር የመሰረተው አንድሬ ቤዴንቶ ሜድትራኒያን ባህር ላይ በምትገኝ ደሴት ላይ ባለች ሳርዲኒያ በምትባል የሃይቅ ዳርቻ ላይ ከትዳር አጋሩ ጋር እየተዝናና ነበር።

ድንገት ሃይቁ ላይ ሲንሳፈፍበት የነበረው ፕላስቲክ ከእጁ አምልጦ ቤዴንቶ መስመጥ ጀመረ። እድለኛ ሆኖ በኦሎምፒክ ውድድር ላይ ጣሊያንን ወክሎ የተወዳደረው ፊሊፖ ማኒኒ በቅርብ እርቀት ይገኝ ነበር። የቀድሞ የዓለም ሻምፒዮን ዋናተኛም እየሰጠመ የነበረውን ቤዴንቶን ህይወት ማትረፍ ችሏል።

የህይወት አድን ዋናተኞች እስኪደርሱለት ድረስ ዋናተኛው ሊሰጥም የነበረውን ቤዴንቶን ጭንቅላት ከውሃ በላይ አድርጎ ቆይቷል።

"እባካቹን ለቤተሰቦቼ ንገሩልኝ! መዋኘት አልችልም፤ ለቤተሰቦቼ ብቸኛ ነኝ"

ስደተኞችን ያሳፈረች መርከብ ተገልብጣ 65 ሰዎች ሞቱ

በቱኒዚያ የ48 ስደተኞች ሕይወት አለፈ

''ማድረግ የሚጠበቅብኝን ነው ያደረኩት'' ብሏል የቀድሞ የዓለም ሻምፒዮን ዋናተኛ።

ቤዴንቶ ከሁለት ቀናት በፊት ያገባ ሲሆን፤ ከትዳር አጋሩ ጋር በአየር የተሞላ ፕላስቲክ መንሳፈፊያ ላይ ተመርኩዘው በሃይቁ ዳርቻ ሲዝናኑ ነበር። ከዚያ ቤዴንቶ ከፕላስቲኩ መንሳፈፊያ ላይ ወደቀ። ወዲያው ኃይለኛ ንፋስ የፕላስቲክ መንሳፈፊያውን እንደወሰደው አብረውት የነበሩት ጓደኞቹ ይናገራሉ።

በህመም ምክያት እግሮቹን ማንቀሳቀስ የማይችለው የ45 ዓመቱ ቤደንቶ ህይቱን ለማትረፍ ቢጥርም እየሰጠመ ነበር።

Image copyright Andrea Benedetto
አጭር የምስል መግለጫ በህመም ምክያት እግሮቹን ማንቀሳቀስ የማይችለው የ45 ዓመቱ ቤደንቶ ህይቱን ለማትረፍ ቢጥርም እየሰጠመ ነበር።

በሁነቱ የተደናገጡት የቤዴንቶ ጓደኞች መጯጯህ ጀመሩ። ህይወት አድን ሰራተኞችም ቤዴንቶን ለማዳን ወደ ሃይቁ ቢገቡም ዋናተኛው ቀድሞ ደርሶ ህይወቱን አትርፏል።

''አጠገቡ ሲደርስ መናገር እንኳን አቅቶት ነበር፤ የባህር ውሃ ጠጥቶ ነበር'' ሲል ዋናተኛው ለጣሊያን መገናኛ ብዙሃን ተናግሯል።

የመስጠም አደጋ ያጋጠመው ቤዴንቶ ራሱን ስቶ የነበረ ሲሆን ከሰዓታት ቆይታ በኋላ ራሱን ያወቀው ሆስፒታል ከደረሰ በኋላ ነበር። ''ህይወቴን ያዳነው ፊሊፖ መሆኑን ሆስፒታል ከደረስኩ በኋላ ነው ያወኩት። እሱን የማመሰግንበት አጋጣሚ እንኳን አላገኘሁም። በአካል አግኝቼው እንደማመሰግነው ተስፋ አለኝ።'' ሲል ተናግሯል።

ዋናተኛው በባህር ዳርቻው ላይ ከታዋቂ ፍቅረኛው ጋር እየተዝናና ነበር።