የአሜሪካው ጄት አውሮፕላን በበረራ ላይ ባጋጠመው ችግር ለማረፍ ተገደደ

የዴልታ አየር መንገድ አውሮፕላኖች በሃርትስፊልድ ጃክሰን አትላንታ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ቆመው። Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ዴልታ አየር መንገድ ዋና መቀመጫው አትላታ ጆርጂያ ነው

በዴልታ አየር መንገድ ከአትላንታ ወደ ባልቲሞር ሲጓዝ በነበረው አውሮፕላን ተሳፍረው የነበሩ ተሳፋሪዎች አውሮፕላኑ የሞተር ችግር ካጋጠመው በኋላ እስኪያርፍ ድረስ የነበረውን አስፈሪ ሁኔታ እየገለጹ ነው።

በአንዱ ተሳፋሪ የተቀረጸው ቪዲዮ እንደሚያሳየው የአውሮፕላኑ ሞተር በእሳት ተያይዞ እና የሞተሩ አካል ተላቆ በንፋስ ሲወዛወዝ ይታያል።

ተሳፋሪዎች ድንገት የፍንዳታ ድምጽ እንደሰሙ እና ወዲያው አውሮፕላኑ በጪስ መሞላቱን ተናግረዋል።

አሜሪካ ባህረ ሰላጤውን ለመቆጣጠር ወታደራዊ ጥምረት ልትመሰርት ነው

አምነስቲ በቅርቡ የታሰሩ ጋዜጠኞች ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ መንግሥትን ነቀፈ

ዴልታ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር 1425 ከአትላንታ ተነስቶ ወደ ባልቲሞር ሲያደርገው በነበረው በረራ 154 ሰዎችን አስፍሮ የነበረ ሲሆን፤ አውሮፕላኑ ችግር ካጋጠመው በኋላ ሰሜን ካሊፎርኒያ በሰላም ማረፍ ችሏል።

አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ አውሮፕላኑ አጋጥሞት የነበረው ችግር ከሞተር ጋር የተያያዘ መሆኑን እና በተፈጠረው ችግር ጉዳት የደረሰበት ሰው እንደሌላ አረጋግጧል።

በአውሮፕላኑ ተሳፍሮ የነበረው ሎጋን ዌብ ክስተቱን ቀረጾ አስቀርቷል።

አቬር ፖርች የተባለች ሌላ ተሳፋሪ ለመገናኛ ብዙሃን ስትናገር፣ በረራ ከተጀመረ ከአንድ ሰዓት በኋላ የፍንዳታ ድምጽ መስማቷን እና ከዚያም አውሮፕላኑ በጭስ መሞላቱን ተናግራለች።

''ከዚያ በጣም ተደናገጥን። አውሮፕላኑም ፍጥነቱን ቀነሰ'' በማለት ሁኔታውን ገልጻለች።

ታይለር ክሬኡገር የተባለው ተሳፋሪ ደግሞ ለወላጆቼ ''እወዳችኋላሁ'' ብዬ የጽሁፍ መልዕክት ላኩላቸው ሲል ተናግሯል።

አብራሪዎች እና የበረራ አስተናጋጆች የአውሮፕላኑ ሞተር መስራት ማቆሙን በመጥቀስ በአደጋ ጊዜ ለማረፍ የሚያስችላቸውን ዝግጅት መጀመራቸውን አስታወቁ ሲል ሌላ ተሳፋሪ ለመገናኛ ብዙሃን ተናግሯል።

ላጤ እናት መሆን የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ሴቶች

ችግሩ ያጋጠመው አውሮፕላን፣ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ 32 ዓመታት ያስቆጠረ ማክዶኔል ዳጉላስ ኤምዲ-88 መሆኑን ኤቢሲ ዘግቧል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ