የጣልያን ፍርድ ቤት በተሳሳተ ማንነት ለሶስት ዓመታት የታሰረው ኤርትራዊ ነፃ መሆኑን ወሰነ

መድሃኔ ተስፋማርያም Image copyright Reuters

የጣልያን ፍርድ ቤት በህገወጥ ሰው ዝውውር የታሰረው ኤርትራዊ የተሳሳተ ሰው መሆኑን በማመን በነፃ አሰናበትቶታል።

መድሃኔ ተስፋማርያም በህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪነት የሚፈለገው ኤርትራዊው መድሃኔ ይሕደጎ መርእድ ወይም በቅፅል ስሙ "ጄኔራል" ነው በሚል ነበር ለእስር ተዳርጎ የቆየው።

ለባለፉት ሶስት አመታትም ተፈላጊው ሰው እሱ እንዳልሆነ ቢወተውትም የሚያምነው አካል አልተገኘም ነበር።

የአንዱ እርግማን ለአንዱ ምርቃን፡ ኢትዮጵያን መጠጊያ ያደረጉ የስደተኞች ታሪክ

አፍጋናዊቷ ስደተኛ በኢትዮጵያ

አርብ ዕለት ፍርድ ቤቱ ስህተት እንደሰራ ቢያምንም በህገወጥ ሰዎች ዝውውር ተሳትፎ ነበረው በሚል አምስት አመት ፈርዶበታል።

ነገር ግን በእስር ያሳለፈው ጊዜ በቂ ሆኖ በመገኘቱ ፍርድ ቤቱ በነፃ አሰናብቶታል።

"ከሶስት ዓመታት ውትወታ በኋላ ዳኛው ስንለው የነበረውን ሰምቶናል። መድሃኔ በላም እርባታ የሚተዳደር ግለሰብ ነው እንጂ በህገ ወጥ ሰዎች ዝውውር እጁ የለበትም ስንል ቆይተናል" በማለት ጠበቃው ሚሸል ካላንትሮፓ ለጋርዲያን ተናግሯል።

“የመከላከያው በአደባባይ ሚዲዎችን እከሳለሁ ማለት አስፈሪ ነው” ዶ/ር አብዲሳ ዘርዓይ

ጠበቃው ጨምሮም በህገወጥ ሰዎች ዝውውር ተሳትፏል በሚል የቀረበበትንም ክስም ይግኝ እንደሚጠይቁ አስታውቋል። መድሃኔ በላም እርባታና በአናጢነት ይተዳደር የነበረ ሲሆን ጣልያንም ጥገኝነት ጠይቆ ነበር ተብሏል።

የእንግሊዝና የጣልያን መርማሪዎች መድሃኔን በመያዝ ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ ሲሆን ከሶስት አመታት በፊትም ሲያዝ የእንግሊዝ ወንጀል መረጃ ባወጣው መግለጫ በሰበሰቡት መረጃ እንደሚተማመኑ ገልፀው ነበር።

Image copyright NCA/Polizia di Stato
አጭር የምስል መግለጫ በግራ በኩል ያለው መድሃኔ ይሕደጎ መርእድ ሲሆን በቀኝ ያለው ደግሞ መድሃኔ ተስፋ ማርያም ነው

ነገር ግን በህገወጥ መንገድ ዝውውር ሰለባ የሆኑና ቤተሰቦቻቸው ይህንን ግለሰብ እንደማያውቁት ፍርድ ቤት ተናግረው ነበር።

በመልካቸው የሚለያዩ ቢሆንም እንዲሁም የዲኤንኤ መረጃም እሱ እንደሆነ ባያሳይም አቃቤ ህግጋቱ እሱ ነው በሚልም እንደፀኑ ተዘግቧል።

በስም መመሳሰል በቁጥጥር ስር የዋለው ሰው እውነተኛ ማንነቱን ለማረጋገጥ የፈጀባቸው ጊዜ ሦስት አመት ከሁለት ወር ነው።

የሰብኣዊ መብቶች ተሟጋችዋ ኤርትራዊዋ ሜሮን እስጢፋኖስ ዛሬ በነበረው የፍርድ ሂደቱ ሶስት ሰዓታትን እንደፈጀ ገልፃ "በህይወቴ ካጋጠመኝ ረጅም የፍርድ ሂደት" በማለት ትናገራለች።

እህቱ ህይወት ተስፋማርያም በበኩሏ ቤተሰቡ ረጅም የጭንቅ አመታት ማሳለፉን ትናገራለች።

"ወንድሜ በተሳሳተ ማንነት እስር ቤት ውስጥ ምን እያደረግኩኝ ነው በሚል ጭንቀት ውስጥ ነበር። ከሦስት አመት በላይ የእኛ ቤተሰብ ብቻ ሳይሆን የኤርትራ ህዝብም ሲጨነቅ ነበር። አሁን ግን ለእግዚኣብሄር እና ለሁሉም ህዝብ የምናመሰግንበት ጊዜ ነው" ብላለች።

መድሃኔ ይሕደጎ በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 2013 ዓ.ም 359 ስደተኞችን ህይወት በቀጠፈው በጣልያን ደሴት ላምፓዱሳ ባጋጠመው የጀልባ መስመጥ ጋር በተያያዘ ክስ ቀርቦበት ነበር።