ትራምፕ የኢራን ኒውክሌር ስምምነትን ያፈረሱት ''ኦባማን ለማበሳጫት'' ነው

US President Donald Trump Image copyright AFP

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ከኢራን ጋር ደርሳ የነበረውን የኒውክሌር ስምምነት ያፈረሱት ባራክ ኦባማን ለማበሳጨት መሆኑን በአሜሪካ የዩናይትድ ኪንግደም አምባሳደር የነበሩት ሰር ኪም ዳሮች መልዕክት አጋለጠ።

የሰር ኪም ዳሮች አፍትልኮ የወጣው መልዕክት፤ የትራምፕ አስተዳደርን ውሳኔን በቅድሞ ፕሬዝደንት የተደረሱት ዲፕሎማሲያዊ ድሎችን ማፈራረስ ላይ ያተኮረ ነው ሲሉ መተቸታቸውን ዴይሊ ሜይል ዘግቧል።

ፕሬዝደንት ትራምፕ ''ግላዊ በሆኑ ምክንያቶች' ስምምቱን ችላ ብለውታል፤ ምክንያቱም ስምምቱ የተደረሰው ከእርሳቸው በፊት በነበሩት ፕሬዝድንት ነውና" ሲሉ የቀድሞ አምባሳደር ጽፈዋል።

የእንግሊዝ አምባሳደር የትራምፕ አስተዳደርን 'የፈረሰ እና የተከፋፈለ' ሲሉ ወረፉ

ኒው ዮርክ መብራት መጣ

ጋዜጣው እንደ ዘገባው ከሆነ ይህ መልዕከት የተጻፈው በወቅቱ የዩናይድት ኪንግደም የውጪ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ቦሪስ ጆንሰን አሜሪካ ከኢራን ጋር የተደረሰውን የኒውክለር ስምምነት እንዳታፈርስ የትራምፕ አስተዳደርን በጠየቁበት ወቅት ነው።

የአሜሪካ እና ኢራን የኒውክለር ስምምነት ኢራን ዩራኒያም የማበልጸግ እንቅሳቃሴዎቿን እንድተገድብ የሚያስገድድ ነበር። በተጨማሪም ኢራን ላይ ተጥለው የቆዩት መጣኔ ሃብታዊ ማዕቀቦች እንዲነሱ፣ ዓለም አቀፍ የኒውክለር እንቀስቃሴን የሚያጠኑ ቡድን አባላት በኢራን ክትትል እንዲያደርጉ የሚፈቅድ ነበር።

ከቀናት በፊትም ዴይሊ ሜይል ኪም ዳሮች የትራምፕ አስተዳደርን 'ደካማ፣ በራሱ የማይተማመን፣ ክህሎት የሌለው' ሲሉ ወርፈዋል ሲል መዘገቡ ይታወሳል።

ከቀድሞው የእንግሊዝ አምባሳደር አፈትልከው በወጡ ኢሜይሎች ላይ ዋይት ሃውስ በዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ሥር ''የፈረሰ'' እና ''የተከፋፈለ'' ነው ብለውት ነበር።

Image copyright AFP/PA Media
አጭር የምስል መግለጫ ፕሬዝደንት ትራምፕ አና ሰር ኪም ዳሮች

የብሪታኒያ የውጪ ጉዳይ ቢሮ አፈትልከው የወጡት ኢሜይሎች ''ከባድ ችግር ፈጥረዋል'' በማለት ሃሰተኛ አለመሆናቸውን አረጋግጧል።

ሰር ኪም ዳሮች ከመንግሥታቸው ጋር የተለዋወጧቸው መልዕክቶች አፈትልከው ከወጡ በኋላ በገዛ ፍቃዳቸው አምባዳሰርነታቸውን መልቀቃቸው ይታወሳል።

ፕሬዝደንት ትራምፕ ሰር ኪም ዳሮችን የአገር መሪ ይለዋል ተብሎ በማይጠበቅ ሁኔታ ''በጣም ደደብ ሰውዬ ነው...' ማለታቸው ባለፈው ሳምንት የዓለም መገናኛ ብዙኃንን ትኩረት የሳበ ጉዳይ ነበር።